«አቤቱ፥ አምናላሁ፤ ነገር ግን አለማመኔን ርዳው» (ማር.፱፥፳፬)

«እምነትስ፣ ተስፋ ስለምናደርገው ነገር የምታረጋግጥ፥ የማናየውንም ነገር የምታስረዳ ናት» (ዕብ. ፲፩፥፩) እንደተባለው ሰው ተስፋን ከአምነት ያገኛል፡፡ አዳም ቢበድልም እንኳን ቸሩ አምላክ እግዚአብሔር በኋላ ዘመን ከልጅ ልጁ ተወልዶ እንደሚያድነው ቃል በጋባለት ጊዜ ተስፋ አግኝቷል፡፡ የመዳኑን ነገር በእምነቱ ተስፋ ሆነለት፡፡ እምነት ለእግዚአብሔር ያለንን ፍቅር የምንገልጥበት፣ እርሱን ደስ የምናሰኝበት የሕይወት መሠረት ነው፡፡ ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ ይህን ሲያስረዳ «ያለ እምነትም እግዚአብሔርን ደስ ማሰኘት አይቻልም» ብሏል፡፡ (ዕብ.፲፩፥፮)

‹‹የእግዚአብሔር ምሕረቱ ብዙ ነው እያልክ በኃጢአት ላይ ኃጢአት አትሥራ›› (ሲራክ ፭፥፭)

እግዚአብሔርን በመፍራት መኖር ሲገባ በየዕለት ተግባራችን በአዕምሮአችን ክፋት በማሰብና ተንኮል ለመሥራት በመሻት፣ ከሰብአዊነት ይልቅ ጭካኔ በልባችን ሞልቶ ጥቅምን በማስበለጥ ኃጢአትንና ክፋትና እየሠራን አንውላን፡፡ ፈሪሀ እግዚአብሔር የሌላቸው ሰዎች ፈጣሪን ስለሚረሱ ባዕድነትን ይላመዳሉ፤ ግብዝም ይሆናሉ፤ ይህም ማንነታቸውን አስለውጦ ወደ ርኩስነት ይለውጣቸዋል፡፡ መጥፎ መንፈስ በውስጣቸው በሚገባበትም ጊዜ መንፈስ ቅዱስ ስለሚርቃቸው ጥሩውን በመጥላት ክፋትን ይወዳሉ፤ በመጥፎነታቸውም ይመካሉ፡፡ እግዚአብሔር አምላክን መዳፈር ይጀምራሉ፤ ሕጉን በተላለፉና ሥርዓቱን በጣሱ ቁጥርም በዓለማዊ ኑሮአቸው፣ በአምልኮት እና በተቀደሱ ሥፍራዎች ጭምር ኃጢአትን ይፈጽማሉ፡፡ ይህም አምላክን ያስቆጣል፤ ለመቅሰፍትም ይዳርጋል፤ ለመርገምና ለመከራ አሳልፎ ይሰጣል፤ በአገልግሎት፣ በክርስትናና በመንፈሳዊ ሕይወትም ዝለትን፤ በሃይማኖትና በምግባር ጉድለትን ያመጣል፤ ከእግዚአብሔር መንግሥት ይለያል፤ ለዘላለም ሞትም አሳልፎ ይሰጣል፡፡ ለዚህ ነው መጽሐፍ ቅዱስ ‹‹የኃጢአት ደመወዝ ሞት ነው›› የሚለን (ሮሜ.፮፥፳፫)

‹‹ልበ ንጹሓን ብፁዓን ናቸው፤ እግዚእብሔርን ያዩታልና›› (ማቴ. ፭፥፲)

በዘመነ ሥጋዌ ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ከናዝሬት ወደ ቅፍርናሆም በሔደ ጊዜ የገሊላ፣ የኢየሩሳሌም፣ የይሁዳ እና የዮርዳኖስ ሕዝብ ዝናውን ሰምተው ወደ እርሱ መጡ፡፡ በዚያም የመንግሥቱንም ወንጌል ሲሰብክ ‹‹……ልበ ንጹሐን ብፁዓን ናቸው፤ እግዚአብሔርን ያዩታልና…….ደስ ይበላችሁ፤ሐሤትንም አድርጉ፤ ዋጋችሁ በሰማያት ብዙ ነውና፤ ከእናንተ አስቀድሞ የነበሩ ነቢያትንም እንዲሁ አሳድደዋቸው ነበርና›› ብሎ አስተማራቸው፡፡ (ማቴ.፭፥፩-፲፪)

«በደብረ ዘይት ተቀምጦ ስለ ዓለም ፍጻሜና ምልክቱ አስተማረ» (ማቴ.፳፬)

የወይራ ተራራው ደብረ ዘይት ምሥጢር የሚነገርበት እና የወይራ ፍሬ ምሥጢራት የሚፈጸሙበት ስለነበር ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በዚያ ይገኝ ነበር። ደቀ መዛሙርቱም ለብቻቸው ወደ እርሱ ቀርበው ስለዳግም ምጽአት «የዓለሙ ፍጻሜስ ምልክቱ ምንድነው?» ሲሉ ጠየቁት። (ማቴ.፳፬፥፫) እርሱም አስቀድሞ «ማንም እንዳያስታችሁ ተጠንቀቁ» አላቸው፤

‹‹አቤቱ÷ በመዓትህ አትቅሠፈኝ÷ በመቅሰፍትህም አትገሥጸኝ›› (መዝ. ፴፯፥፩)

ከጥንት ጀምሮ ዓለም በእንደዚህ ዓይነት በሽታ ስትጠቃ እንደቆየች ታሪክ ምስክር ነው፤ እንደ ኤች.አይ.ቪ ኤድስ ቫይረስና የቅርብ ጊዜ ክስተት የሆኑት ኢቦላና ሳርስ በሽታዎች ሰዎችን በተለያዩ መንገድ በመያዝና በማሠቃየት ለሞት ዳርገዋል፡፡ ሀገራችን ኢትዮጵያም ከተጠቁት የዓለም ክፍላት ውስጥ አንዷ ናት፤ በኤች.አይ.ቪ ኤድስ ሺዎችን አጥታለች፤ አሁንም እንደ ሰደድ እሳት እየተዛመተ ያለው ኮሮና ቫይረስ ዋና ከተማዋ አዲስ አበባ እንደገባ ምንጮች የሕክምና ማስረጃ ምንጮ ይፋ አድርገዋል፡፡
በዓለም ዙሩያ በሕክምናው ዘርፍ ያሉ ባለሙያዎች ለበሽታው መድኃኒት በማጣታቸው መንግሥታት ለዜጎቻቸው ቅድመ ጥንቃቄ እንዲያደርጉ አስጠንቅቀዋል፤ መከላከያ ሊሆኑ ይችላሉ የሚሏቸውን መንገዶች አስታውቀዋል፡፡
ነገር ግን ቤተክርስቲያናችን ሰዎች በክፉ ደዌ ሲያዙ ፈውሰ ሥጋን የሚያገኙት በጸበል፤ በጾምና በጾሎት እንደሆነ ታስተምራለች፤ እንደነዚህ ዓይነቱ ተዛማች በሽታም የእግዚአብሔር ቁጣ መሆኑን ታስረዳለች፡፡ ልበ አምላክ ዳዊትም በመዝሙሩ ‹‹አቤቱ÷ በመዓትህ አትቅሠፈኝ÷ በመቅሰፍትህም አትገሥጸኝ›› ሲል አምላኩን ተማጽኗል፡፡ (መዝ. ፴፯፥፩)

ዝክረ ግማደ መስቀሉ!

ቅድስት ዕሌኒም መስከረም ፲፯ ቀን ቁፋሮ እንዲጀመር አዘዘች፡፡ ቁፋሮውም ሰባት ወር ያህል ከፈጀ በኋላ መጋቢት ፲ ቀን ሦስት መስቀሎች በአንድነት ተገኙ፡፡ ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የተሰቀለበትን መስቀል መለየት ግን አልተቻለም ነበር፡፡ ስለዚህም ሦስቱን መስቀሎች ወደ ሞተ ሰው በመውሰድ በተራ በተራ አስቀመጧቸው፤ ያን ጊዜ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የተሰቀለበት መስቀል የሞተውን ሰው በማስነሳቱ መስቀሉ ተለየ፤ ተአምሩም ተገለጸ፡፡ ቅድስት ዕሌኒና መላው ክርስቲያን ለመስቀሉ ሰገዱለት፡፡

ክብር ለኢትዮጵያውያን ሰማዕታት!

በዚህ ዓመት ታኅሣሥ ወር ፳፬ ቀን ጸጥታ አስከባሪዎች በሁለት ወጣት ኦርቶዶክሳውያን ላይ በግፍ የገደሉትን ስፍራ የ ‹‹፳፬ ቀበሌ›› ወደ ቀደመ ክብሩ ተመልሶ ሕንጻ ቤተክርስቲያን እንዲሠራበት በተላለፈው ውሳኔ መሠረት ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ፓትርያክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለሃይማኖት በተገኙበት መጋቢት  ፮ ፳፻፲፪ ዓ.ም. የመሠረት ድንጋይ ተጥሏል፡፡

“እነሆ÷ ድነሃል ግን ከዚህ የባሰ እንዳያገኝህ ዳግመኛ እንዳትበድል ተጠንቀቅ” (ዮሐ.፭፤፲፬)

ቤተ ክርስቲያናችን ሁሉንም በሥርዓት የምታከናውን ስንዱ እመቤት ናትና በዐቢይ ጾም ከሚገኙት ሰንበታት ውስጥ ዐራተኛውን ሰንበት መጻጉዕ ብላ ሰይማዋለች፡፡ አምላካችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ብንወድቅ እንደሚያነሣን፣ ብንታመም እንደሚፈውሰን ለማስተማር፣ እንዲሁም ደግሞ ከመጻጉዕ ሕይወት እንማር ዘንድ መታሰቢያውን አደረገች፡፡ “ዳግመኛ እንዳትበድል ተጠንቀቅ” እንዳለ ከኃጢአት ወደ ጽድቅ፣ ከሞት ወደ ሕይወት፣ እንሸጋገር ዘንድ፣ የአምላካችንን ቃል መፈጸም እንደሚገባን፣ እሰከ ሞትም መታመን እንዳለብን ያስተምረናል፡፡

‹‹የአባቴን ቤት የንግድ ቤት አታድርጉ›› (ዮሐ.፪፥፲፮)

በዐቢይ ጾም ሦስተኛው ሳምንት በእለተ እሑድ ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ወደ ኢየሩሳሌም መጣ፤ በቤተ መቅደስም በሬዎችንና በጎችን፥ ርግቦችንም የሚሸጡትን፥ ገንዘብ ለዋጮችንም ተቀምጠው አገኘ፡፡ ይህን ባለመውደዱም የገመድ ጅራፍ ካበጀ በኋላ በጎችንና በሮዎችን እንዲሁም ሁሉንም ከቤተ መቅደስ አስወጣቸው፤ የሻጮቹንም ገንዘብ በተነባቸው፤ ገበታዎቻቸውንም ገለበጠ፤ ርግብ ይሸጡ የነበሩትን ደግሞ ‹‹ይህን ከዚህ አውጡ፤ የአባቴን ቤት የንግድ ቤት አታድርጉ አላቸው፡፡›› (ዮሐ.፪፥፲፬-፲፮)

ቅድስት

ቅድስት ማለት የተለየች፣ የተመረጠች፣ የከበረች ማለት ነው። ቅዱስ የሚለው ቃል  እንደ  የአገባቡ  ለፈጣሪም  ለፍጡርም  ያገለግላል።  ለፈጣሪ ሲነገር  እንደ  ፈጣሪነቱ  ትርጉሙ  ይሰፋል  ይጠልቃል  ለፍጡር  ሲነገር ደግሞ  እንደ  ፍጡርነቱ  እና  እንደ  ቅድስናው  ደረጃ  ትርጉሙ ሊወሰን  ይችላል።