ፍቅር ግን እርሱ ነው!
ፍቅር ግን ምንድነው? ብዬ ስጠይቀው
ሁሉም ሊያብራራልኝ ሊገልጸው አቃተው!
ፍቅር ግን እርሱ ነው
ኢየሱስ ክርስቶስ አምላክ ወሰብእ የሆነው
ራሱን በመስቀል ለእኛ ሲል የሰዋው!
This author has not written his bio yet.
But we are proud to say that Mahibere Kidusan contributed 814 entries already.
ፍቅር ግን ምንድነው? ብዬ ስጠይቀው
ሁሉም ሊያብራራልኝ ሊገልጸው አቃተው!
ፍቅር ግን እርሱ ነው
ኢየሱስ ክርስቶስ አምላክ ወሰብእ የሆነው
ራሱን በመስቀል ለእኛ ሲል የሰዋው!
መልእክተኛውም ሚክያስን ‹‹እነሆ ነቢያት ሁሉ በአንድ አፍ ሆነው ለንጉሡ መልካሙን ይናገራሉ፤ ቃልህም እንደ ቃላቸው እንዲሆን መልካም እንድትናገር እለምንሃለሁ›› ይለዋል፡፡ (፩ኛ ነገ.፳፪፥፲፫) ነቢዩ ግን ‹‹ሕያው እግዚአብሔርን! እግዚአብሔር የሚነግረኝን እርሱን እናገራለሁ›› አለው፡፡
በአርሲ ዞን አንዳንድ ወረዳዎች በኦርቶዶክሳውያን ላይ የሚፈጸመውን ጥቃት በጥብቅ እናወግዛለን፤ የጸጥታ ተቋማትም ጥቃቱን እንዲከላለሉ እንጠይቃለን።
የሁላችንም ሕይወት ትኩስ፣ ለብ ያለና በራድ ተብለው በሚገለጹ ሦስት ሁነቶች ውስጥ የሚገኝ ነው። ቅዱስ ዮሐንስ እነዚህን ሦስቱን የገለጸው ‹‹በራድ ወይም ትኩስ እንዳይደለህ ሥራህን አውቃለሁ፤ በራድ ወይም ትኩስ ብትሆንስ፣ መልካም ነበር፤ እንዲሁ ለብ ስላልህ፥ በራድም ወይም ትኩስ ስላልሆንህ ከአፌ ልተፋህ ነው›› በማለት ነበር፡፡ (ራእ.፫፥፲፭-፲፮)
ምስጋና ለሥሉስ ቅዱስ ይድረስና ሁልጊዜ በየዓመቱ በኅዳር ፳፬ ቀን እኛ የኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ምእመናን የካህናተ ሰማይ (ሱራፌ) በዓልን እንድናከብር አባቶች ሥርዓትን ሠርተውልናል፡፡
፭፻ ዓመታት ገደማ በእስራኤል ብዙ ገቢረ ተአምራትን ስታደርግ የነበረችዋ በሙሴ የተቀረጸች ታቦት በቀዳማዊ ምኒልክ በኩል ለኢትዮጵያ ተሰጠች።የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን በየዓመቱ ኅዳር ፳፩ ቀን በታላቅ ክብር ታከብረዋለች፡፡ካህናቱም ከዋዜማው ጀምረው በከበሮና በጸናጽል ስብሐተ እግዚአብሔር ያደርሳሉ፡፡በጽዮን ፊት እንደ የመዓርጋቸው ቆመው ‹‹እግትዋ ለጽዮን ወህቀፍዋ፤ ጽዮንን ክበቧት፥ በዙሪያዋም ተመላለሱ›› እያሉ ይዘምራሉ፡፡
የእግዚአብሔር ሰዎች ትክክለኛና እውነተኛ ሰዎች በመሆናቸው የተናገሩት ሁሉ የሚፈጸም ነው፡፡ በአንደኛ ሳሙኤል መጽሐፍ ላይ እንዲህ የሚል ቃል አለ፤ ‹‹…እነሆ አንድ የእግዚአብሔር ሰው በዚህች ከተማ አለ፤ እርሱም የተከበረ ሰው ነው፤ የሚናገረውም ሁሉ በእውነት ይፈጸማል …፡፡›› (፩ኛሳሙ.፱፥፮)
ከፀሐይ በታች ሁሉም እንደ ጥላ የሚያልፍ መሆኑን ጠቢቡ ሰሎሞን በመጽሐፈ መክብብ መጀመርያ ላይ ሲገልጽ ‹‹ሁሉም ነገር ከንቱ ነው›› ብሎ ተናገረ። ጠቢቡ ይህን ያለው በሕይወት ካየው እና ከተረዳው ነው። እርሱም በዚህ ምድር ላይ በዕውቀት፣ በጥበብ፣ በሀብትም ሆነ በሥልጣን የሚተካከለው እንዳልነበረ በመጽሐፈ ነገሥት ተጽፏል፡፡
ውድ የዚህ ጽሑፍ አንባብያን! እንደምን ሰነበታችሁ? ዘመነ ክረምቱን/ዘመነ ጽጌን እግዚአብሔር ረድቶን ብዙ ተምረንበት አልፏል፡፡ከፊታችን ኅዳር ፲፭ ቀን ጀምሮ እስከ ታኅሣሥ ፳፰/፳፱ ድረስ ደግሞ ዘመነ ነቢያትን የምንዘክርበት፣ ‹‹ጾመ ነቢያት›› ብለን ከጾም ጋር አገናኝተን ስለ ነቢያትና ነቢይነት፣ እንዲሁም ስለ ትንቢት ዓላማና ምክንያቱ ቤተ ክርስቲያን ብዙ የምታስተምርበት ወቅት ነው፡፡
ውድ የእግዚአብሔር ልጆች! እንዴት አላችሁ! መንፈሳዊ ሕይወት እንዴት ነው? በትምህርት ቤት፣ በሠፈር ውስጥ እንዲሁም በተለያየ ቦታ ስትገኙ በሥርዓት እና በአግባብ እንደምትኖሩ ተስፋችን እሙን ነው፤መልካም!!! ለዛሬ የምንነግራችሁ ስለ ቅዱሳን ነቢያት ነው፡፡