ሥራህን ሥራ

በሁዳዱ መሬት መልካም በሚያፈራው

ሠራተኛው ጥቂት መኸሩ ብዙ ነው

የእርሻው ጦም ማደር አንተን አስጨንቆህ

ከወጣህ ልትሠራ ወገብህን ታጥቀህ

አንተ ! . . . ጎበዝ . . .  ደስ ይበልህ

የደረቀ መሬት  . . .  አለስልሰህ ዘርተህ

የአበባው  ጊዜ  አልፎ . . . ፍሬውን ታያለህ

በስራህ በርትተህ . . . ፀሐይ ብትጠልቅም ምሽቱ ቢነጋ

ሰነፍ ቢያንጓጥጥህ በነገር ቢተጋ

መልስ ለመመለስ . . . ወደ ኋላ አትዙር . . . በከንቱ አትድከም

ማሳው እንዳይጠፋ  . . . እንዳይበላው አረም

የተዘራው ፍሬ ሠላሳ እና ስልሳ መቶ እንዲያፈራ

የተሰጠኸውን . . . ሥራ ብቻ ሥራ