Entries by Mahibere Kidusan

ሥርዓተ ቤተክርስቲያን

በሊቀ ካህናት ክንፈ ገብርኤል አልታዬ   ሥርዓት ማለት ‹‹ሠርዐ›› ሠራ ከሚለው የግእዝ ግስ የወጣ የምዕላድነት ዘር ያለው ስም ነው፡፡ ትርጉሙ ሕግ ደንብ አሠራር መርሐ ግብር ማለት ነው፡፡ ሙሉውን እዚህ በመጫን ያንብቡ

የክርስቲያን ፊደል- ኒቆዲሞስ

ጌታችን ወደዚህ ምድር መጥቶ የምስራቹን ቃል ሲያውጅ እስራኤላውያን የተቀበሉት በተደበላለቀ ስሜት ነበር፡፡ በአንድ በኩል ሕዝቡ ለብዙ ዘመናት በባርነት ሲገዛ ስለነበር ከሮማውያን ቅኝ ግዛት ነጻ የሚያወጣቸው መሲህ ይፈልጋሉ፡፡ በሌላ በኩል ደግሞ ሕዝቡ ለብዙ ዘመናት በባርነት ቀንበር ስለደከመ ተስፋ በመቁረጥ ተዳክሞ ነበር፡፡ መሲህ ቢመጣ እንኳ ይመጣል ብለው የሚጠብቁት ጦር ይዞ ሰራዊት አስከትሎ ነው ብለው ያምኑ ነበር፡፡ ስለዚህም ነው ክርስቶስን መሲህ ነኝ ብሎ ሲመጣ ለመቀበል ፈቃደኞች አልነበሩም፡፡ ምክንያቱ ደግሞ ጦር ሳይዝ ሰራዊት ሳያስከትል እንዲሁ ባዶ እጁን አርነት ላወጣችሁ መጥቻለሁ እያለ ደጋግሞ ተናግሯልና ነው፡፡ ምንም እንኳ አብዛኛው እስራኤላዊ የክርስቶስን መሲህነት ቢጠራጠርና ባይቀበለውም፣ በፍጹም እምነት እስከ መጨረሻው  የተከተሉትም  ነበሩ፡፡ ለዚህም  ትልቅ ማሳያ የሚሆነን ከፈሪሳውያን ወገን የሆነ ኒቆዲሞስ የተባለ አይሁዳዊ ነው፡፡ቅድስት ቤተክርስቲያንም ይህን  ታላቅ ሰው ለማዘከር የዐቢይን ጾም ሰባተኛ እሁድ በእርሱ ስም ሰይማ ታከብረዋለች ፡፡ ተከታዮቿ ምዕመናንም የእርሱን አሰረ ፍኖት እንዲከተሉ ትመክራለች ታስተምራለችም፡፡ 

ሌሎች መካነ ድሮች

ማኅበረ ቅዱሳን ህብር ሚዲያ መካነ ድር የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ-ክርስቲያን ጠቅላይ ቤተ-ክህነት ቅድስት ሥላሴ መንፈሳዊ ኮሌጅ አዲስ አበባ ማኅበረ ቅዱሳን አሜሪካ ማዕከል ማኅበረ ቅዱሳን ድምጸ-ተዋህዶ(አሜሪካ) ማኅበረ ቅዱሳን አውሮፓ ማዕከል ማኅበረ ቅዱሳን አውሮፓ ማዕከል ፓልቶክ የግብፅ ኦርቶዶክስ ቤተ-ክርስቲያን የግብፅ ኦርቶዶክስ ቤተ-ክርስቲያን መጽሐፍት 1 የግብፅ ኦርቶዶክስ ቤተ-ክርስቲያን መጽሐፍ Normal 0 false false false EN-US X-NONE TH MicrosoftInternetExplorer4 […]

ጸሎትና ጥቅሙ

             

ልጆች ትምህርት ጥሩ ነው?ቤተ ክርስቲያን እሑድ እሑድ ትሔዳላችሁ ? በጣም ጥሩ ልጆች ! ዛሬ የምንማማረው ስለ ጸሎት ጥቅም ነው፡፡ ጸሎት ማለት ከእግዚአብሔር የምንገናኝበት እግዚአብሔርን የምናመሰግንበት ትልቅ ኃይል ማለት ነው፡፡

ሥነ ፍጥረት

ልጆች የምንነግራችሁ ስለ ሥነ ፍጥረት ነው፡፡ እግዚአብሔር የሚታየውን ዓለም የፈጠረው በስድስት ቀናት ውስጥ ነው፡፡ ይህም በአንድ ቀን ለመፍጠር አቅም አጥቶ አይደለም፡፡ እርሱ ባወቀ ሁሉን በሥርዐትና በአግባቡ ለማድረግ ብሎ ነው እንጂ፡፡ ደግሞም ፈቃዱና ጊዜውም ስለሆነ ፍጥረታትን በስድስት ቀናት ውስጥ አከናወነ፡፡ 

ሀብዎሙ ዘይቤልዑ

የሚበሉትን ስጡአቸው(ክፍል አንድ)

በመ/ር አፈወርቅ ወ/አረጋዊ
ማቴ. 14.16

ከዓለም አስቀደሞ የነበረ በማእከለ ዘመን ያለ ዓለምን አሳልፎ ለዘለዓለም የሚኖር፣ ከሦስቱ አካላት አንዱ አካል እግዚአብሔር ወልድ ኢየሱስ ክርስቶስ የተናገረው ቃል ነው፡፡ የሰውን ልጅ ለማዳን ከወደቀበት ለማንሣት ወደቀደመ ክብሩም ለመመለስ ከንጽሕተ ንጹሐን ከቅድስተ ቅዱሳን እመቤታችን ድንግል ማርያም ከሥጋዋ ሥጋ ከነፍሷ ነፍስ ነሥቶ አምላክ ሰው ሆነ፡፡

ገብርሔር

በዲ/ን አባተ አስፋ
ዛሬ ታላቁን የጌታችንን ጾም ከጀመርን ስድስተኛ ሳምንት ላይ ደርሰናል፡፡ ይህን ሳምንት ቅድስት ቤተክርስቲያን «ገብርሔር» የሚል ስያሜ ሰጥታዋለች፡፡ ገብርሔር በጎ አገልጋይ ማለት ሲሆን የስያሜውን መነሻ የምናገኘው በዕለቱ ሥርዓተ ቅዳሴ ከሚነበበው የወንጌል ክፍል ማቴ.25-14-30 ነው፡፡

በዓለማችን የመጀመሪያ የሆነው የአባ እንጦንስ ገዳም በዐሥራ አራት ሚሊዮን ዶላር እድሳት ተደረገለት

ገዳሙ አንድ ሺሕ ስድስት መቶ ዓመታትን አስቆጥሯል

በሻምበል ጥላሁን

በዓለም የመጀመሪያው የምንኩስናና የገዳማውያን ኑሮ መሥራች የሆነው የአባ እንጦንስ ገዳም በግብፅ መንግሥት በዐሥራ አራት ሚሊዮን ዶላር ወጪ እድሳት ተደርጎለት ለአገልግሎት መዘጋጀቱን ቢቢሲ የካቲት 4 ቀን 2002 ዓ.ም ዘገበ፡፡ በግብፅ የሚገኘው የቅዱስ እንጦንስ ገዳም ከአንድ ሺሕ ስድስት መቶ ዓመት በላይ ዕድሜ ያለው ጥንታዊ ገዳም ነው፡፡