የስድስተኛው ፓትርያርክ ምርጫ ውሎ
የካቲት 21 ቀን 2005 ዓ.ም.
በእንዳለ ደምስስ

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ስድስተኛውን ፓትርያርክ ለመምረጥ በዛሬው ዕለት ከሌሊቱ 12፡00 ሰዓት ጀምሮ መራጮች የምርጫ ካርዳቸውን ይዘው በጠቅላይ ቤተ ክህነት የስብከተ ወንጌል አዳራሽ በመግባት ተጀመረ፡፡ ወደ አዳራሹ ሲገባ ከመድረኩ በስተግራና ቀኝ በምድብ ሀ እና ምድብ ለ በኩል የመራጮችን ዝርዝር የሚመዘግቡ አገልጋዮች መዝገቦቻቸውን ይዘው የተዘጋጀላቸውን ሥፍራ ይዘዋል፡፡ አጠገባቸው መራጮች የመራጭነት ካርዳቸውን ሲመልሱ የሚያኖሩባቸው ሁለት የታሸጉ ሳጥኖች ይታያሉ፡፡ በተወሰኑ ሜትሮች ርቀት ደግሞ መራጮች በምስጢር ድምፅ የሚሰጡበት የተከለለ ስፍራ ይገኛሉ፡፡ መራጮችም ቀስ በቀስ በመግባት በተዘጋጀላቸው ስፍራ ላይ ዐረፍ ብለዋል፡፡ የምርጫው ታዛቢዎች፤ ምርጫውን የሚያስፈጽሙ አገልጋዮች በተመደቡቡት የሥራ ድርሻ ሁሉም ዝግጅታቸውን አጠናቀው የምርጫውን መጀመር በጉጉት በመጠባበቅ ላይ ናቸው፡፡ አስመራጭ ኮሚቴውም ያዘጋጀውን ስለ አምስቱ እጩ ፓትርያርኮች ማንነት የሚገልጽ መጽሔት ለሁሉም እንዲሰራጭ ተደረገ፡፡
ከጠዋቱ አንድ ሰዓት ሲሆን የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ዐቃቤ መንበረ ፓትርያርክና የአርሲ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስን ጨምሮ ብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት ወደ አዳራሹ በማምራት በመድረኩ ላይ በተዘጋጀው ልዩ ስፍራ ላይ ዐረፍ ብለዋል፡፡ ከመድረኩ ወረድ ብሎም ከመራጮች ፊት ለፊት ሁለት ባለ መስታወት የምርጫ ሳጥኖች ይታያሉ፡፡
ከጠዋቱ አንድ ሰዓት በኋላ በዐቃቤ መንበረ ፓትርያርኩ ብፁዕ አቡነ ናትናኤል መሪነት ውዳሴ ማርያም፤ የኪዳን ጸሎትና ጸሎተ ወንጌል ከደረሰ በኋላ መራጮች በብፁዕ አቡነ እስጢፋኖስ የጅማ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስና የአስመራጭ ኮሚቴው ሰብሳቢ አማካይነት ቃለ መሐላ ፈጽመዋል፡፡ ወደ ምርጫው ከመገባቱ በፊትም ለመራጮች ተጨማሪ ግንዛቤ ለመስጠት በምርጫውና በአመራረጡ ዙሪያ ማብራሪያ ከአስመራጭ ኮሚቴው ተሰጥቷል፡፡
ብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳት፤ አስመራጭ ኮሚቴው የምርጫ ታዛቢዎች፤ መራጮች ባሉበት ሁለቱ የምርጫ ሳጥኖች እንዲታሸጉ ተደረገ፡፡ የምርጫ ሳጥኖቹ መታሸጋቸው ከተረጋገጠ በኋላ በቀጥታ ወደ ምርጫ ሥነ ሥርዓቱ የተገባ ሲሆን በቅድሚያ በመምረጥ ምርጫውን ያስጀመሩት ዐቃቤ መንበረ ፓትርያርኩ ብፁዕ አቡነ ናትናኤል ናቸው፡፡ በመቀጠልም ብፀዓን ሊቃነ ጳጳሳት፤ የመምሪያ ሓላፊዎች፤ የሀገረ ስብከት ሥራ አስኪያጆችና ሌሎችም በቅደም ተከተል መታወቂያቸውንና የምርጫ ካርዳቸውን በመያዝ ከመዝገባቸው ጋር በማመሳከር ከተረጋገጠ በኋላ የምርጫ ወረቀቱን በመውስድ በምስጢር ድምፅ ወደሚሰጡበት ቦታ በመግባት ወረቀቱን ለአራት በማጠፍ ፊት ለፊት ከሚገኙት የምርጫ ሳጥኖች ውስጥ በግልጽ በመጨመር የምርጫው ሥነ ሥርዓት ቀጠለ፡፡
የምርጫው ሥነ ሥርዓት እየተከናወነ ሳለ ከግብፅ ተወከወለው የመጡ በብፁዕ አቡነ ጳኩሚስ የቀድሞው የግብፅ አቃቤ መንበረ ፓትርያርክ የሚመራው አምስቱ ልዑካን ወደ አዳራሽ በመግባታቸው የምርጫው ሥነ ሥርዓት እንዲቆም በማድረግ አቀባበል ተደረገላቸው፡፡
ከግብፅ የመጡት አባቶችም፡- ብፁዕ አቡነ ጳኩሚስ፤ ብፁዕ አቡነ ቢሾይ፤ ብፁዕ አቡነ ሄድራ፤ ብፁዕ አቡነ ቢመን፤ እንዲሁም ብፁዕ አቡነ ሩፋኤል የግብፅ ኮፕቲክ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ጸሐፊ ሲሆኑ ምርጫውን ከማካሔዳቸው በፊት ብፁዕ አቡነ ጳኩሚስ ቃለ ምእዳን ሰጥተዋል፡፡ በሰጡት ቃለ ምእዳንም “የመጣነው ከኢትዮጵያውያን ወንድሞቻችን ጋር በአሉን ለማክበር ነው፡፡ ይዘን የመጣነው የግብፅ ቅዱሳንን ቡራኬ ነው፡፡ እኛ የቅዱስ ማርቆስ ቡራኬ ይዘን መጥተናል፤ ከኢትዮጵያ ደግሞ የጻድቁ አባት አቡነ ተክለ ሃይማኖትን ቡራኬ ይዘን እንሄዳለን፡፡ እኅት ለሆነችውም የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያንና ኢትዮጵያውያን ታላቅ ፍቅር አለን” በማለት ተናግረዋል፡፡ግብጻውያን ብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳት ምርጫውን በማከናወን ከተሸኙ በኋላ ምርጫው ቀጥሏል፡፡
የከስዓት በኋላውን ሥነ ሥርዓት እንደደረስ እናቀርብላችኋለን፡፡






የቀድሞው አባ ኅሩይ ወልደ ሰንበት የአሁኑ ብፁዕ አቡነ ኤልሳዕ በ1930 ዓ.ም ተወለዱ
ቆሞስ አባ ኀይለጊዮርጊስ ኀይለ ሚካኤል ይባላል፡፡ ፊደል የቆጠሩት፣ ዜማን የተማሩት፣ ቅኔን የተቀኙት በሀፋፍ ማርያም በኢቲሳ ደብረ ጽላልሽ ገዳም ነው፡፡ ቅዳሴን በዳግማዊ ምኒሊክ መታሰቢያ የቀሳውስት ማሠልጠኛ ት/ቤት ተምረዋል፡፡ በሰዋሰወ ብርሃን ቅዱስ ጳውሎስ መንፈሳዊ ት/ቤት ለ4 ዓመታት ተምረው በዲፕሎማ ተመርቀው ዘመናዊ ትምህርታቸውን እስከ 12ኛ ክፍል በማጠናቀቅ በምዕራብ ጀርመን እሸት ኬርከሌ መንፈሳዊ ት/ቤት ስለ ገዳማት አስተዳዳር አጥንተዋል፡፡
የቀድሞ ስማቸው መልአከ ምሕረት አባ ሀብተ ማርያም ይባላል፡፡ ግንቦት 7 ቀን 1946 ዓ.ም በደቡብ ወሎ አማራ ሳይንት ልዩ ስሙ ደብረ ብርሃን ለንጓጥ ሥላሴ ተወለዱ፡፡ አባታቸው ግራ ጌታ መኮንን ኀይሉ እናታቸው ወ/ሮ አታላይ ደርሰህ ይባላል፡፡ ዜማ፣ አቋቋም፣ ቅኔ፣ ፍትሐ ነገሥት ትርጓሜ ተምረዋል፤ የቅኔ መንገድ ከነአገባቡ ተምረው በመምህርነት ተመርቀዋል በ1956 ዓ.ም ከብፁዕ አቡነ ገብርኤል ዲቁና ተቀብለዋል፡፡
አቋቋም፣ ቅኔ ከነአገባቡ ቅዳሴ ኪዳን አንድምታ፣ ዜማ፣ ሠለስት፣ አርያም፣ ጾመ ድጓ፣ ቁም ዜማ ተምረዋል፡፡ በ1969 ዓ.ም ከብፁዕ አቡነ መቃርዮስ ዲቁና ተቀብለው ቅስና ከብፁዕ አቡነ ሳሙኤል ተቀብለዋል፡፡ በ1975 ዓ.ም በደብረ ዝቋላ አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ገዳም ሥርዓተ ምንኩስና ፈጽመዋል፡፡ በሰዋሰው ብርሃን ቅዱስ ጳውሎስ መንፈሳዊ ትምህርት ቤት ለ4 ዓመታት ያህል ተምረው በዲፕሎማ ተመርቀዋል፡፡ በሆላንድ ሆህ እስኩል የነገረ መለኮት ትምህርት ቤት ገብተው ለ4 ዓመታት ተምረው የመጀመሪያ ዲግሪ ተቀብለዋል፡፡
ዛሬ ከስዓት በኋላ በቅዱስ ሲኖዶስ የመሰብሰቢያ አዳራሽ ብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት፤ የአስመራጭ ኮሚቴ አባላት፣ እንዲሁም ከልዩ ልዩ የሚዲያ አካላት የተወከሉ ጋዜጠኞች በተገኙበት በተሰጠው መግለጫ ላይ፡-ብፁዕ አቡነ ማትያስ በኢየሩሳሌም የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ገዳማት ሊቀ ጳጳስ፣ ብፁዕ አቡነ ኤልሳዕ የሰሜን ጎንደር ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ፣ ብፁዕ አቡነ ዮሴፍ የባሌ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ፣ ብፁዕ አቡነ ሕዝቅኤል የቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ጸሐፊ የምዕራብና ደቡብ አዲስ አበባ የከፋ ሸካ ቤንች ማጂ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ፣ ብፁዕ አቡነ ማቴዎስ የወላይታና ዳውሮ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ለፓትርያርክነት እጩ ሆነው መቅረባቸው ተገልጧል፡፡

ከ2003 ዓ.ም. ጀምሮ በደብረ ጽጌ ቅድስት ማርያም ገዳም፤ በፍቼ ቅዱስ ጴጥሮስ ቤተ ክርስቲያን፤ እንዲሁም በበኬ ቅድስት ማርያም ቤተ ክርስቲያን የሐዊረ ሕይወት መርሐ ግብር መካሄዱ የሚታወስ ሲሆን ምእመናን ከወዲሁ ትኬቱን በብር 120፡00 /አንድ መቶ ሃያ/ በመግዛት በጉዞው እንዲሳተፉ የማኅበሩ ምክትል ዋና ጸሐፊና የጉዞው አዘጋጅ ኮሚቴ ሰብሳቢ አቶ ግርማ ተሾመ ጥሪያቸውን አስተላልፈዋል፡፡

