Entries by Mahibere Kidusan

«ኢትዮጵያ እጆቿን ወደ እግዚአብሔር ትዘረጋለች»መዝ፤ ፷፯፥፴፩

በሕይወት ሳልለው  ሀገራችን ኢትዮጵያ ክርስትናን ከተቀበሉት ቀደምት ሀገሮች አንዷ ናት፤ ነቢዩ ዳዊት በመዝሙር፤ ፷፯፥፴፩ ላይ «ኢትዮጵያ እጆቿን ወደ እግዚአብሔር ትዘረጋለች» ብሏል፡፡ ሊቀ ነቢያት ሙሴ ኢትዮጵያዊት ሴት ባገባበት ዘመን ኢትዮጵያ በሕገ ልቡና አምልኮተ እግዚአብሔርን ትፈጽም ነበር፤ የብሉይ ኪዳን እምነትና የሕገ ኦሪት ሥርዓት ደግሞ በንግሥተ ሳባ ዘመነ መንግሥት መጀመሩን መጽሐፍ ቅዱስ ያስተምረናል፡፡ ይህም የሆነው ንግሥተ ሳባ ስለ […]

የብፁዕ አቡነ ኤልሳዕ ህልፈተ ሕይወት

  ዲያቆን ዘአማኑዔል አንተነህ ብፁዕ አቡነ ኤልሳዕ በቀድሞው አጠራር በሰሜንና በጌምድር ጠቅላይ ግዛት በአሁኑ ደቡብ ጎንደር ዞን አስተዳደር በደራ ወረዳ አፈሯ እናት በመካነ ሰማዕት ቅዱስ ገላውዴዎስ ደብር ልዩ ስሙ አባ ጉንቸ እየተባለ በሚጠራው አካባቢ ከአባታቸው ከአቶ ፈንታ ወልድዬ ከእናታቸው ከእሙሐይ ጥዑምነሽ አብተው በ፲፱፻፳፯ ዓ/ም ግንቦት ፳፱ ቀን ተወለዱ፡፡ብፁዕነታቸው በአባታቸውና በእናታቸው በሥርዓትና እንክብካቤ ካደጉ በኋላ ዕድሜያቸው […]

ፊደል

ዲያቆን ዐቢይ ሙሉቀን ፊደል፤ ፈደለ፤ ጻፈ ከሚለው የግእዝ ቃል የተገኘ ሲሆን፤ ትርጉሙም የጽሕፈት ሁሉ መጀመሪያ፤ ምልክት፤ የመጽሐፍ ሁሉ መነሻ ማለት ነው፡፡ ኪዳነ ወልድ ክፍሌ ፊደል የሚለውን ቃል ሲተረጉሙ በቁሙ ልዩ፤ምርጥ ዘር፤ ቀለም፤ ምልክት፤ አምሳል፤ የድምጽና የቃል መልክ ሥዕል፤ መግለጫ፤ ማስታወቂያ፤ ዛቲ ፊደል፤ ሆህያተ ፊደል፤ ወዘተ በማለት ያብራሩታል፡፡ ካሕሳይ ገብረ እግዚአብሔር ሊቀ ሥልጣናት ሀብተ ማርያም ወርቅነህን […]

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የርክበ ካህናት ቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ በጸሎት ተከፈተ!

በሕይወት ሳልለው በዓመት ፪ ጊዜ የሚካሔደው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የርክበ ካህናት ቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ ግንቦት ፲፬ ቀን ፳፻፲፩ ዓ.ም. በጸሎት ተከፈተ! በአሁኑ ወቅት በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ላይ እየደረሰባት ያለውን ችግር ለመፍታት ከአሁን ቀደም ጸሎተ ምሕላው በአግባቡ ያልተካሔደ መሆኑን በመግለጫቸው ያሳወቁት ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ፓትርያክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀጳጳስ […]

ምስክርነት

ዲያቆን ዮሴፍ በቀለ በሐዋርያት ሥራ ምዕራፍ ፩ ቁጥር ፰ ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ለደቀ መዛሙርቱ የተናገራቸው ቃል «በኢየሩሳሌምና በይሁዳ ሁሉ፤ በሰማርያ እስከ ምድር ዳርቻ ድረስም ምስክሮቼ ትሆኑኛላችሁ» የሚል ነው፡፡ ይሁዳ ኢየሩሳሌምን የሚያጠቃልል ግዛት ነው፤በኢየሩሳሌም የጌታችን ተአምር የተፈጸመበት፤ ብዙ ሰው ስለ እርሱ የሰማበትም ከተማ ነው፡፡ ከኢየሩሳሌም ይልቅ በይሁዳ ስለ ክርስቶስ የሚያውቁም የሚሰሙም ዝቅተኛ ናቸው፡፡ ሌላው ሰማርያ […]

ከትንሣኤ እስከ ዳግም ትንሣኤ ያሉት ዕለታት ስያሜያቸውና ታሪካዊ አመጣጣቸው

ዲያቆን ተመስገን ዘገየ ከትንሣኤ ሌሊት ፩ ሰዓት ጀምሮ እስከ ዳግም ትንሣኤ ያለው ሳምንት የፉሲካ ምሥጢር የተገለጠበት፤ ከግብፅ ወደ ምድረርስት ከሲኦል ወደ ገነት መሻገርን የሚያመላክት ሳምንት ነው። ለፉሲካ የሚታረደውም በግ ፉሲካ ይባላል (ዘዳ. ፲፮÷፪:፭÷፮)፤ ፉሲካ ማለት ደግሞ ማለፍ ነው፤ ኢየሱስ ክርስቶስ የተሰቀለበትም ሳምንት የፉሲካ ሳምንት ነበር፤ (ሉቃ. ፳፪፥፲፬-፲፮፤ ዮሐ. ፲፰፥፴፰-፵)። እርሱም ንጹሕ የእግዚአብሔር በግ ሆኖ ደሙን […]

ሕያውን ከሙታን መካከል ስለምን ትፈልጋላችሁ? ሉቃ. ፳፬፥፭

ቀሲስ ሰሎሞን ወንድሙ በኦሪት ዘፀአት ፲፪፥፳፩-፳፰ እንደተጻፈው ይህ ዕለት በብሉይ ኪዳን ፋሲካ በመባል ይታወቃል፡፡ ትርጉሙም መሻገር ማለት ነው፤ ይህም ሕዝበ እሥራኤል ከግብጽ ባርነት ነጻ ወጥተው ወደ ምድረ ርስት የተሸጋገሩበት ዕለት ነው፤ በሐዲስ ኪዳን ደግሞ ትንሣኤ ይባላል፡፡ በዓለ ትንሣኤ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ሞትን በሞቱ ድል ነሥቶ ነጻነትን ለሰው ልጆች ሰጥቶ ከሞት ወደ ሕይወት፤ ከኀሳር ወደ ክብር […]

የጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ስቅለት

በተክለ አብ በጲላጦስ ዘመን ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ለሰው ልጅ በገባለት ቃል ኪዳን መሠረት፤ ትንቢቱም ይፈጸም ዘንድ መከራን ተቀበለ፤ ጲላጦስ በ፫ ሰዓት ይሰቅል ዘንድ ሲፈርድበትም፤ ‹‹መስቀሉንም ተሸክሞ በዕብራይስጥ ጎልጎታ ወደ ተባለው ቀራንዮ ወደሚባል ቦታ ወጣ›› (ዮሐ.፲፱፥፲፯) የራስ ቅል ስፍራ ቀራንዮ-ጎልጎታ አዳም ዐጽም የተቀበረበት ቦታ ነበር፡፡ በዚያም የአዳም መቃብር የሆነች ዋሻ አለች፤ የመስቀሉንም እንጨት በዚያ በምድር […]