መንፈሳዊነት
ኦርቶዶክሳዊነት ርትዕት ሃይማኖት፣ ጽኑ እምነት፣ መልካም ምግባርና መንፈሳዊ እውቀት በአንድነት የተዋሐዱበት፤ አርአያ እግዚአብሔርን አጽንቶ በሐዋርያዊ የሕይወት ተጋድሎ እግዚአብሔርን በግብር ወደ መምሰል የሚታደግበት ፍጹም ሰማያዊ ሕይወት በመሆኑ፤ አባላት በየትኛውም ቦታ፣ ጊዜና ሁኔታ በማሰብ፣ በመናገር እና በመሥራት/በተግባር በሚገለጽ ክርስቲያናዊ ሥነ ምግባር ታንጸው፣ ፍኖተ አበውን ተከትለው፣ በታማኝነት እና በፈሪሐ እግዚአብሔር ቤተ ክርስቲያንን በቅንነት ያገለግላሉ::




በተለያዩ ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ትምህርታቸውን ሲከታተሉ የቆዩ የግቢ ጉባኤ ተማሪዎች መመረቃቸው ተገለጸ።
በማኅበረ ቅዱሳን አዲስ አበባ ማእከል ግቢ ጉባኤያት አገልግሎት ዋና ክፍል ሰአሊተ ምሕረት ማስተባበሪያ አድማስ ግቢ ጉባኤ፣ ሎርካን ግቢ ጉባኤ፣ ቅዱስ ገብርኤል ማስተባበሪያና ደቡብ ማስተባበሪያ አድማስ ግቢ ጉባኤ ቃሊቲ ካምፓስና መካኒሳ ካምፓስ፣ ኪውንስ ግቢ ጉባኤ፣ ንፋስ ስልክ ፓሊ ቴክኒክ ግቢ ጉባኤ፣ ሪፍት ቫሊ ግቢ ጉባኤ ሲያስተምራቸው የነበሩ የግቢ ጉባኤ ተማሪዎችን ሐምሌ 11 እና 12 ቀን 2018 […]
ማኅበረ ቅዱሳን በተለያዩ ቋንቋዎች የመዝሙር አልበሞችን በማዘጋጀት ተደራሽ እያደረገ እንደሚገኝ ገለጸ
በማኅበረ ቅዱሳን የዜማና ኪነ ጥበባት ማእከል ምእመናን በሚሰሙት ቋንቋ መዝሙራትን በማዘጋጀት ስብከተ ወንጌልን ለማስፋፋት በተለያዩ ቋንቋዎች የመዝሙር አልበሞችን አዘጋጅቶ ተደራሽ እያደረገ እንደሚገኝ ገልጿል። በዚህም በዘንድሮው ዓመት ከያዘው ዕቅድ መካከል ከዚህ በፊት በ2017 ዓ.ም ቀረጻ የተከናወነላቸውን አዊኛ፣ ቡርጅኛ፣ባይሶኛና ሞስዬኛ ቋንቋዎችን የቅንብር ሥራ በመሥራት የማሰራጨትና አዳዲስ ቀረጻዎችን በኽምጣጞ(ኽምጠኛ)፣ በሐዲይሳ፣ በማሌኛ፣ በትግርኛ(የበገና) ቋንቋዎች ቀረጻ በማከናወን እንዲሁም በሐዲይሳ፣ ማሌኛና […]
ቅዱስ ዮሐንስ መጥምቅ
በቀሲስ ኃይሉ ብርሃኑ ሰኔ ፴ በዚች ዕለት ነቢይ ሰማዕትና ሐዋርያ የሆነ መጥምቁ ዮሐንስ ተወለደ። ዮሐንስ ማለት እግዚአብሔር ጸጋ ነው ማለት ነው፡፡ትርጓሜ ወንጌልም መጥምቀ መለኮት ዮሐንስን ፍሥሐ ወሐሴት (ተድላናደስታ) ይለዋል ፤ወላጆቹ በእርሱ መወለድ ተደስተዋልና /ሉቃ.፩፥፲፬/፡፡በቅዱስ ወንጌል እንደ ተጻፈ ሄሮድስ የመድኀኒታችን የክርስቶስን መወለድ ከሰብአ ሰገል ሲሰማ መንግሥቴን ይወስድብኛል ብሎ ስለሠጋ ጌታችንን ያገኘሁ መስሎት የቤተልሔም ሕፃናትን መግደል ጀመረ/ማቴ.፪፥፩-፲፮/፡፡ […]
ዘመነ ክረምት
እንኳን አደረሳችሁ!!! ክፍል አንድ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን አስተምህሮ ወቅቶች በአራት ይከፈላሉ፡፡ በቅዱስ ያሬድ የዜማ መጻሕፍት፣ በመጽሐፈ ግጻዌ እንደ ተገለጸው እነዚህም፡- ዘመነ መጸው (መከር)፣ ዘመነ ሐጋይ (በጋ)፣ ዘመነ ጸደይ (በልግ) እና ዘመነ ክረምት ይባላሉ፡፡ ከላይ ላሉት አራቱ ወቅቶች አራት መጋብያነ ከዋክብት አሏቸው። እነሱም ፦ ፩) ምልክኤል___መጋቢት 26- ሰኔ 25 ፪) […]
“መሠረተ ሃይማኖት” የተባለ የልጆች መጽሐፍ የፊታችን እሑድ እንደሚመረቅ የስብከተ ወንጌል እና ሐዋርያዊ አገልግሎት ገለጸ
የስብከተ ወንጌል እና ሐዋርያዊ አገልግሎትን በስፋት ተደራሽ ለማድረግ የሚውል “መሠረተ ሃይማኖት” በሚል ርእስ የተዘጋጀ የልጆች መጽሐፍ ሰኔ 28 ቀን 2018 ዓ.ም በማኅበሩ ሕንጻ 3ኛ ወለል ንቡረ ዕድ ድሜጥሮስ አዳራሽ እንደሚመረቅ በማኅበረ ቅዱሳን የስብከተ ወንጌል እና ሐዋርያዊ አገልግሎት ዳይሬክተር ዲ/ን ሙሉጌታ ነጋ ገልጸዋል። መጽሐፉ በዲ/ን ማርኤል ሽመልስ የተዘጋጀ ሲሆን የክርስትና መሠረተ እምነት የሆኑትን አምስቱን አዕማደ ምሥጢራት […]
ደብረ ማርቆስ ማእከል 252 የግቢ ጉባኤ ተማሪዎችን አስመረቀ።
በማኅበረ ቅዱሳን የደብረ ማርቆስ ማእከል ግቢ ጉባኤያት አገልግሎት ዋና ክፍል ለ4 ዓመታት በደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ እንድማጣ ገነተ ኢየሱስ ዋናው ግቢ 150 እና ጤና ካምፓስ የመቃ አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ቤተ ክርስቲያን 102 በድምሩ 252 ተማሪዎችን ካህናት አባቶች፣ የማእከሉ የሥራ አስፈጻሚ አባላትና የተመራቂ ቤተሰቦች በተገኙበት ሰኔ 21 ቀን 2018 ዓ.ም አስመረቋል። በመርሐ ግብሩ ለተመራቂ ተማሪዎች የእንኳን […]
በዘንድሮው ዓመት ባሕር ዳር ዩኒቨርስቲ ካዘጋጃቸው 18 ሜዳሊያ ዋንጫውን ጨምሮ 14ቱ በግቢ ጉባኤያት ተማሪዎች የተወሰዱ መሆናቸው ተገለጸ
በማኅበረ ቅዱሳን የባሕር ዳር ማእከል በ7 የተለያዩ ግቢ ጉባኤያት ያስተማራቸውን 1,073 የግቢ ጉባኤያት ተማሪዎችን ሰኔ 21 ቀን 2018 ዓ.ም የአድባራት እና ገዳማት አስተዳዳሪዎች፣ ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች እና የተመራቂ ቤተሰቦች በተገኙበት በፔዳ ግቢ ጉባኤ የስብከተ ወንጌል አዳራሽ አስመርቋል። አቶ ብርሃኑ አሳሳ በማኅበረ ቅዱሳን የባሕር ዳር ማእከል ምክትል ሰብሳቢ በምረቃ መርሐ ግብሩ ላይ ተገኝተው የማእከሉን የእንኳን ደስ […]
የግቢ ጉባኤ አባል (CGPA) 4.00 ነጥብ በማምጣት የዓመቱ የዋንጫ እና የወርቅ ሜዳሊያ ተሸላሚ ሆነ።
በማኅበረ ቅዱሳን ባሌ ሮቤ ማእከል የጎባ ወረዳ ማእከል በመደ ወላቡ ዩኒቨርሲቲ የጎባ ሪፈራል ሆስፒታል ግቢ ጉባኤ 82 ተማሪዎች በጎባ ደብረ ሰላም ቅዱስ ዑራኤል ቤተ ክርስቲያን ሰኔ 21 ቀን 2018 ዓ.ም በአባቶች ቡራኬ አሰመርቋል። ከተመረቁት ተማሪዎች መካከል በግቢ ጉባኤው በሥራ አሰፈጻሚነት ሲያገለግል የነበረው ተማሪ ቶልቻ ከበደ በነርሲንግ የትምህርት መስክ ከ39 ኮርሶች 25ቱን ‘A+’ እና ቀሪውን ‘A’ […]
ማኅበረ ቅዱሳን እያስገነባ የሚገኘውን የልህቀት ማእከል የመጀመሪያ ዙር የፊኒሺንግ ሥራ ለማከናወን የገንዘብና የዐይነት ድጋፍ ማሰባሰብ መጀመሩን አስታወቀ
ማኅበረ ቅዱሳን ባለፉት 34 ዓመታት በርካታ መንፈሳዊ አገልግሎቶችን በስብከተ ወንጌል፣ በገዳማትና በአብነት ትምህርት ቤቶች፣ በጥናትና ምርምር፣ በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት (የዩንቨርስቲ/ኮሌጅ) ኦርቶዶክሳውያን ተማሪዎችን በማስተማር፣ 24 ሰዓታት የሚዲያ አገልግሎት በመስጠት፣ በመዝሙርና በኪነ ጥበባት፣ በሙያ፣ በማኅበራዊና በኢኮኖሚያዊ ዘርፍ እንዲሁም ሌሎች አገልግሎቶችን እያከናወነ ይገኛል። ይህን አገልግሎት በስፋት ተደራሽ ለማድረግ የልህቀት ማእከል እያስገነባ እንደሚገኝ በማኅበረ ቅዱሳን የልህቀት ማእከሉ ግንባታ ዐቢይ […]
የእንጅባራ ማእከል ላለፉት 4 ዓመታት ሲያስተምራቸው የቆዩ 200 ተማሪዎችን አስመረቀ
በማኅበረ ቅዱሳን የእንጅባራ ማእከል የግቢ ጉባኤ ማስተባበሪያ ዋና ክፍል ለአራት ተከታታይ ዓመታት በሐመረ ኖኅ ቅድስት ኪዳነምሕረት ቤተ ክርስቲያን በመደበኛ እና በኤክስቴንሽን መርሐ ግብር ሲያስተምራቸው የነበሩ 200 የእንጅባራ ዩኒቨርስቲ ተማሪዎችን አስመርቋል። ከተመራቂ ተመሪዎች መካከል አንድ የዋንጫ፣ 11 የሜዳልያ እና 12 የማዕረግ ሰርተፍኬት ተሸላሚዎች የሚገኙበት ሲሆን የዋንጫ እና የሁለት ሜዳልያ ተሸላሚው ዲ/ን አላምራው ዋጋው ከወሰደው 55 ኮርሶች […]