መፃጒዕ
በዘመነ ሥጋዌ በኢየሩሳሌም ውስጥ ይኖሩ የነበሩ በተለያየ ሕመም ይሠቃዩ የነበሩ ሰዎች ለመፈወስ የሚሰበሰቡባት ቤተ ሳይዳ የምትባል አንዲት መጠመቂያ ነበረች፡፡ አምስትም መመላለሻ ነበራት፡፡ በዚያም ብዙ ድውያን ይተኛሉ፤ ከእነርሱም ውስጥ የታወሩ፣ አንካሾች፣ የሰለሉ፣ ልምሹ የሆኑ፣ በየእርከን እርከኖች ላይ ይተኙ ነበር፡፡ የእግዚአብሔር መልአክም ውኃውን ለመቀደስ በሚወርድ ጊዜ ድምፁ እስኪያስተጋባ ድረስ ውኃው ይናወጣል፡፡ ድውያኑም በዚያ ሥፍራ ተኝተው የውኃውን መናወጥ ይጠባበቃሉ፡፡ ምክንያቱም በዕለተ ሰንበት (ቀዳሚት) ውኃው ሲናወጥ ቀድሞ ወደ ውኃው የገባ አንድ ሰው ከደዌው ይፈወስ ነበርና፡፡…