የሰሜን ወሎ ሀገረ ስብከት ያስገነባው ሕንፃ ተመረቀ
ዲ/ን ቴዎድሮስ ኃይሉ
• የብፁዕ አቡነ ቄርሎስ 25ኛ ዓመት የብር እዩቤልዩ በዓልም ተያይዞ ተከብሯል
{gallery count=1 width=350 height=300 counter=1 links=0 alignment=center animation=3000}abunekerilos{/gallery}
መልአከ ሐይል ስጦታው ሞላ በሰሜን ወሎ ሀገረ ስብከት የሰበካ ጉባኤ ማደራጃ ክፍል ኃላፊ የአዳጎ ሕንፃ መሠራቱ ቤተ ክርስቲያኒቱ በስብከተ ወንጌል የምታደርገውን እንቅስቃሴ በጉልህ የሚደግፍ ነው ብለዋል ፡፡ የወልድያ ከተማ ከንቲባ አቶ ሓየሎም ጣውዬ በምረቃው ወቅት ‹‹ የሰሜን ወሎ ሀገረ ስብከት ሕዝቡን በእምነቱ የጸና፣ ሀገር ወዳድና በልማት ዋነኛ ተሳታፊ ለማድረግ እያከናወናቸው ያለው አበረታች የልማት ተግባራት መንግሥት ከያዛቸው የድኅነት ማስወገጃ ስትራቴጂዎች አንፃር የሚሄዱ ለመሆናቸው ምስክርነት የሚያሻው ጉዳይ አይደለም፡፡ ሀገረ ስብከቱ ከጀመራቸው የልማት ሥራዎች መካከል የወልድያ ከተማችን የኢንቬስትመንት እድገት የሚያሠራውን አዳጎ ላይ የተገነባው ሕንፃ ለሌሎችም አርአያ ከመሆን አልፎ ለብዙ ዜጎች የሥራ ዕድል ፈጥሮ ያለፈና አሁንም እየፈጠረ ያለነው ቢባል መጋነን አይሆንም ›› በማለት መልእክታቸውን አስተላልፈዋል፡፡