‹‹ምን እናድርግ?›› (ግብ.ሐዋ.፪፥፴፯)
ፀሐይ ብርሃኗን በምትሰጥበት የመዓልት ጉዟችን የጨለማ ጉዞ እስኪመስል በፍርሃት ተሸብበናል፤ ከቦታ ቦታ ተንቀሳቅሶ የመኖር ተስፋችን፣ እምነትን በወደድነውም ሆነ በፈለግነው ሥፍራ የመግለጽ ነጻነታችን ሲመነምን፣ ነገን በብሩህ ተስፋ የምንመለከትበት የእምነት መነጽራችን በጥርጥር ደመና ሲደበዝዝብን፣ ከአቀበቱ ጀርባ ሜዳ፣ ከጨለማው ማዶ ብርሃን እንዳለን ማስተዋል ተሳነን፡፡



