‹‹አልጋህን ተሸክመህ ሂድ›› (ዮሐ.፭፥፩-፱)

ለሠላሳ ስምንት ዓመታት በደዌ ዳኛ በአልጋ ቁራኛ ተይዞ የነበረው አንድ በሽተኛ ሰው በጌታችን ቃል ተፈውሶና አልጋውን ተሸክሞ ወደ ቤቱ መሄዱ በቅዱስ መጽሐፍ ተመዝግቧል፡፡

ምኵራብ

‹‹ከመሥዋዕት ይልቅ ምሕረትን እወዳለሁ፤ የሰንበት ጌታዋ የምሕረት አባቷም እኔ ነኝ፤ የሰው ልጅም የሰንበት ጌታዋ ነው፡፡ ያባቴን ቤት የንግድ ቦታ አታድርጉት››

ቅድስት

ቅድስት ማለት ‹የተለየች፣ የነጻች፣ የከበረች› ማለት ነው፡፡ ይኸውም ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ጾም የጀመረባት፣ ልዩ፣ የተቀደሰች፣ የከበረች፣ ንጹሕ፣ ክቡር በሚሆን በጌታችን የተጾመች መሆኗን ያመላክታል፡፡ ይህች ጾም በማቴዎስ ወንጌል የተገለጠች ስትሆን፣ አምላካችን በገዳመ ቆሮንቶስ ዐርባ መዓልትና ዐርባ ሌሊት በጾመበት ጊዜያት ሦስቱን አርእስተ ኃጣውእ ድል አድርጓል፡፡ (ማቴ.፬፥፪)

ዘወረደ

ከሰማይ ከወረደው በቀር ወደ ሰማይ የወጣ የለም ካለው ከጌታችን ከመድኃኒታችን ከኢየሱስ ክርስቶስ ቃል በመነሣት ሊቁ ቅዱስ ያሬድ በዚህ ዕለት ምስባክ ‹‹አዳምን ለማዳን ከሰማይ የወረደውን አይሁድ ሰቀሉት፤ የሰማይን ሥልጣን ያለው የሁሉ ጌታ እንደሆነም ምንም አላወቁም›› ብሎ ተናግሮ ነበር፡፡ ይህም ድርሰት በቤተ ክርስቲያናችን የጾም መጀመሪያ የሆነው ዕለተ ሰንበት ዋዜማ፣ መግቢያ (መሐትው) ሆኖ ከዋዜማ በፊት ምንጊዜም በየዓመቱ ይቆማል፤ ይዘመራል፤ ይመሰገናል ማለት ነው፡፡

ዐቢይ ጾም

‹ዐቢይ›› የተባለው የዓለማት ፈጣሪ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ለአርአያነት ጾሞ የመሠረተው ጾም ስለሆነ ነው፡፡ በኦርቶዶክሳዊት ቤተ ክርስቲያን ካሉት ሰባት የአዋጅ አጽዋማት ረጅሙ (፶፭ ቀን ያለው) ስለሆነ ደግሞ ‹‹ሁዳዴ›› ይባላል፡፡ ኢትዮጵያዊው የዜማና የቅዱሳት መጻሕፍት ሊቅ ቅዱስ ያሬድ በዐቢይ ጾም ውስጥ የሚገኙትን ስምንት ሣምንታት ለትምህርት፣ ለአዘክሮና ለምስጋና በሚመች መልኩ ልዩ ስያሜዎች ሰጥቷቸዋል፡፡ ስለሆነም በእያንዳንዱ ሳምንት (ሰንበት) የሚነበቡ፣ የሚተረጎሙ፣ የሚዘከሩ፣ የሚዘመሩ ልዩ ልዩ መጽሐፍ ቅዱሣዊ ኩነቶችና አስተምህሮዎች አሉ፡፡

‹‹ከዚያ ወዲያ ኢየሱስ ከዲያብሎስ ይፈተን ዘንድ መንፈስ ወደ ምድረ በዳ ወሰደው›› (ማቴ.፬፥፩)

በወንጌል ቅዱስ ማቴዎስ ስለ ጌታችን መድኃኒታችንን ኢየሱስ ክርስቶስ ዐቢይ ጾም ሲጽፍ  ‹‹ከዚያ ወዲያ›› በማለት ከጀምረ በኋላ እርሱ ለሰዎች ድኅነት ሲል ለዐርባ ቀንና ሌሊት ያለ መብልና መጠጥ በጾም በምድረ በዳ እንደቆየ ይገልጽልናል፡፡

የነነዌ ጾም

ነነዌ የሜሶፖታምያ ከተሞች ከሆኑት መካከል አንዷ ናት፡፡ ከሞሱል ከተማ በተቃራኒ ከባግዳድ ሰሜን ምዕራብ ፫፻፶ ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ እንደ ነበረች በታረክ ይነገራል፡፡ በ፵፻ (ዐራት ሺህ) ቅድመ ልደተ ክርስቶስ በናምሩድ በኩል ከተቆረቆረችም በኋላ በ፲፻፬፻ (አንድ ሺህ ዐራት መቶ) ቅድመ ልደተ ክርስቶስ የአሦራውያን ዋና ከተማ ሆናለች፡፡ (ዘፍ.፲፥፲፩፣፪ኛነገ.፲፱፥፴፮)

በከተማዋም ታዋቂ የነበረ አስታሮት የተባለ የጣዖት ቤተ ነበረ፡፡ በዚህች ከተማ የሚኖሩት ሰዎች የሚሠሩት ክፋትና ኃጢአት እጅግ ከመብዛቱ የተነሣ ጽዋው ሞልቶ መጥፊያቸው ስለ ደረሰ ለፍጥረቱ ርኅራኄ ያለው እግዚአብሔር ግን ንስሓ ይገቡ ዘንድ ነቢዩ ዮናስን ልኮላቸዋል፡፡ ይህ ነቢይ ከአሕዛብ ወደ አሕዛብ ወደ ንስሓ ይጠራቸው ዘንድ ነበር የተላከ ነው፡፡

ጾመ ገሀድ

የከበሩ አባቶቻችን ሐዋርያት የጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የልደትና የጥምቀት በዓል በረቡዕ ወይም በዓርብ ቀን ቢሆን በበዓለ ኃምሳ የሚበላውን የጥሉላት መብል በጥዋት በመብላት ምእመናን ሁሉ በዓሉን እንዲአከብሩ አዝዘዋል፤ ይህም ጾመ ገሀድ ነው፡፡ እነዚህ ሁለቱ የእግዚአብሔር ታላላቅ በዓላቶቹ ናቸውና።

ዘመነ ስብከት

ዘመነ ስብከት ከጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የልደት በዓል በፊት ከታኅሣሥ ፯ ጀምሮ እስከ ፳፱ ያለው ወቅት ነው፡፡ ሳምንታቱም ስብከት፣ ብርሃንና ኖላዊ ይባላሉ፡፡ በዚህም ወቅት ስለ ጌታችን ኢየሱስ  መወለድ ነቢያት የተናገሩት ትንቢት ይሰበክበታል፡፡

ጾመ ነቢያት

ከሰባቱ የአዋጅ አጽዋማት መካከል አንዱ የሆነውን ጾመ ነቢያት በየዓመቱ ከኅዳር ፲፭ ጀምሮ እስከ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የልደት በዓል ድረስ በአምላካችን ቅዱስ ፈቃዱ እንጾማለን!