በኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ/በሰ/ት/ቤቶች ማ/መምሪያ -  ማኅበረ ቅዱሳን
  • ቀዳሚ ገጽ
  • ስለ ማኅበሩ
    • ማእከላት
      • ሰሜን አሜሪካ
      • አውሮፓ
      • ሩቅ ምሥራቅ
      • ደቡባዊ አፍሪካ
      • የካናዳ ማእከል
      • አዲስ አበባ ማእከል
        • የወርሃዊ አስተዋጽኦ መሰብሰቢያ
    • ኅትመት እና ሚዲያ
      • ሐመር እና ስምዐ ጽድቅ
      • ማኅበረ ቅዱሳን ቲቪ
      • የማኅበረ ቅዱሳን ዩቲዉብ
      • መጽሔተ ተልዕኮ
      • ማእከለ ሥዕላት
        • ካሜራው ምን ይላል
        • የቅዱሳት ሥዕላት ማኅደር
  • ትምህርቶች
    • የርቀት ትምህርት
    • ስብከት
    • መሠረታዊ የቤተ ክርስቲያን ትምህርቶች
  • ግቢ ጉባኤ
  • ሌሎች ድረ ገጾች
    • በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን መንበረ ፓትርያርክ የብፁዕ ወቅዱስ ልዩ ጽ/ቤት ድረ ገጽ
    • በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ድረ ገጽ
    • በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ሰንበት ት/ቤቶች ማደራጃ መምሪያ ድረ ገጽ
  • ቋንቋ
    • አማርኛ
    • ትግርኛ
    • ወላይትኛ
    • ሲዳምኛ
    • Affan Oromo
    • English
  • ያግኙን
  • Click to open the search input field Click to open the search input field Search
  • Menu Menu

ጥምቀት

You are here: Home1 / ምሥጢራተ ቤተ ክርስቲያን2 / ጥምቀት

ጥምቀት

ጥር ፱ ቀን ፳፻፲፬ ዓ.ም

የሰው ልጅ ሕገ እግዚአብሔርን በመተላለፉና ለኃጢአት ተገዢ በመሆኑ ንጽሕት ነፍሱ አደፈች፤ ረከሰችም፤ በኃጢአቱም ምክንያት ከአምላኩ ተጣላ፤ ወደ ምድርም ተጣለ፤ ምድርም በእርሱ የተነሣ ተረገመች፤ እሾህና አሜከላንም አበቀለች፡፡ እርሱም ለብዙ ዘመን አዝኖና በሥቃይ ኖረ፡፡

ቸርነቱ የማይልቅ መሐሪና ይቅር ባይ አምላካችን እግዚአብሔር በኅዘኑ አዝኖና ሥቃዩን ተመልክቶ ለእርሱ፤ ስለ እርሱ መከራና ሥቃይ ይቀበልለት ዘንድ ከንጽሕት ቅድስት ድንግል ማርያም ተወልዶ ሊያድነው በገባለት ቃል መሠረት ተፈጸመ፡፡ ከዚያም በኋላ ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ዮርዳኖስን ብርህት ማኅፀን እንድትሆን፣ ምእመናንም ከአብራከ መንፈስ ቅዱስ፣ ከማኅፀነ ዮርዳኖስ ዳግም ተወልደው መንግሥተ ሰማያት እንዲገቡ  እንደዚሁም ሥርዓተ ጥምቀትን ለማስተማርና አብነት ለመሆን በጥር ዐሥራ አንድ ቀን ተጠምቋልና ይህችን የተከበረች ቀን ሕዝበ ክርስቲያን ያከብር ዘንድ ይገባል፡፡

በመጽሐፍ ቅዱስም ‹‹ጥሩ ውኃንም እረጭባችኋለሁ፤ እናንተም ከርኵሰታችሁ ሁሉ ትጠራላችሁ›› ተብሎ አስቀድሞ በተነገረው መሠረት ጌታችን በውኃ ተጠመቀ፡፡ የዚህም ምክንያት ሊቀውንተ ቤተ ክርስቲያን እንደሚያስረዱት ውኃ ለሁሉ አስፈላጊ በመሆኑና ያለ ውኃ መኖር የሚችል ባለመሆኑ ያለ ጥምቅት ደግሞ ያለ ጥምቀት ወደ እግዚአብሔር መንግሥት መግባት አይቻልምና ጥምቀትም ለሁሉም የሚገባ ሥርዓት ነው፡፡ ከዚህም ባሻገር ውኃ መልክ ያሳያል፤ መልክ ያለመልማል (ያጠራል)፡፡ ጥምቀትም መልክዐ ነፍስን ያሳያል፤ መልክዐ ነፍስን ያለመልማልና (ያጠራልና)፡፡ (ሕዝ.፴፮፥፳፭)

በዘመነ ሥጋዌ ‹‹ጌታችን  መድኃኒታችን  ኢየሱስ  ክርስቶስ  በዮሐንስ  እጅ  ይጠመቅ  ዘንድ  ከገሊላ  ወደ ዮርዳኖስ መጣ›› (ማቴ.፫፥፲፫፣ማር.፩፥፱፣ሉቃ.፫፥፳፩፣ዮሐ.፩፥፴፪)፡፡ መጥምቀ መለኮት ቅዱስ ዮሐንስ ግን አገልጋይ በጌታው እጅ ይጠመቃል እንጂ ጌታ በአገልጋዩ አይጠመቅም፤ ‹‹እኔ በእንተ ልጠመቅ እሻለሁ፤ አንተ ወደ እኔ ትመጣለህን?›› ብሎ አይሆንም አለው፡፡ ጌታችን ኢየሱስም መልሶ ‹‹አሁንስ ተው፤ እንዲህ ጽድቅን ሁሉ ልንፈጽም ይገባናልና›› አለው፡፡ ከዚህም በኋላ ተወው፡ ጌታችን ኢየሱስም ከተጠመቀ በኋላ ወዲያው ከውኃ ወጣ፤ እነሆ ሰማይም ተከፈተለት፤ የእግዚአብሔርም መንፈስ በርግብ አምሳል ወርዶ በራሱ ላይ ሲቀመጥ አየ፤ እነሆም ‹‹በእርሱ ደስ የሚለኝ የምወደው ልጄ ይህ ነው››የሚል ድምጽ ተሰማ፡፡(ማቴ.፫፥፲፫-፲፯)

መንፈስ ቅዱስ በርግብ አምሳል መውረዱም ምሥጢር አለው፡፡ ርግብ ኃዳጊተ በቀል ናት፤ መንፈስ ቅዱስም ኃዳጌ በቀል ነውና፡፡ ርግብ በኖኅ ጊዜ ‹‹ሐጸ ማየ አይኅ ነትገ ማየ አይኅ፤ የጥፋት ውኀ ጎደለ›› ስትል ቆጽለ ዕፀ ዘይት ይዛ ተገኝታለች፡፡ መንፈስ ቅዱስም ተስፋ መስቀልን ያበሥራልና፡፡

እኛም የሐዲስ ኪዳን ሕዝቦች ይህን ምሥጢር በመረዳት፣ መከራ መስቀሉን በመሸከምና እምነት በመጽናት እንድኖንር አስፈላጊ በመሆኑ ነገረ ድኅነቱን በመረዳት በልደቱ እንደዘከርነው ሁሉ በጥምቀቱም እንዲሁ እናደረግ ዘንድ ይገባል፡፡

ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የተጠመቀውም በሠላሳ ዓመቱ ነው (ሉቃ. ፫፥፳፫)፡፡ በሠላሳ ዓመቱ የተጠመቀበት ምሥጢርም አዳም የሠላሳ ዓመት፤ ሔዋን የዐሥራ አምስት ዓመት ሰው ሆነው ተፈጥረው አዳም በዐርባ ቀን፣ ሔዋን በሰማንያ ቀን ከሥላሴ የተቀበሉትን ልጅነት በምክረ ከይሲ ዕፀ በለስን በልተው አስወስደው ነበረና በሠላሳ ዓመቱ ተጠምቆ መልሶላቸዋል፡፡ በሠላሳ ዓመት የመጠመቁ ምሥጢር ይህ ሲሆን እኛ ዛሬ ወንዶች በዐርባ ቀን፣ ሴቶች በሰማንያ ቀን በዕለተ ዓርብ ከቀኝ ጎኑ በፈሰሰው ማየ ገቦ ተጠምቀን ከአብራከ መንፈስ ቅዱስ ከማኅፀነ ዮርዳኖስ ሁለተኛ የምንወለድበት ምክንያትም አዳም በዐርባ ቀኑ፣ ሔዋን በሰማንያ ቀኗ ከሥላሴ ያገኙትን ልጅነት መሠረት በማድረግ ነው /ኩፋ. ፬፥፱/፡፡ የምንጠመቀውም በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም ነው፡፡  ‹‹ወእንዘ ታጠምቅመው በሉ በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ፤ ስታጠምቋቸውም በአብ በወልድና በመንፈስ ቅዱስ ስም አጥምቋቸው፤›› እንዲል(ማቴ. ፳፰፥፲፱)፡፡

በአሁኑ ጊዜም ታቦታቱን ወደ ጥምቀተ ባሕር በማውረድ በዓለ ጥምቀቱን ለሚያከብሩ ክርስቲያኖች በሙሉ ከታቦታቱ ሁለት ሺህ ክንድ ርቀው መከተል እንዲገባቸው በመጽሐፍ ቅዱስ እንዲህ ተብሎ ተገልጿል፤ ‹‹ሕዝቡን የአምላካችሁን የእግዚአብሔርን ቃል ኪዳን ታቦት ሌዋውያን ካህናት ተሸክመውት ባያችሁ ጊዜ ከሠፈራችሁ ተነሥታችሁ ተከተሉት፡፡ በእናንተና በታቦቱ መካከል ያለው ርቀት በስፍር ሁለት ሺህ ክንድ ይሁን፡፡ በዚህ መንገድ በፊት አልሄዳችሁበትና፤ የምትሄዱበትን መንገድ እንድታውቁ ወደ ታቦቱ አቅርቡ፡፡›› (ኢያ.፫፥፩-፲፯)

ታቦታቱ ወደ ጥምቀተ ባሕር ወርደው ለማደራቸው መነሻ ይህ ትምህርት ነው፡፡ የጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በዓለ ጥምቀትም ከተጠመቀበት ከ፴ ዓመተ ምሕረት ጀምሮ እስከ ዓለም ፍጻሜ ድረስ በየዓመቱ ጥር ፲፩ ቀን ሃይማኖታዊ ሥርዓቱን በጠበቀ መልኩ ሲከበር ይኖራል፡፡

ከበዓለ ጥምቀቱ ረድኤት፣ በረከት ይክፈለን፡፡

በፌስቡክ የትስስር ገጽ ያግኙን

Search Search

አዳዲስ ጽሑፎች

  • አብርሃም ርእየ ፫ተ እደወ፤ በዛቲ ዕለት ምሥጢረ ሥላሴ ዜነወ።
  • በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን!
  • ቅዱስ ዮሐንስ መጥምቅ
  • ዘመነ ክረምት
  • “መሠረተ ሃይማኖት” የተባለ የልጆች መጽሐፍ የፊታችን እሑድ እንደሚመረቅ የስብከተ ወንጌል እና ሐዋርያዊ አገልግሎት ገለጸ
  • ደብረ ማርቆስ ማእከል 252 የግቢ ጉባኤ ተማሪዎችን አስመረቀ።
  • በዘንድሮው ዓመት ባሕር ዳር ዩኒቨርስቲ ካዘጋጃቸው 18 ሜዳሊያ ዋንጫውን ጨምሮ 14ቱ በግቢ ጉባኤያት ተማሪዎች የተወሰዱ መሆናቸው ተገለጸ
  • የግቢ ጉባኤ አባል (CGPA) 4.00 ነጥብ በማምጣት የዓመቱ የዋንጫ እና የወርቅ ሜዳሊያ ተሸላሚ ሆነ።
  • ማኅበረ ቅዱሳን እያስገነባ የሚገኘውን የልህቀት ማእከል የመጀመሪያ ዙር የፊኒሺንግ ሥራ ለማከናወን የገንዘብና የዐይነት ድጋፍ ማሰባሰብ መጀመሩን አስታወቀ
  • እንኳን ለእናታችን ለእመቤታችን ለቅድስተ ቅዱሳን ለድንግል ማርያም ሰኔ ጐልጐታና ሕንጸተ ቤተ ክርስቲያን (ለመጀመሪያ ጊዜ ቤተ ክርስቲያኗ ለታነጸበት) ክብረ በዓል በሰላምና በጤና አደረሰን አደረሳችሁ፡፡
  • የእንጅባራ ማእከል ላለፉት 4 ዓመታት ሲያስተምራቸው የቆዩ 200 ተማሪዎችን  አስመረቀ
  • ማኅበረ ቅዱሳን በመተከል ዞን ዳንጉር ወረዳ ለሚገኙ ተፈናቃዮች  አስቸኳይ የምግብ ግብዓቶች ድጋፍ አደረገ
  • የአዲስ አበባ ማእከል 500 የግቢ ጉባኤ ተማሪዎች መመረቃቸውን ገለጸ።
  • የወላይታ ሶዶ ማእከል ለ8 ወራት ያስተማራቸውን 45 የበገና ዘማርያንን አስመረቀ።
  •    ‘’ከመላእክት አለቆች አንዱ የሆነው ሚካኤል ሊረዳኝ መጣ።’’ (ት.ዳን. ፲ ፥፱)

የጽሑፎች ማውጫ – በወራት

© Mahibere Kidusan - All Rights Reserved. Website by MK-IT
  • Link to Facebook
Link to: በዓለ ጥምቀት Link to: በዓለ ጥምቀት በዓለ ጥምቀት Link to: ‹‹በገሊላ አውራጃ በቃና መንደር ሠርግ ሆነ፤ ውኃውንም ወደ ወይንነት ለወጠው›› (ዮሐ. ፪፥፩-፲፩) Link to: ‹‹በገሊላ አውራጃ በቃና መንደር ሠርግ ሆነ፤ ውኃውንም ወደ ወይንነት ለወጠው›› (ዮሐ. ፪፥፩-፲፩) ‹‹በገሊላ አውራጃ በቃና መንደር ሠርግ ሆነ፤ ውኃውንም...
Scroll to top