• እንኳን በደኅና መጡ !

ዜናዎች፣ ወቅታዊ ክንውኖች እና ልዩ ልዩ ይዘቶች

ዐቢይ ጾም

ዐቢይ ጾም ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶሰ ከተጠመቀ በኋላ ዐርባ ቀን የጾመው፤ እኛም እንድንጾማቸው በቤተ ክርስቲያናችን ከታዘዝናቸው ሰባቱ የአዋጅ አጽዋማት አንዱ ነው፡፡ ምእመናን ጌታችን ያደረገውን ምሳሌ ተከትለን ጾሙን በየዓመቱ እንጾመዋለን፡፡ ዐቢይ ጾም ስምንት ሳምንታት (፶፭ ቀኖች) አሉት፡፡ በውስጡ ስምንት ቅዳሜዎች፣ ሰባት እሑዶች ይገኛሉ፡፡ ይኸውም ዐሥራ አምስት ቀን ማለት ነው፡፡ እነዚህ ቀናት ከጥሉላት እንጂ ከእህል ውኃ ስለማይጦሙ የጦሙ ወራት ዐርባ ቀን ብቻ ይሆናል፡፡

‹‹ለተቀበሉት ሁሉ ግን÷ በስሙ ለሚያምኑት ለእነርሱ የእግዚአብሔር ልጆች ይሆኑ ዘንድ ሥልጣንን ሰጣቸው›› (ዮሐ. ፩፥፲፪)

የክርስቶስ አካል እንደመሆናችን መጠን ደግሞ ይህን ኃላፊነት በተለያየ መልኩ በሕይወታችን ልንተገብር እንደሚገባ መረዳት ያስፈልጋል፡፡ ክርስቲያኖች ከአምላካቸው የተቀበሉትን ትእዛዝ መፈጸምም አለባቸው፡፡ ወላጆች ልጆቻቸውን በልጅነት ጥምቀት በማስጠመቅ፣ በቤተ ክርስቲያን ሥርዓት በማሳደግ እና ሥርዓተ አምልኮቱን እንዲፈጽሙ በመርዳት ማሳደግ አለባቸው፡፡ ይህንንም መጀመር ያለባቸው ልጆቹ ሰባት ዓመት ሲሞላቸው እንደሆነ የቤተ ክርስቲያን አስተምህሮ ላይ ተጠቅሷል፡፡

በኢትየጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ላይ እየደረሰ ያለውን ወቅታዊ ችግር አስመልክቶ ከቅዱስ ሲኖዶስ የተሰጠ መግለጫ

ልጆችሽ

ቅድስት ማርያም (ባለሽቶዋ) እንተ ዕረፍት

ጌታችንም በስምዖን ቤት እንደ ግብፃውያን አቀማመጥ እግሩን ወደኋላ አድርጎ ነበር፤ አንድም ወንበሩ እንደ አፍርንጆች ወንበር እግር ወደኋላ የሚያደርግ ነው፤(ወንጌል ቅዱስ) እርሷም ከአጠገቡ ስትደርስ ከእግሩ በታች ከሰገደች በኋላ ‹‹በስተኋላውም በእግሩ አጠገብ ቆማ እያለቀሰች በእንባዋ እግሩን ታርስ ጀመረች፤ በራስ ጠጉሯም ታብሰው፣ እግሩንም ትስመው፣ ሽቱም ትቀባው ነበረች፡፡›› (ሉቃ.፯፥፴፰-፴፱)

ሶርያዊው ቅዱስ ኤፍሬም

በኢትዮጵያ ቤተክርስቲያን የረጅም ዘመን ሐዋርያዊ ጉዞ ላይ በጎ ተፅዕኖ ካላቸው የአራተኛው መቶ ክፍለ ዘመን አባቶች መካከል አንዱ ሶርያዊው ቅዱስ ኤፍሬም ነው፡፡ ይህ አባት ምንም እንኳን በቋንቋ ውሱንነትና በቦታ ርቀት በርካቶች ሥራዎቹና ጽሑፎቹ የታወቁለት ባይሆንም ሕይወቱን በብሕትውና የመራ የትርጓሜ መጻሕፍትን፣ የቅኔ፣ የግጥምና የወግ ጽሑፍ በማዘጋጀት የኖረ አባት ነው፡፡

ጾመ ሰብአ ነነዌ

‹‹ጾመ ሰብአ ነነዌ፤ የነነዌ ሰዎች ጾም›› የሦስት ቀን ጾም የጾሙት በነነዌ ይኖሩ የነበሩ ሰዎች ናቸው፡፡ ከተማዋም (ነነዌ) በጤግሮስ ወንዝ ዳርቻ የምትገኝ ስትኾን መሥራቿም ናምሩድ ነው (ዘፍ.፲፥፲፩-፲፪)፡፡ ጥንታዊቷ የነነዌ ከተማ ለአሦር መነሻ የሆነች፤ እጅግ ሰፊና ያማረች፤ የቅጥሯ ርዝመትም ፲፪ ኪሎ ሜትር የሚሸፈን ነበር፡፡ በከተማዋ ንጉሡ ሰናክሬም ብዙ ሕንጻዎችን ገንብቶ ነበር (ዮናስ ፬፥፲፩)፡፡

የኢትዮጵያውያን ቅዱሳት አንስት አርአያነት

የቅዱሳት አንስት ገድል እንደ አርአያና ምሳሌ ሆኖ ለብዙ ምእመናን ትምህርት ሊሆን የሚችል ታሪክ ነው። የእነዚህም አንስት ተጋድሎ እንደየዘመናቱ ቢለያይም ለሕዝቡ ካለው ሚና አንጻር ሁሌም አስፈላጊነቱ የላቀ ነው፡፡

ሥርዓተ ንባብ

ውድ አንባብያን በአለፈው ትምህርታችን ከምንባቡ ላይ ተነሽ ንባባትን እንድትጽፉ መልመጃ መስጠታችን ይታወቃል። እንደሠራችሁትም ተስፋ እናደርጋለን። ለማረጋገጥ ያህል ምንባቡንና መልሱን እንደሚከተለው እናቀርባለን።

‹‹ጊዜ ዕረፍታ ለሶልያና››

እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም በምድር ላይ በአይሁድ ክፋት ብዙ መከራና ኃዘንን ካሳለፈች በኋላ በዘመነ ሉቃስ ጥር ሃያ አንድ ቀን በስድሳ አራት ዓመቷ ወደ ዘለዓለም ደስታ ትገባ ዘንድ ዐርፋለች፡፡

በፌስቡክ የትስስር ገጽ ያግኙን

ስለ ማኅበረ ቅዱሳን መሰረታዊ መረጃዎች

ስያሜ

ማኅበረ ቅዱሳን እግዚአብሔር ያከበራቸው የነቢያት፣ የሐዋርያት፣ የጻድቃንና የሰማዕታት በአጠቃላይ የቅዱሳን ገድል፣ ትሩፋትና አማላጅነት የሚዘከርበት በመሆኑ ‹‹ማኅበረ ቅዱሳን›› የሚል ስያሜውን አግኝቷል፡፡

የማኅበሩ ርእይ

ቤተ ክርስቲያን ሁለንተናዊ የመሪነት ሚናዋን ስትወጣ ማየት

ተልእኮ

ለቤተ ክርስቲያን ተልእኮ መሳካት እና ለሕልውናዋ የሚተጋ፣ የተደራጀ ፣ ምሉዕ ኦርቶዶክሳዊ፤ ርቱዕ ዘመናዊ፤ ሁለገብ መሪ ትውልድ ማፍራት እና ማሰማራት

እሴቶች

  • መንፈሳዊነት

    ኦርቶዶክሳዊነት ርትዕት ሃይማኖት፣ ጽኑ እምነት፣ መልካም ምግባርና መንፈሳዊ እውቀት በአንድነት የተዋሐዱበት፤ አርአያ እግዚአብሔርን አጽንቶ በሐዋርያዊ የሕይወት ተጋድሎ እግዚአብሔርን በግብር ወደ መምሰል የሚታደግበት ፍጹም ሰማያዊ ሕይወት በመሆኑ፤ አባላት በየትኛውም ቦታ፣ ጊዜና ሁኔታ በማሰብ፣ በመናገር እና በመሥራት/በተግባር በሚገለጽ ክርስቲያናዊ ሥነ ምግባር ታንጸው፣ ፍኖተ አበውን ተከትለው፣ በታማኝነት እና በፈሪሐ እግዚአብሔር ቤተ ክርስቲያንን በቅንነት ያገለግላሉ::
  • አገልጋይነት

    የማኅበሩ አባላት አገልግሎትን የክርስቲያናዊ ሕይወታቸው መገለጫ አድርገው በመቀበል በበጎ ፈቃድ ሰማያዊውን ክብርና ጸጋ በመሻት፣ ምድራዊ ክብርና ውዳሴ ከንቱን ሳይፈልጉ፣ በትሕትና እና በክርስቲያናዊ ፍቅር በታማኝነት ያገለግላሉ::
  • የሐሳብ መሪነት

    ማኅበሩ ለቤተ ክርስቲያን ዘላቂ አገልግሎት የሚያስፈልጉ፣ ኦርቶዶክሳዊ እሳቤን የተከተሉና ዘመኑን የዋጁ የመሪነት ሐሳቦችን በማፍለቅ ከሚመለከታቸው የቤተ ክርስቲያን መሪዎች ጋር በመመካከር ይሠራል::
  • ተባባሪነት

    ማኅበሩ የቤተ ክርስቲያን አገልግሎት የሁሉም የቤተ ክርስትያን አካላት የወል ተግባር ነው ብሎ ያምናል:: በመሆኑም እንደየጉዳዩ አግባብነት ካላቸው ባለ ድርሻ እና አጋር አካላት ጋር በመግባባት፣ በመመካከር እና በቅንነት ለተልእኮ አንድነት ብዝኃ ጸጋን በማክበር አብሮ ይሠራል::
  • ሙያ አክባሪነት

    የማኅበሩ አባላት ባላቸው ልዩ ልዩ ሙያ /ዕውቀት/ ቤተ ክርስቲያንን ለማገልገል የተሰባሰቡ በመሆናቸው፣ በማኅበሩ አሠራሮች ሁሉ ከኦርቶዶክሳዊው ትምህርተ ሃይማኖት ጋር በማይጋጩ በእውነተኛ መረጃ ለሚደገፉ ሙያዊ ምክረ ሐሳቦች ተገቢውን ክብርና ቅድሚያ ይሰጣል:: በቤተ ክርስቲያንም ለመንፈሳዊ እና ለዘመናዊው (አስኳላ) ሙያ ተገቢው ክብር እንዲሰጥ ይሠራል::
  • ምክንያታዊ ሞጋችነት

    ማኅበሩ በእውነተኛ መረጃ ላይ ተመሥርቶ ቤተ ክርስቲያንን ከውስጥም ሆነ ከውጭ የሚፈትኑ አስተሳሰቦችን፣ አሠራሮችን፣ ልማዶችን እና ትርክቶችን በግልጽና በመንፈሳዊ ጥብዓት እና በእውነት እንዲሞገቱና መፍትሔ ላይ እንዲደረስ ይሠራል::
  • ተጠያቂነት

    የማኅበሩ አገልግሎት ግብ ሰማያዊ ዋጋ ማግኘት ስለሆነ ኀላፊነትን በአግባቡ አለመወጣት በእግዚአብሔር እና በሰዎች ዘንድ የሚያስጠይቅ በመሆኑ በየትኛውም እርከን ላይ ያለ አባል እና አመራር በማኅበሩ አሠራር መሠረት በተሰጠው ኀላፊነት ተጠያቂ ይሆናል፡፡

ዓላማዎች

  • የቤተ ክርስቲያን ተቋማዊ አስተዳደር፣ የአሠራር ሥርዐትና አስተሳሰብ፣ በቴክኖሎጂ እና በልዩ ልዩ መንገዶች በመደገፍ ዘመኑን ለዋጀ ጠንካራ አገልግሎት ማብቃት፤
  • የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ተማሪዎችን ሙሉ ሰብእናን የሚገነባ ሥርዐተ ትምህርት በማስተማር ዘመኑን የዋጁ ምሉዕ ኦርቶዶክሳዊ የሆኑ በቤተ ክርስቲያን አስተዳደራዊ መዋቅር የሚያገለግሉ እንዲሁም በማኅበራዊ፣ በኢኮኖሚያዊ በፖለቲካዊ እና በሀገር አስተዳደር ጉዳዮች መሪ/ንቁ ተሳታፊ አገልጋዮችን ማፍራት እና ማሠማራት፤
  • የተተኪውን ትውልድ ምንጭ ለማጎልበት የሰ/ት/ቤቶችን አቅም በማጠናከር የሕጻናት እና የወጣቶችን የተተኪነት ሚና ማሳደግ፤
  • ኦርቶዶክሳዊ መንፈሳዊነትን በተግባር የሚገልጽ ቤተሰብ እና አንድነቱን የጠበቀ ኦርቶዶክሳዊ ማኅበረሰብ በመገንባት የተደራጀ እና የተናበበ አገልግሎት መስጠት፤
  • በተደራጀ እና ተደራሹን ማእከል ባደረገ መንገድ ስብከተ ወንጌልንና ሐዋርያዊ ተልእኮን ዘርፈ ብዙ በሆኑ መንገዶች በመላው ዓለም ማስፋፋት፤
  • በቤተ ክርስቲያን ላይ የሚነዙትን የርእዮተ ዓለም፣ የሐሰት ትርክቶች እና የአጽራረ ቤተ ክርስቲያንን እንቅስቃሴ ጥናት እና ምርምር ላይ ተመርኩዞ መሞገት እና የተሳሳቱትን በማረም፣ በጠንካራ የዕቅበተ እምነት አገልግሎት የቤተ ክርስቲያንን ሕልውና ማስጠበቅ፤
  • በተመረጡ ገዳማት እና አብነት ትምህርት ቤቶች የልኅቀት ማእከል እና የተለየ ክርስቲያናዊ ተልእኮ የሚፈጽሙ እንዲሆኑ የሚያስችል ሁለገብ የአእምሮ ልማት ድጋፍ ማድረግ፤
  • ማኅበሩ ዘመኑን የዋጀ ተቋማዊ የአሠራር ሥርዓት በመዘርጋት ተልእኮውን ማሳካት የሚችልበት አቅም መፍጥር ( በአመራር፣ በሰው ኃይል፣ በመንፈሳዊነት፣ በግንኙነት፣ በዕውቀት፣በልማት፣ በፋይናንስ፣ በቴክኖሎጂ)፤
  • ዓለም አቀፍ ግንኙነትና የትብብር አገልግሎትን መርሕ ያደረገ የኦርቶዶክሳውያን ኢኮኖሚያዊ፣ ማኅበራዊና ፖለቲካዊ ተሳትፎ ማሳደግ፣

አቡነ ጎርጎርዮስ ካልዕ
የሸዋ ሊቀ ጳጳስ ፲፱፻፴፪-፲፱፻፹፪ዓ.ም.

የማኅበሩ ህንጻ