የ፳፻፯(2007)ዓ/ም ዐብይ ጾምና በዓላቱ
ጥር 29 ቀን 2007 ዓ.ም.
የ2007 ዓ.ም. ዘመን አቆጣጠር በዓላትና አጽዋማትን በአዲሱ ዓመት መባቻ ማቅረባችን ይታወሳል፡፡ አሁን ያለንበት ወቅት የነነዌ ጾም አልፈን ዐብይ ጾምን የምንቀበልበት ወቅት በመሆኑ መረጃውን ለማስታወስ ይህንን ዝግጅት ያቀረብን ሲሆን የምትፈልጉትን ቀን ለማወቅ ከማኅበሩ ድረ ገጽ ላይ ያለውን የዘመን መቁጠሪያ በመቀያየር መጠቀም ትችላላችሁ፡፡

በሰሜን ጎንደር ሀገረ ስብከት በደምቢያ ወረዳ በጣና ሐይቅ ውስጥ በ1335 ዓ.ም. ተገድማ የነበረችው የጀበራ ማርያም አንድነት ገዳም ከፈረሰች ከበርካታ ዘመናት በኋላ ዳግም ለማቅናት ከፍተኛ ጥረት እያደረጉ የነበሩት አባ ገብረ ኢየሱስ ወልደ ኢየሱስ /አባ ዘወንጌል/ ጥር 20 ቀን 2007 ዓ.ም. በደረሰባቸው ድንገተኛ አደጋ ማረፋቸውን ከገዳሙ የደረሰን መረጃ ያመለክታል፡፡
የ2007 ዓ.ም. የከተራ በዓል ቅዱስ ፓትርያርኩ፤ ብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት፤ ሊቃውንተ ቤተ ክርስቲያን፤ በኢትዮጵያ የግብጽ አምባሳደር፤ የተለያዩ ሀገራት ዲፕሎማቶች፤ የየአድባራትና ገዳማት ሓላፊዎችና አገልጋዮች፤ የማኅበረ ቅዱሳን መዘምራን፤ የሰንበት ትምህርት ቤት መዘምራን፤ ምእመናንና ክብረ በዓሉን ለመከታተል ከውጭ ሀገር የመጡ ጎብኚዎች በተገኙበት በጃን ሜዳ በድምቀት ተከበረ፡፡
የከተራ በዓልን በማስመልከት በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ አብያተ ክርስቲያናት ዓውደ ምሕረትና ግቢ፤ ታቦታት በሚያልፉባቸው ጎዳናዎችና አደባባዮች ማኅበራትና ወጣቶች ተሰባስበው የተለያዩ ኅብረ ቀለማትን በመጠቀም በማስዋብ ላይ ይገኛሉ፡፡
በነቢያት የተነገረው ትንቢት በወንጌል የተጻፈው የጌታችን የመድኃኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስ በዓለ ጥምቀት ከተሥአቱ ከዘጠኙ ታላላቅ በዓላት አንዱ ነው፡፡ጥምቀት ተጠምቀ ተጠመቀ ካለው ግሥ የወጣ ሲሆን ጥምቀት ማለት በውሃ መጠመቅና በወራጅ ወንዝ በሐይቅ ውስጥ በምንጭ የሚፈጸም ነው:: በካህናት እጅ የሚፈጸመው ጥምቀት ከሌላው ጥምቀት ልዩ ነው::
ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአኵሱም ወዕጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት የ2007 ዓ.ም. የጌታችን የመድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የልደት በዓልን አስመልክቶ ለመላው ሕዝበ ክርስቲያን ታኅሣሥ 27 ቀን 2007 ዓ.ም. የእንኳን አደረሳችሁ መልእክት አስተላለፉ፡፡