‹‹ጸሎታችሁ እንዳትሰናከል ሚስቶቻችሁን አክብሩ›› (፩ኛጴጥ.፫፥፯)
በትዳር ሕይወት ስንኖር ባል ራስ ነውና ሚስቶች ለባሎቻቸው እንዲገዙና እንዲታዘዙ ሲያዛቸው፣ ለባሎች የሰጠው ትእዛዝ ደግሞ ከዚህ የጸና ትእዛዝ ነው። ይኸውም የገዛ ሕይወቱን አሳልፎ እስኪሰጥላት ድረስ ጌታችን አምላካችን እና መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ቅድስት ቤተ ክርስቲያንን እንደወደዳት ባልም እንዲሁ ሚስቱን እንዲወዳት ጽኑዕ ትእዛዝን አዟል። ታዲያ ከመታዘዝና ከመገዛት ይልቅ ምን ያህል የሚጸና እንደሆነ ልናስተውለው ይገባል።