ነቢዩ ኢያሱ ወልደ ነዌ
የነዌ ልጅ ኢያሱ የታላቁ ነቢይና መስፍን የነቢያት አለቃ የሙሴ ደቀ መዝሙር የነበረ በኋላም እግዚአብሔር የመረጠው ነቢይ ነው፡፡ የስሙ ትርጓሜም‹‹ እግዚአብሔር አዳኝ›› ማለት ነው፤ ‹‹የእግዚአብሔር ባሪያ ሙሴ ከሞተ በኋላ እግዚአብሔር የሙሴን አገልጋይ የነዌን ልጅ ኢያሱን እንዲህ ብሎ ተናገረው። ባሪያዬ ሙሴ ሞቶአል፤ አሁንም አንተና ይህ ሕዝብ ሁሉ ተነሥታችሁ ለእስራኤል ልጆች ወደምሰጣቸው ምድር ይህን ዮርዳኖስ ተሻገሩ። ለሙሴ እንደ ነገርሁት የእግራችሁ ጫማ የሚረግጠውን ቦታ ሁሉ ለእናንተ ሰጥቼአለሁ።…