ጥምቀት
ጥር 9 ቀን 2005 ዓ.ም
በዲ/ን ዮሴፍ ይኲኖ አምላክ
በሰው ልጅ ዘላለማዊ ድኅነት ውስጥ ትልቁን ድርሻ የሚይዘው ሥርዓተ ጥምቀት ከሌሎቹ ምሥጢራተ ቤተ ክርስቲያን በቀዳሚነት የሚፈጸምና የማይደገም ሥርዓት ነው፡፡ ብርሃነ ዓለም ቅዱስ ጳውሎስ “አንዲት ጥመቀት” በማለት የሥርዓተ ጥምቀትን አለመደገምና አለመሠለስ ገልጦ ተናግሯል /ኤፌ.4፥5/፡፡ በቤተ ክርስቲያን ታሪክ ተመዝግቦ እንደሚገኘውና፥ የታናሽ እስያ ክፍል በሆነችው ቁስጥንጥንያ በ381 ዓ.ም. የተሰበሰቡ 150 የሃይማኖት አባቶቻችን “ወነአምን በአሐቲ ጥምቀት ለሥርየተ ኀጢአት፣ ለኀጢአት ማስተሥረያ /ኀጢአትን በምታስተሠርይ/ በአንዲት ጥምቀት እናምናለን” በማለት የጥምቀትን አንድ መሆንና ኀጢአትን በደልን የምታርቅ፣ የምታስወግድ ስለመሆኗ በእግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስ ተመርተው ተናግረዋል፡፡ ሃይማኖታቸውንም ገልጠዋል፡፡


በሰሜን ሸዋ ሀገረ ስብከት የምትገኘው ታሪካዊቷና ተአምረኛዋ የደብረ ምጥማቅ የጻድቃኔ ቅድስት ማርያም ቤተ ክርስቲያን እሰከ 25 ሚሊዮን ብር በሚደርስ ወጪ የቤተ ክርስቲያኑን ሕንፃ እየተገነባ መሆኑን በአዲስ አበባ የተቋቋመው የሕንፃ አሠሪ ኮሚቴ ገለጸ፡፡
የቅዱስ ሲኖዶስ ምልዐተ ጉባኤ ጥር 6 ቀን 2005 ዓ.ም. የሚካሄደው አስቸኳይ ስብሰባ ለዕርቀ ሰላሙ ቅድሚያ ሰጥቶ እንደሚመክር የቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ጸሓፊ፣ የደቡብና ምዕራብ አዲስ አበባ አህጉረ ስብከትና የከፋ ሸካ ቤንች ማጂ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ሕዝቅኤል በተለይ ለስምዐ ጽድቅ ጋዜጣ ገለጹ፡፡
የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ዐቃቤ መንበረ ፓትርያርክና የአርሲ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ናትናኤል የጌታችን የመድኀኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስ የልደት በዓል ምክንያት በማድረግ ባስተላለፉት መልእክት “በሀገራችን በኢትዮጵያ በገጠርና በከተማ፣ ከሀገር ውጭ በተለያዩ አህጉር የምትኖሩ የሀገራችንን ዳር ድንበር ለመጠበቅና ለማስከበር በየጠረፉ የቆማችሁ በሕመም ምክንያት በየሆስፒታሉ ያላችሁ እንዲሁም የሕግ ታሪሚዎች ሆናችሁ በማረሚያ ቤት የምትገኙ ኢትዮጵያውያንና ኢትዮጵያውያት እንኳን ለ2005 ዓ.ም. የጌታችን የአምላካችንና የመድኀኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስ በዐለ ልደት በሰላም አደረሳችሁ፡፡” ካሉ በኋላ “በጌታችን ቤዛነት እንድን ዘንድ አንድ ልጁን ወደ ዓለም ልኮአልና፤ እግዚአብሔር ለእኛ ያለውን ፍቅር በዚህ አውቀናል፡፡ እግዚአብሔር ከፍጡራን ሁሉ የተለየና ከአእምሮ በላይ የሆነ መለኮታዊ ኀይል ያለው አምላክ በመሆኑ የባሕርዩን ጥልቅነት በምልአት ማወቅ ፈጽሞ የማይቻል ቢሆንም እርሱ ራሱ በገለጸልን መጠን የተወሰኑ ነገሮችን እናውቃለን፡፡ ቅዱስ መጽሐፍ “እግዚአብሔር ፍቅር ነው” ብሎ ምልአተ ፍቅሩን ካስረደ በኋላ በማስረጃ ሲያብራራ ቤዛ ሆኖ የሰውን ልጅ ያድን ዘንድ አንድ ልጁን ወደ ዓለም ልኮአልና ፍቅሩን በዚህ አውቀናል” ይላል፡፡ እግዚአብሔር በልጁ መሥዋዕትነት ዓለምን ለማዳን ያደረገው ፍቅር ከሌላው ሁሉ የበለጠ በመሆኑ ልቆ ተነገረ እንጂ የእግዚአብሔር ፍቅር ከፍጡራን የተለየበት ጊዜ እንደሌለ ሁላችንም እናውቃለን፤ በስፋትም ልንገነዘብ ይገባልና፡፡” ብለዋል፡፡