Entries by Mahibere Kidusan

የትንሣኤ የቅዳሴ ምንባብ 4( ዮሐ.20፥1-19)

ከሳምንቱም በመጀመሪያዉ ቀን ማርያም መግደላዊት በማለዳ ገና ጨለማ ሳለ ወደ መቃብር መጣች፤ ድንጋዩንም ከመቃብሩ አፍ ተነሥቶ አገኘችው፡፡ ፈጥናም ወደ ስምዖን ጴጥሮስና ጌታችን ኢየሱስ ይወደው ወደ ነበረው ወደዚያ ወደ ሌላዉ ደቀ መዝሙር መጥታ፥ “ጌታዬን ከመቃብር ወስደውታል፤ ወዴትም እንደ ወሰዱት አላውቅም” አለቻቸው፡፡ ጴጥሮስና ያ ሌላዉ ደቀ መዝሙርም ወጥተው ወደ መቃብሩ ሄዱ፡፡ ሁለቱም በአንድነት ሲሮጡ ያ ሌላዉ ደቀ […]

የትንሣኤ የቅዳሴ ምንባብ 3( ሐዋ.2፥22-37)

“እናንተ የእስራኤል ሰዎች ሆይ፥ ይህን ነገር ስሙ፤ እንደምታውቁት በመካከላችሁ እግዚአብሔር በእጁ ባደረገው በከሃሊነቱ በተአምራቱና በድንቅ ሥራዎቹ እግዚአብሔር የገለጠላችሁን ሰው የናዝሬቱን ኢየሱስን ስሙ፡፡ እርሱንም በተወሰነው በእግዚአብሔር ምክርና በቀደመው ዕውቀቱ እናንተ አሳልፋችሁ በኃጥኣን እጅ ሰጣችሁት፤ ሰቅላችሁም ገደላችሁት፡፡ እግዚአብሔር ግን የሞትን ማሰሪያ ፈቶ ከሙታን ለይቶ አስነሣው፤ ሞት እርሱን ሊይዘው አይችልምና፡፡ ዳዊትም ስለ እርሱ እንዲህ አለ፡- እግዚአብሔርን ሁል ጊዜ በፊቴ አየዋለሁ፤ እንዳልታወክ በቀኜ ነውና፡፡ ስለዚህ ልቤን ደስ አለው፤ አንደበቴም ሐሤት አደረገ፤ ሥጋዬም ደግሞ በተስፋው አደረ፡፡ ነፍሴን በሲኦል አትተዋትምና፥ ጻድቅህንም ጥፋትን ያይ ዘንድ አትሰጠውምና፡፡ የሕይወትን መንገድ አሳየኸኝ፤ ከፊትህ ጋራ ደስታን አጠገብኸኝ፡፡

የትንሣኤ የቅዳሴ ምንባብ 2( 1ጴጥ.1፥1-13)

ከጌታችን ከኢየሱስ ክርስቶስ ሐዋርያ ከጴጥሮስ፥ በጳንጦስ፥ በገላትያና በቀጰዶቅያ፥ በእስያና በቢታንያ ሀገሮች ለተበተኑ ስደተኞች፥ እግዚአብሔር አስቀድሞ እንዳወቃቸው፥ በመንፈስ ቅዱስም እንደሚቀደሱ፥ ይታዘዙና በኢየሱስ ክርስቶስ ደም ይረጩ ዘንድ፥ ለተመረጡት፥ ጸጋና ሰላም ይብዛላችሁ፡፡
ኢየሱስ ክርስቶስ ከሙታን በመነሣቱ፥ ለሕያው ተስፋ እንደ ምሕረቱ ብዛት ሁለተኛ የወለደን የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ አባት እግዚአብሔር ይመስገን፡፡ የማያረጀውን፥ የማይለወጠውንና የማይጠፋውን፥ በሰማያት ለእኛና ለእናንተ ተጠብቆልን ያለውን ለመውረስ፥ በኋላ ዘመን በሃይማኖት ትገለጥ ዘንድ ለተዘጋጀችው ድኅነት በእግዚአብሔር ኀይል ለተጠበቃችሁት፥ እስከ ዘለዓለም ደስ ይላችኋል፤ ነገር ግን በሚመጣባችሁ ልዩ ልዩ መከራ አሁን ጥቂት ታዝናላችሁ፡፡ በእሳት ከአጠሩት ከጥሩ ወርቅ በሚመረጥ ሃይማኖታችሁ እንደምትቀበሉት መከራ መጠን ኢየሱስ ክርስቶስ በሚገለጥበት ጊዜ በክብር፥ በጌትነትና በምስጋና ትገኛላችሁ፡፡ እርሱም ሳታዩት የምትወዱት ነው፤ እስከ ዛሬም ድረስ አላያችሁትም፤ ነገር ግን ታምኑበታላችሁ፤ አሁንም ፍጻሜ በሌላትና በከበረች ደስታ ደስ ይላችኋል፡፡ በሃይማኖታችሁም ፍጹምነት የነፍሳችሁን ድኅነት ታገኛላችሁ፡፡

የትንሣኤ የቅዳሴ ምንባብ 1 (1ቆሮ. 15፥20-41)

አሁንም ክርስቶስ ከሞቱ ሰዎች ሁሉ አስቀድሞ ተነሥቶአል፡፡ በመጀመሪያው ሰው ሞት መጥቶአልና፥ በሁለተኛው ሰው ትንሳኤ ሙታን ሆነ፡፡ ሁሉ በአዳም እንደሚሞት እንዲሁ በክርስቶስ ሁሉ ሕያዋን ይሆናሉ፡፡ ነገር ግን ሰው ሁሉ በየሥርዐቱ ይነሣል፤ በመጀመሪያ ከሙታን የተነሣ ክርስቶስ ነው፤ ከዚያ በኋላ በክርስቶስ ያመኑ እርሱ በሚመጣበት ጊዜ ይነሣሉ፡፡ እግዚአብሔር አብ መንግሥቱን እጅ ባደረገ ጊዜ፥ ገዥም ሁሉ፥ ንጉሥም ሁሉ፥ ኀይልም ሁሉ […]

የትንሣኤ የማሕሌት ምንባብ 3 (ሉቃ.24፥1-13)

ከሳምንቱም በመጀመሪያዪቱ ቀን ያዘጋጁትን ሽቶ ይዘው እጅግ ማልደው ወደ መቃብሩ ሄዱ፤ ሌሎች ሴቶችም አብረዋቸው ነበሩ፡፡ ያቺንም ድንጋይ ከመቃብሩ ላይ ተንከባልላ አገኙአት፡፡ ገብተውም የጌታችን የኢየሱስን ሥጋ አላገኙም ስለዚህም ነገር የሚሉትን አጥተው ሲያደንቁ ሁለት ሰዎች ከፊታቸው ቆመው ታዩአቸው፤ ልብሳቸውም ያብረቀርቅ ነበር፡፡ ፈርተውም ፊታቸውን ወደ ምድር አቀረቀሩ፡፡ እነርሱም እንዲህ አሉአቸው፥ “ሕያዉን ከሙታን ጋር ለምን ትሹታላችሁ? በዚህ የለም፤ ተነሥቶአል፡፡ […]

ትንሣኤ /ለሕፃናት/

ሚያዝያ 6/2004 ዓ.ም.

በልያ አበበ

ልጆች መግደላዊት ማርያምን ታውቋታላችሁ? መግደላዊት ማርያም ጌታችን መድኀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ከፈወሳቸው ሕመምተኛ የነበሩ ሰዎች አንዷ ናት፡፡ ከነበረባት በሽታ ከዳነች ጊዜ ጀምሮ ጌታችን መድኀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የሚያስተምረውን ትምህርት በሙሉ የምትከታተል እና እርሱንም የምታገለግል ነበረች፡፡

የትንሣኤ የማሕሌት ምንባብ 2 (ማር.16፥1-ፍጻሜ )

ሰንበትም ባለፈች ጊዜ ማርያም መግደላዊት፥ የያዕቆብ እናት ማርያም፥ ሰሎሜም መጥተው ሥጋዉን ሊቀቡ ሽቱ ገዙ፡፡ በእሑድ ሰንበትም እጅግ ማልደው ፀሐይ በወጣ ጊዜ፥ ወደ መቃብር ሄዱ፡፡ እርስ በርሳቸውም፥ “ድንጋዪቱን ከመቃብሩ አፍ ላይ ማን ያነሣልናል?” አሉ፤ ድንጋዪቱ እጅግ ታላቅ ነበረችና፡፡ አሻቅበውም በተመለከቱ ጊዜ ደንጋዪቱ ተንከባልላ አዩ፡፡ ወደ መቃብሩም በገቡ ጊዜ አንድ ጎልማሳ ነጭ ልብስ ለብሶ በስተቀኝ ተቀምጦ አገኙና ደነገጡ፡፡ እርሱም እንዲህ አላቸው፥ “አትደንግጡ፤ የተሰቀለውን የናዝሬቱን ኢየሱስን ትሻላችሁን? ተነሥቶአል፤ በዚህስ የለም፤ የተቀበረበትም ቦታ እነሆ፡፡ ነገር ግን፥ ሂዱና ለደቀ መዛሙርቱና ለጴጥሮስም ወደ ገሊላ እንደሚቀድማቸው ንገሩቸው፤ እንደ ነገራቸውም በዚያ ያዩታል፡፡” ከመቃብርም ወጥተው ሸሹ፤ ፍርሀትና ድንጋጤ ይዞአቸዋልና፤ ስለፈሩም ለማንም አልተናገሩም፤ ያዘዛቸውንም ሁሉ ለጴጥሮስና ለወንድሞቹ ተናገሩ፡፡ ጌታችን ኢየሱስም ከሙታን ተለይቶ ከተነሣ በኋላ ተገለጠላቸውና፥ ለዘለዓለም ሕይወት የሚሆን የማይለወጥ ቅዱስ ወንጌልን ለፍጥረቱ ሁሉ ከምሥራቅ እስከ ምዕራብ ይሰብኩ ዘንድ ላካቸው፡፡
በእሑድ ሰንበትም ማለዳ ተነሥቶ ሰባት አጋንንትን ላወጣላት ለማርያም መግደላዊት አስቀድሞ ታያት፡፡

የትንሣኤ የማሕሌት ምንባብ 1 (ማቴ.28፥1-ፍጻሜ )

በሰንበትም ማታ ለእሑድ አጥቢያ ማርያም መግደላዊትና ሁለተኛዋ ማርያም መቃብሩን ሊያዩ መጡ፡፡ እነሆ፥ ታላቅ የምድር መናወጥ ሆነ፤ የእግዚአብሔር መልአክ ከሰማይ ወርዶአልና፤ ቀርቦም በመቃብሩ አፍ ላይ ድንጋይዋን አንከባሎ በላይዋ ተቀመጠ፡፡ መልአኩም እንደ መብረቅ፥ ልብሱም እንደ በረዶ ነጭ ነበረ፡፡ እርሱንም ከመፍራት የተነሣ መቃብሩን የሚጠብቁ ታወኩ፤ እንደ በድንም ሆኑ፡፡ መልአኩም መልሶ ሴቶችን እንዲህ አላቸው፤ “እናንተስ አትፍሩ፤ የተሰቀለውን ኢየሱስን እንደምትሹ አውቃለሁና፡፡ በዚህ የለም፤ እርሱ እንደ ተናገረው ተነሥቶአል፤ ነገር ግን ኑና ተቀብሮበት የነበረውን ቦታ እዩ፡፡ ፈጥናችሁም ሂዱና፡- ከሙታን ተለይቶ ተነሣ፤ እነሆ፥ ወደ ገሊላ ይቀድማችኋል፤ በዚያም ታዩታላችሁ፤ ብላችሁ ለደቀ መዛሙርቱ ንገሩአቸው፤ እነሆም፥ ነገርኋችሁ፡፡” በፍርሀትና በታላቅ ደስታም ከመቃብሩ ፈጥነው ሔዱ፤ ለደቀ መዛሙርቱም ይነግሩአቸው ዘንድ ሮጡ፡፡ እነሆም፥ ጌታችን ኢየሱስ አገኛቸውና፥ “ሰላም ለእናንተ ይሁን” አላቸው፤ እነርሱም ቀርበው እግሩን ይዘው ሰገዱለት፡ ከዚህም በኋላ ጌታችን ኢየሱስ እንዲህ አላቸው፥ “አትፍሩ ሒዱና ወደ ገሊላ እንዲሄዱ ለወንድሞቼ ንገሩአቸው፤ በዚያም ያዩኛል፡፡”

እጅግ የተከበሩ የዓለም ሎሬት ሜትር አርቲስት አፈወርቅ ተክሌ አረፉ

ሚያዝያ 04፣ 2004ዓ.ም

እንዳል ደምስ

ejig yetekeberu_yealemlorietእጅግ የተከበሩ የዓለም ሎሬት ሜትር አርቲስት አፈወርቅ ተክሌ ባደረባቸው ሕመም ምክንያት በህክምና ሲረዱ ቆይተው በተወለዱ በ80 ዓመታቸው ሚያዚያ 2/2004 ዓ.ም. ምሽት ላይ ከዚህ ዓለም በሞት ተለይተዋል፡፡ እጅግ የተከበሩ የዓለም ሎሬት አርቲስት አፈወርቅ ተክሌ ከአባታቸው ከአቶ ተክሌ ማሞ እና ከእናታቸው ከወ/ሮ ፈለቀች የማታወርቅ በጥቅምት ወር 1924 ዓ.ም. በአንኮበር ከተማ ተወልደዋል፡፡ የአንደኛ ደረጃ ትምህርታቸውን በአዲስ አበባ፣ እንዲሁም የከፍተኛ ትምህርታቸውን በእንግሊዝ አገር በሚገኘው የሥነ ጥበብ አካዳሚ በሥነ ስዕል በቅርፃ ቅርጽና በሥነ ሕንፃ ዲዛይን ተከታትለዋል፡፡