‹‹እስከ መጨረሻው የሚጸና ግን እርሱ ይድናል›› (ማቴ.፳፬፥፲፫)
ማመንንና መታመንን የሚፈታተኑ ነገሮች በዓለም ባይኖሩ ኖሮ ስለ ጽናት አይነገርም ነበር፡፡ ጽናትን የሚወልደው የመከራና የፈተና ብዛት ነው፡፡ በዚህ ዘመን ክርስቲያን ለመሆን እንዲሁም ስመ እግዚአብሔርን ለመጥራት እንፈልግ እንጂ ስለ ክርስትና መከራን ለመቀበል ግን አንፈልግም፡፡ ይህ ደግሞ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ‹‹በዓለም ሳላችሁ መከራ አለባችሁ፤ ግን አይዟችሁ፤ እኔ ዓለምን አሸንፌዋለሁ›› በማለት ለተናገረው ቃል ምንኛ ባዕድ እየሆንን ለመምጣታችን ማሳያ ነው፡፡ (ዮሐ.፲፮፥፴፫)