• እንኳን በደኅና መጡ !

ዜናዎች፣ ወቅታዊ ክንውኖች እና ልዩ ልዩ ይዘቶች

ርደተ መንፈስ ቅዱስ

ርደተ መንፈስ ቅዱስ ወይንም የመንፈስ ቅዱስ መውረድ በብሉይ ኪዳን በትንቢት የተነገርና  በሐዲስ ኪዳን የተፈጸመ ነው፡፡ ነቢዩ ኢዮኤል ስለ መንፈስ ቅዱስ ወደዚህ ዓለም መውረድ፣ በመንፈስ ቅዱስ ጸጋና ሀብትነት ዓለም እንደሚታነጽና ሃይማኖት እንደሚጸና እንዲህ ሲል ተናግሯል፤ ‹‹ከዚህም በኋላ እንዲህ ይሆናል፤ መንፈሴን በሥጋ ለባሽ ሁሉ ካይ አፈሳለሁ፡፡›› (ኢዩ. ፪፥፳፰)

የሊቀ መላእክት ቅዱስ ሚካኤል ክብረ በዓል

አንድ አምላክ በኾነ በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም ሰኔ ዐሥራ ሁለት፤ በዚች ዕለት የከበረ የመላእክት አለቃ የመልአኩ የሚካኤል የመታሰቢያውን በዓል ያከብራሉ፡፡ የሚያከብሩበትም ምክንያት እንዲህ ነው፤…

‹‹መረባችሁን በታንኳይቱ በስተቀኝ በኩል ጣሉ›› (ዮሐ. ፳፩፥፮)

ዓሣ ማሥገር አድካሚ እንደሆነ ሁሉ አስጋሪውም ብዙ ዓሣዎችን ይይዝ ዘንድ መረቡን ወደየት አቅጣጫ መጣል እንዳለበት ማወቅ ይጠበቅበታል፤ ካልሆነ ግን ምንም ዓሣ ሳያጠምድ ወደ ቤቱ ይመለሳል፤ ተርቦም ሊያድር ይችላል፡፡

‹‹ጌታችን በመለከት ድምጽ ዐረገ›› (መዝ. ፵፮፥፭)

ነቢዩ ዳዊት ለመዘምራን አለቃ የቆሬ ልጆች አስቀድሞ በመንፈሰ ትንቢት ‹‹አምላካችን በዕልልታ፥ ጌታችንም በመለከት ድምጽ ዐረገ፥ ዘምሩ፥ ለአምላካችን ዘምሩ፤ ዘምሩ፥ ለንጉሣችን ዘምሩ››  በማለት እንደተናገረ ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የማዳን ሥራውን ፈጽሞ ከሙታን ተለይቶ ከተነሣ በኋላ በዐርባኛው ቀን ዐርጓል፤ እኛም ይህንን ቃል በማሰብና በማክበር የጌታችንን የዕርገት በዓል ተስፋ መንግሥተ ሰማያትን አመላካች በመሆኑ በዝማሬ እና በዕልልታ እናከብር ዘንድ ይገባል፡፡ (መዝ.፵፮፥፭)

‹‹ከፊት ይልቅ ትጉ›› (፪ ጴጥ. ፩፥፲)

ሐዋርያው ቅዱስ ጴጥሮስ በመልእክቱ ከቀደመ ተግባራችን ይልቅ እንድንተጋ ያስተማረበት ኃይለ ቃል እንዲህ የሚል ነው፤ ‹‹እናንተ ግን በሥራው ሁሉ እየተጋችሁ፥ በእምነት በጎነትን፥ በበጎነትም ዕውቀትን ጨምሩ፤ በዕውቀትም ንጽሕናን፥ በንጽሕናም ትዕግሥትን፥ በትዕግሥትም እግዚአብሔርን ማምለክን፥ እግዚአብሔርም በማምለክ ወንድማማችነትን በወንድማማችነትንም ፍቅርን ጨምሩ፤ እነዚህ ነገሮች ለእናንተ ሆነው ቢበዙ፥ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስን በማወቅ ሥራ ፈቶችና ፍሬ ቢሶች እንዳትሆኑ ያደርጓችኋልና፡፡ እነዚህ ነገሮች የሌሉት ዕውር ነውና፥ በቅርብ ያለውን ብቻ ያያል፤ የቀደመውንም የኃጢአቱን መንጻት ረስቶአል፡፡ ስለዚህ ወንድሞች ሆይ፥ መጠራታችሁንና መመረጣችሁን ታጸኑ ዘንድ፥ ከፊት ይልቅ ትጉ፤ እነዚህንም ብታደርጉ ከቶ አትሰናከሉም፡፡ እንዲሁ ወደ ዘለዓለም ወደ ጌታችንና መድኃኒታችን ወደ ኢየሱስ ክርስቶስ መንግሥት መግባት በምልአት ይሰጣችኋል፡፡›› (፪ ጴጥ. ፩፥፭-፲፩)

‹‹ልባም ሴትን ማን ሊያገኛት ይችላል፤ ዋጋዋ ከቀይ ዕንቊ እጅግ ይበልጣል!›› (ምሳ. ፴፩፥፱)

ዓለማችን የልዩነት መድረክ ናት፡፡ ልዩነቶቹ እንዲህ፣ እንዲያ፤ አንድ እና ሁለት ተብለው የማይወሰኑ ናቸው፡፡ ሴትነትና ወንድነትም የጾታ ልዩነት አንድ መደብ ናቸው፤ የሴት መሆንም የወንድ መሆንም መገናኛው ሰው መሆን ነው፡፡ ጥያቄው ታዲያ ምን ዓይነት ሴት ወይም ምን ዓይነት ወንድ እንሁን፤ ከዚያም ምን ዓይነት የሰው ልጅ ይኑር የሚለው ነው፡፡ ወንድ የሚለው ስም ብቻውን ወደ ሰውነት አያደርስም፤ ሴት ተብሎ መጠራትም ሴት የመሆንን ትክክለኛ መዳረሻ ጥግ አያመጣውም፡፡ ሁሉ በተገቢው ሚዛን ሊመዝነው የሚችለውን ሚዛን መምረጥ አለበት፡፡

ደብረ ምጥማቅ

ግብጽ በምትገኘው በእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ስም በተሠራችው ደብረ ምጥማቅ ቤተ ክርስቲያን ጉልላት ላይ ድንግል ማርያም ከግንቦት ፳፩ ጀምሮ እስከ ፳፭ ቀናት በተከታታይ በመገለጧ ሕዝበ ክርስቲያን በዓሏን ያከብራሉ፡፡  

‹‹እርስ በርሳችሁ የምትነካከሱ ከሆነ ግን፥ እርስ በርሳችሁ እንዳትጠፋፉ ተጠንቀቁ›› (ገላ.፭፥፲፭)

ዓለም አንድ መንደር ለመገንባት የሚያደርገውን ሩጫ ባፋጠነበት በዚህ ጊዜ ኢትዮጵያውያን በችግሮቻችን የተነሣ መለያየታችን እየባሰ በመሆኑ ሥቃያችን፣ ሞታችን፣ ስደታችንና መከራችን እየበዛ ነው፡፡ የመለያየቱ ጡዘት ሞትን እንጂ ሕይወትን፣ ማጣትን እንጂ ማግኘትን፣ ውርደትን እንጂ ክብርን አላመጣልንም፡፡ በመለያየት የዓለም ጅራት እንጂ ራስ አልሆንም፡፡ መለያየት ኋላ ቀርነትን እንጂ በረከትን ይዞልን አልመጣም፡፡ በመገዳደል ጠላትን ማሸነፍ ወይንም ድል ማድረግ አይቻልም፡፡ በመጻሕፍት እንደተማርነው ገድለው የወረሱ በጊዜ ሂደት ውስጥ ተገድለው ተወርሰዋል፡፡ ቆም ብለን ማስተዋል እስካልቻልን ድረስ ወደ ፊትም ይህ እውነት ይቀጥላል፤ አይቆምም፡፡

መልእክተ ቅዱስ ፓትርያርክ

በፌስቡክ የትስስር ገጽ ያግኙን

ስለ ማኅበረ ቅዱሳን መሰረታዊ መረጃዎች

ስያሜ

ማኅበረ ቅዱሳን እግዚአብሔር ያከበራቸው የነቢያት፣ የሐዋርያት፣ የጻድቃንና የሰማዕታት በአጠቃላይ የቅዱሳን ገድል፣ ትሩፋትና አማላጅነት የሚዘከርበት በመሆኑ ‹‹ማኅበረ ቅዱሳን›› የሚል ስያሜውን አግኝቷል፡፡

የማኅበሩ ርእይ

ቤተ ክርስቲያን ሁለንተናዊ የመሪነት ሚናዋን ስትወጣ ማየት

ተልእኮ

ለቤተ ክርስቲያን ተልእኮ መሳካት እና ለሕልውናዋ የሚተጋ፣ የተደራጀ ፣ ምሉዕ ኦርቶዶክሳዊ፤ ርቱዕ ዘመናዊ፤ ሁለገብ መሪ ትውልድ ማፍራት እና ማሰማራት

እሴቶች

  • መንፈሳዊነት

    ኦርቶዶክሳዊነት ርትዕት ሃይማኖት፣ ጽኑ እምነት፣ መልካም ምግባርና መንፈሳዊ እውቀት በአንድነት የተዋሐዱበት፤ አርአያ እግዚአብሔርን አጽንቶ በሐዋርያዊ የሕይወት ተጋድሎ እግዚአብሔርን በግብር ወደ መምሰል የሚታደግበት ፍጹም ሰማያዊ ሕይወት በመሆኑ፤ አባላት በየትኛውም ቦታ፣ ጊዜና ሁኔታ በማሰብ፣ በመናገር እና በመሥራት/በተግባር በሚገለጽ ክርስቲያናዊ ሥነ ምግባር ታንጸው፣ ፍኖተ አበውን ተከትለው፣ በታማኝነት እና በፈሪሐ እግዚአብሔር ቤተ ክርስቲያንን በቅንነት ያገለግላሉ::
  • አገልጋይነት

    የማኅበሩ አባላት አገልግሎትን የክርስቲያናዊ ሕይወታቸው መገለጫ አድርገው በመቀበል በበጎ ፈቃድ ሰማያዊውን ክብርና ጸጋ በመሻት፣ ምድራዊ ክብርና ውዳሴ ከንቱን ሳይፈልጉ፣ በትሕትና እና በክርስቲያናዊ ፍቅር በታማኝነት ያገለግላሉ::
  • የሐሳብ መሪነት

    ማኅበሩ ለቤተ ክርስቲያን ዘላቂ አገልግሎት የሚያስፈልጉ፣ ኦርቶዶክሳዊ እሳቤን የተከተሉና ዘመኑን የዋጁ የመሪነት ሐሳቦችን በማፍለቅ ከሚመለከታቸው የቤተ ክርስቲያን መሪዎች ጋር በመመካከር ይሠራል::
  • ተባባሪነት

    ማኅበሩ የቤተ ክርስቲያን አገልግሎት የሁሉም የቤተ ክርስትያን አካላት የወል ተግባር ነው ብሎ ያምናል:: በመሆኑም እንደየጉዳዩ አግባብነት ካላቸው ባለ ድርሻ እና አጋር አካላት ጋር በመግባባት፣ በመመካከር እና በቅንነት ለተልእኮ አንድነት ብዝኃ ጸጋን በማክበር አብሮ ይሠራል::
  • ሙያ አክባሪነት

    የማኅበሩ አባላት ባላቸው ልዩ ልዩ ሙያ /ዕውቀት/ ቤተ ክርስቲያንን ለማገልገል የተሰባሰቡ በመሆናቸው፣ በማኅበሩ አሠራሮች ሁሉ ከኦርቶዶክሳዊው ትምህርተ ሃይማኖት ጋር በማይጋጩ በእውነተኛ መረጃ ለሚደገፉ ሙያዊ ምክረ ሐሳቦች ተገቢውን ክብርና ቅድሚያ ይሰጣል:: በቤተ ክርስቲያንም ለመንፈሳዊ እና ለዘመናዊው (አስኳላ) ሙያ ተገቢው ክብር እንዲሰጥ ይሠራል::
  • ምክንያታዊ ሞጋችነት

    ማኅበሩ በእውነተኛ መረጃ ላይ ተመሥርቶ ቤተ ክርስቲያንን ከውስጥም ሆነ ከውጭ የሚፈትኑ አስተሳሰቦችን፣ አሠራሮችን፣ ልማዶችን እና ትርክቶችን በግልጽና በመንፈሳዊ ጥብዓት እና በእውነት እንዲሞገቱና መፍትሔ ላይ እንዲደረስ ይሠራል::
  • ተጠያቂነት

    የማኅበሩ አገልግሎት ግብ ሰማያዊ ዋጋ ማግኘት ስለሆነ ኀላፊነትን በአግባቡ አለመወጣት በእግዚአብሔር እና በሰዎች ዘንድ የሚያስጠይቅ በመሆኑ በየትኛውም እርከን ላይ ያለ አባል እና አመራር በማኅበሩ አሠራር መሠረት በተሰጠው ኀላፊነት ተጠያቂ ይሆናል፡፡

ዓላማዎች

  • የቤተ ክርስቲያን ተቋማዊ አስተዳደር፣ የአሠራር ሥርዐትና አስተሳሰብ፣ በቴክኖሎጂ እና በልዩ ልዩ መንገዶች በመደገፍ ዘመኑን ለዋጀ ጠንካራ አገልግሎት ማብቃት፤
  • የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ተማሪዎችን ሙሉ ሰብእናን የሚገነባ ሥርዐተ ትምህርት በማስተማር ዘመኑን የዋጁ ምሉዕ ኦርቶዶክሳዊ የሆኑ በቤተ ክርስቲያን አስተዳደራዊ መዋቅር የሚያገለግሉ እንዲሁም በማኅበራዊ፣ በኢኮኖሚያዊ በፖለቲካዊ እና በሀገር አስተዳደር ጉዳዮች መሪ/ንቁ ተሳታፊ አገልጋዮችን ማፍራት እና ማሠማራት፤
  • የተተኪውን ትውልድ ምንጭ ለማጎልበት የሰ/ት/ቤቶችን አቅም በማጠናከር የሕጻናት እና የወጣቶችን የተተኪነት ሚና ማሳደግ፤
  • ኦርቶዶክሳዊ መንፈሳዊነትን በተግባር የሚገልጽ ቤተሰብ እና አንድነቱን የጠበቀ ኦርቶዶክሳዊ ማኅበረሰብ በመገንባት የተደራጀ እና የተናበበ አገልግሎት መስጠት፤
  • በተደራጀ እና ተደራሹን ማእከል ባደረገ መንገድ ስብከተ ወንጌልንና ሐዋርያዊ ተልእኮን ዘርፈ ብዙ በሆኑ መንገዶች በመላው ዓለም ማስፋፋት፤
  • በቤተ ክርስቲያን ላይ የሚነዙትን የርእዮተ ዓለም፣ የሐሰት ትርክቶች እና የአጽራረ ቤተ ክርስቲያንን እንቅስቃሴ ጥናት እና ምርምር ላይ ተመርኩዞ መሞገት እና የተሳሳቱትን በማረም፣ በጠንካራ የዕቅበተ እምነት አገልግሎት የቤተ ክርስቲያንን ሕልውና ማስጠበቅ፤
  • በተመረጡ ገዳማት እና አብነት ትምህርት ቤቶች የልኅቀት ማእከል እና የተለየ ክርስቲያናዊ ተልእኮ የሚፈጽሙ እንዲሆኑ የሚያስችል ሁለገብ የአእምሮ ልማት ድጋፍ ማድረግ፤
  • ማኅበሩ ዘመኑን የዋጀ ተቋማዊ የአሠራር ሥርዓት በመዘርጋት ተልእኮውን ማሳካት የሚችልበት አቅም መፍጥር ( በአመራር፣ በሰው ኃይል፣ በመንፈሳዊነት፣ በግንኙነት፣ በዕውቀት፣በልማት፣ በፋይናንስ፣ በቴክኖሎጂ)፤
  • ዓለም አቀፍ ግንኙነትና የትብብር አገልግሎትን መርሕ ያደረገ የኦርቶዶክሳውያን ኢኮኖሚያዊ፣ ማኅበራዊና ፖለቲካዊ ተሳትፎ ማሳደግ፣

አቡነ ጎርጎርዮስ ካልዕ
የሸዋ ሊቀ ጳጳስ ፲፱፻፴፪-፲፱፻፹፪ዓ.ም.

የማኅበሩ ህንጻ