መሠዊያው

በመዝሙርና ኪነ ጥበባት ክፍል 

የካቲት ፳፰፤፳፻፲፭ ዓመተ ምሕረት

በእስራኤል ምድር በሰማርያ ላይ አክዓብ ነገሠ

ጣዖትን አቆመ …መለከትን ነፋ …ለበኣል ደገሠ

የቤተ መቅደሱ መሠዊያው ፈረሰ

የእግዚአብሔር ካህናት ደማቸው ፈሰሰ

የኤልዛቤልን ምክር የአክዓብን ክፋት አምላክ አይቷልና

ቴስብያዊው ኤልያስ ወጣ በጎዳና

ለምድር በረከት እንዳይሰጥ ደመና

ዝናብ ከለከለ ስለ እግዚአብሔር ቀና፡፡

ለሦስት ዓመታቶች ምድር ጠል ሳታይ

በቃል ብቻ ጸና ተገዝቶ ሰማይ

በሰማርያ ላይ …ሰቆቃው በረታ

ርሐቡ ከፋ …ቤታቸው ተፈታ፡፡

ለሥነ ፍጥረቱ እግዚአብሔር እራራ

ከደብረ ቄርሜሎስ ኤልያስ ተጣራ

እግዚአብሔርን ትተው ለበኣል ያደሩ

፬፻፶ ነቢያተ ሐሰት በአንድ ላይ መከሩ

ነቢያተ ሐሰት መሥዋዕት ዘርግተው …“በኣል ሆይ” እያሉ

ከጧት እስከ ቀትር በታላቅ ቃል ሰጮኹ

መጣች ከሰማያት እሳትም ወረደች

የሚቃጠለውን መሦዋዕቱን፣ እንጨቱንም…

….ድንጋዩንም በላች

የጉድጓዱን ውኃ አፈሩንም ላሰች

ሕዝቡም ይህን ዓይተው …

…በኤልያስ አምላክ አምነው ተደነቁ

ነቢያተ ሐሰት በሰይፍ ወደቁ

የእግዚአብሔር እጁ በኤልያስ ታየች

ምሕረት ቸርነቱ ጠል ሁና ወረደች፡፡