መንፈሳዊነት
ኦርቶዶክሳዊነት ርትዕት ሃይማኖት፣ ጽኑ እምነት፣ መልካም ምግባርና መንፈሳዊ እውቀት በአንድነት የተዋሐዱበት፤ አርአያ እግዚአብሔርን አጽንቶ በሐዋርያዊ የሕይወት ተጋድሎ እግዚአብሔርን በግብር ወደ መምሰል የሚታደግበት ፍጹም ሰማያዊ ሕይወት በመሆኑ፤ አባላት በየትኛውም ቦታ፣ ጊዜና ሁኔታ በማሰብ፣ በመናገር እና በመሥራት/በተግባር በሚገለጽ ክርስቲያናዊ ሥነ ምግባር ታንጸው፣ ፍኖተ አበውን ተከትለው፣ በታማኝነት እና በፈሪሐ እግዚአብሔር ቤተ ክርስቲያንን በቅንነት ያገለግላሉ::
ከሰላም የምታደርሰንን መንገድ እንያዝ
ብዙዎቻችን ስለ ሰላም እንናገራለን እንጂ ሰላም በውስጣችን አለመኖሩን የሚያሳዩ ተግባራትን ስንፈጽም እንታያለን፡፡ ሰላም የምንሻ ከሆነ ሰላማውያን ከመሆን በተጨማሪ ሌሎችም ሰላማውያን እንዲሆኑ የምንችለውን ሁሉ ማድረግ ይኖርብናል፡፡ ከጥፋት ልንድን ብቻ ሳይሆን ሌሎችን ከጥፋት ልንታደግ እንደሚገባ “ወንድሞቻችን ሆይ ከእናንተ ከጽድቅ የሳተ ቢኖር ከኃጢአቱ የመለሰውም ቢኖር ኃጢአተኛውን ከተሳሳተበት መንገድ የሚመልሰው ራሱን ከሞት እንዳዳነ ብዙ ኃጢአቱንም እንደአስተሰረየ ይወቅ” (ያዕ. […]
“መከራ ልትቀበሉ እንጂ በስሙ ልታምኑ ብቻ አልተጠራችሁም” (ፊል. ፩፥፳፱)
ዘመናችን መረጃ በፍጥነት የሚለዋወጥበት፣ ስላሙ ሲደፈርስ ደቂቃ የማይፈጅበት እየሆነ መጥቷል፡፡ ሰዎች ሞትን ለመሸሽ የማያደርጉት ጥረት የለም፡፡ ኃያላን ሰማይ ጠቀስ ፎቆች፣ የኤሌክትሪክ አጥር፣ የድኅንነት ካሜራ እያዘጋጁ ወንጀልንና ወንጀለኞችን ለመቆጣጠር ቢሞክሩም አልተሳካላቸውም፡፡ መንገዳቸው ሥጋዊ ፍላጎትን የተከተለ በመሆኑ መፍትሔ ማሰገኘት አልቻለም፡፡ ችግሩ የሚፈታው ሁልጊዜ ችግርን ወደ ሌላ በመጠቆም አለመሆኑን መረዳት ይገባል፡፡ ምዕራባውያን የአዳጊ ሀገሮችን ቅርስና መዋዕለ ንዋይ […]
“ከእንግዲህ በኋላ አብያተ ክርስቲያናትን ማቃጠልና ክርስቲያኖችን በጭካኔ መግደል በዝምታ አይታይም” ብፁዕ ሥራ አስኪያጅ
በካሣሁን ለምለሙ በአንዳንድ የሀገራችን ክፍሎች በተለየ መልኩ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ አብያተ ክርስቲያናት ላይ ያነጣጠረ ቃጠሎ፣ ዝርፊያ፣ እንዲሁም በክርስቲያኖች ላይ የሚካሔደው ጭካኔ የተሞላበት ግድያ ከእንግዲህ በኋላ በዝምታ ሊታይ እንደማይገባ የጠቅላይ ቤተ ክህነት ሥራ አስኪያጁ ብፁዕ አቡነ ዲዮስቆሮስ ገለጡ፡፡ ለሀገር ብዙ ዋጋ በከፈለችው ቅድስት ቤተ ክርስቲያንና በአማኞቿ ላይ ለበርካታ ዓመታት አረመናዊ ድርጊት በተደጋጋሚ ሲፈጸም ቆይቷል፡፡ እምነትን […]
መስጠትና መቀበል (ሐዋ፳፥፴፭)
[…]
በአሜሪካ የዲሲ ንዑስ ማእከል አቡነ ጎርጎርዮስ ትምህርት ቤት ተማሪዎችን አስመረቀ
ከአሜሪካ ማእከል በማኅበረ ቅዱሳን በአሜሪካ የዲሲ ንዑስ ማእከል አቡነ ጎርጎርዮስ ትምህርት ቤት ነሐሴ ፲፪ ቀን ፳፻፲ ዓ.ም ለሰባት ወራት ያስተማራቸውን 64 ተማሪዎችን የተማሪ ወላጆችና የማኅበሩ አመራር አባላት በተገኙበት በሜሪላንድ ግዛት አስመረቀ፡፡ በምረቃው መርሐ ግብር ላይ የትምህርት ቤቱ አስተባባሪ ዲ/ን ሙሉጌታ ኃይለ ማርያም የማኅበሩን መልእክትና የአቡነ ጎርጎርዮስ ትምህርት ቤትን የ፳፻፲ ዓ.ም ሪፖርት አቅርበዋል፡፡ ዲ/ን ሙሉጌታ ኃይለ […]
አባቶቻችን ለዕርቅ አርአያ በመሆናቸው ዘመኑን ዋጅተዋል
ማስታረቅና ማስማማት ከሰላም መሪ የሚገኝ አርአያነት ያለው ተግባር ነው ይቅር ማለትም እንደዚሁ፡፡ በዓለም ላይ ተቈጥረው የማያልቁ ጦርነቶች ቢካሔዱም ለጊዜው የተሸነፈ የመሰለው ጊዜ እስከሚያገኝ አድፍጦ እንዲቆይ ማድረግ ቻለ እንጂ አማናዊ ሰላም ማምጣት አልቻለም፡፡ አንዱ ሌላውን ሲወር፣ አንዱ ሌላውን ሲያስገብር ኖሯል፡፡ አባቶቻችን ዘመኑን ሲዋጁ የኖሩት ዕርቅ በማድረግ የተለያዩትን በማስማማት ነው፡፡ የጦርነት ውጤቱ ቂምና በቀል ሲሆን የዕርቅ […]
“ሰላምን ሻት ተከተላትም”(መዝ.፴፫፥፲፬)
በመ/ር ኃይለ ሚካኤል ብርሃኑ ሰላም ማለት ጸጥታ፣ ዕረፍት፣ እርጋታ፣ እርካታ ማለት ሲሆን የእርስ በእርስ ስምምነት በአንድነት አብሮ መኖር መቻልና የዕረፍት ስሜት እንደሆነ የመጽሐፍ ቅዱስ መዝገበ ቃላት ያስረዳል፡፡ነቢየ እግዚአብሔር ቅዱስ ዳዊት “ሰላምን ሻት ተከተላትም” ብሎ ከመናገሩ አስቀድሞ የመጽሐፉን ክፍል ወደ ኋላ መለስ ብለን የተነሳንበትን ኃይለ ቃል ሙሉ አሳቡን ለመረዳት ስንመለከተው እንዲህ የሚል ቃል እናገኛለን፡፡ “ልጆቼ ኑ […]
የ፳፻፲፩ ዓ.ም የአጽዋማት ባሕረ ሐሳባዊ ቀመር
በዲ/ን ታደለ ሲሳይ በዘመናት ሁሉ የነበረው ያለውና የሚኖረው፣ ሁሉን የፈጠረ በሁሉም ያለ እግዚአብሔር ብቻ ነው፡፡ ለእርሱ በዚህን ጊዜ መኖር ጀመረ፣ በዚህን ጊዜ መኖር ያቆማል የማይባልለት የህልውናው መጀመሪያም ሆነ መጨረሻ የሌለው ዘለዓለማዊ ነው፡ “ተራሮች ሳይወለዱ ምድርም ዓለምም ሳይሠሩ ከዘላለም እስከ ዘለዓለም ድረስ አንተ ነህ”፡፡ “ኢየሱስም እውነት እውነት እላችኋለሁ አብርሃም ሳይወለድ እኔ አለሁ አላቸው፡፡”፣ ብሏል፡፡ በተጨማሪም፣ “ኢየሱስ […]
በኢትዮጵያ ሱማሌ ክልል በተከሰተው ችግር ከማኅበረ ቅዱሳን የተሰጠ መግለጫ!
እንግዲያስ ሰላም የሚቆምበትን እርስ በርሳችንም የምንታነጽበትን እንከተል /ሮሜ 14፥19/ ። በሀገራችን በኢትዮጵያ የሚካሔደውን የመንግሥት የአሠራር ለውጥ ተከትሎ ላለፉት ጥቂት […]
ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን በኢትዮጵያ ሶማሌ ክልል በተፈጠረው ችግር የተሰጠ መግለጫ
Betekihenet megelecha