• እንኳን በደኅና መጡ !

ዜናዎች፣ ወቅታዊ ክንውኖች እና ልዩ ልዩ ይዘቶች

Zimare_Mewasit.JPG

የዝማሬ መዋሥዕት አድራሾች ተመረቁ

በደረጀ ትዕዛዙ
 
Zimare_Mewasit.JPG
 
በዙር አባ አቡነ አረጋዊ ገዳም የዝማሬ መዋሥዕት ትምህርታቸውን ተከታትለው ተመረቁት ደቀ መዛሙርት ከአቡነ እንድርያስ ጋር
በደቡብ ጎንደር ሀገረ ስብከት በላይ ጋይንት ወረዳ ሳሊ በተባለው ቀበሌ የሚገኘው የጽርሐ አርያም ዙር አባ አቡነ አረጋዊ ገዳም ዝማሬ መዋሥዕት ትምህርት ቤት ዐሥራ ሰባት የዝማሬ መዋሥዕት አድራሾችን አስመረቀ፡፡
Semera_Kidus_Yohanes_Church.jpg

በአፋር ሰመራ ከተማ የመጥምቁ ዮሐንስ ገዳም ቅዳሴ ቤት ተከበረ

ሎጊያ ወረዳ ማዕከል
    Semera_Kidus_Yohanes_Church.jpg
 
 
 
 
 
 
 
በሰመራ ከተማ የተሰራዉ የቅዱስ ዮሐንስ ቤተ ክርስቲያን
በአፋር ሀገረ ስብከት ሰመራ ከተማ በሀገረ ስብከቱና በአካባቢው ማኅበረሰብ ከፍተኛ ጥረት የተሠራው የቅዱስ ዮሐንስ መጥምቅ ገዳም መቃኞ ተጠናቆ ቅዳሴ ቤቱ ተከበረ፡፡

ሰንበት ትምህርት ቤቶቹ የልምድ ልውውጥ አደረጉ

በይብረሁ ይጥና
ከሲዳማ ሀገረ ስብከት ሀዋሳ ከተማና አካባቢዋ የተውጣጡ የስድስት ሰንበት ትምህርት ቤቶች ተወካዮች በአዲስ አበባ የአምስት ሰንበት ትምህርት ቤቶችን እንቅስቃሴ በመጎብኘት የልምድ ልውውጥ አደረጉ፡፡

የሐይቅ ቅዱስ ዮሐንስ ሕንፃ ቤተ ክርስቲያን ሥራ እንዲጠናቀቅ የድጋፍ ጥሪ ቀረበ

በደረጀ ትዕዛዙ
በደቡብ ወሎ ሀገረ ስብከት ሐይቅ ከተማ የሚገኘው የደብረ ናግራን ቅዱስ ዮሐንስ ፍቅረ እግዚእ ሕንፃ ቤተ ክርስቲያን ግንባታን ለማስፈጸም የምእመናን ድጋፍ ተጠየቀ፡፡

ዐቢይ ጾም፤ ወደ ትንሣኤ የሚደረግ ጉዞ

ዲ/ን ዘላለም ቻላቸው
አንድ ሰው ለጉዞ ሲነሣ ወዴት እንደሚሄድ ማወቅ አለበት፡፡ በዐቢይ ጾምም እንዲሁ፡፡ ከሁሉም በላይ ዐቢይ ጾም መንፈሳዊ ጉዞ ነው፤ መድረሻውም ትንሣኤ ነው፡፡ ለእውነተኛው መገለጥ ለፋሲካ መሟላት የሚደረግ ዝግጅት ነው፡፡ ስለዚህ በጣም አስፈላጊ የሆነና ስለ ክርስትና እምነታችንና ሕይወታችን በጣም ወሳኝ የሆነ ነገር ስለሚገልጥልን ይህን በዐቢይ ጾም እና በትንሣኤ መካከል ያለውን ግንኙነት ለመረዳት በመሞከር መጀመር አለብን፡፡

የክርስትና መሠረተ እምነት በጸሎተ ሃይማኖት (አራተኛ መጽሐፍ)

በሊቀ ጉባኤ አባ አበራ በቀለ   የሕይወት ብርሃን የሚያጠፋው ሞት የተባለው ጠላታችን በመጨረሻው ዘመን በእግዚአብሔር ኃይል አንዲጠፋና ሰውም የማይጠፋና ሰውም የማይጠፋውን የዘላለም ሕይወት እንደሚያገኝ ፣ ተድላ ደስታ ያለበትን መንግሥተ ሰማያትንም እንደሚወርስ በቅዱሳት መጻሕፍት ተገልጿል ፤ በወንጌሉ የምሥራች ቃል ተረጋግጧል፡፡ ሙሉውን እዚህ በመጫን ያንብቡ

የክርስትና መሠረተ እምነት በጸሎተ ሃይማኖት (ሦስተኛ መጽሐፍ)

በሊቀ ጉባኤ አባ አበራ በቀለ   ‹‹ ጌታ ማኅየዊ ›› የተባሉት ቃላት ለአምላክ ብቻ የሚሰጡ ናቸው፡፡ ስለዚህም መንፈስ ቅዱስ ‹‹ ጌታ ማኅየዊ ›› መሆኑንና አምላክነቱንም በቅዱሳት መጻሕፍት ቃል በማረጋገጥ ፣ የመንፈስ ቅዱስ ተቃዋሚዎችን የረቱት የጥንቶቹ የቤተ ክርስቲያን አባቶች በአንቀጸ ሃይማኖታቸው ደንግገውልናል፡፡ መንፈስ ቅዱስም ከአብ ከወልድ ጋር እኩል ስለሆነ ከእነርሱ ጋር ልንሰግድለትና ልናመሰግነው እነደሚገባን አስተምረውናል፡፡ ሙሉውን […]

የክርስትና መሠረተ እምነት በጸሎተ ሃይማኖት (ሁለተኛ መጽሐፍ)

በሊቀ ጉባኤ አባ አበራ በቀለ   ሰው ባጠፋው ጥፋት ከደስታ ሕይወት ወጥቶ፣ ከክብሩ ተዋርዶና ወድቆ በችግርና በመከራ ኖሮ በመጨረሻ ሥጋው በመቃብር በስብሶ ሲቀር፣ ነፍሱ ደግሞ በሲዖል ስትሠቃይ በማየቱ ወልደ እግዚአብሔር ሰውን ከዚህ ክፉ ነገር ለማዳን ሰው ሆኖ ሕማምና ሞትን ተቀብሎ እንዳዳነው እናምናለን፡፡ ሙሉውን እዚህ በመጫን ያንብቡ

የክርስትና መሠረተ እምነት በጸሎተ ሃይማኖት (አንደኛ መጽሐፍ)

በሊቀ ጉባኤ አባ አበራ በቀለ እግዚአብሔር አምላክ የሁሉም አባት ነው መባሉ እርሱ ለፍጥረታት ሁሉ ማለት ለዓለም ሁሉ ሠራኢና መጋቢ ፣ ለሕዝብና ለአሕዛብ ሁሉ መሪና ጠባቂ በመሆኑ ነው፡፡ ‹‹እርሱ በክፉዎችና በበጎዎች ላይ ፀሐይን ያወጣልና በጻድቃንና በኃጢያተኞችም ላይ ዝናቡና ያዘንባልና››(ማቴ.5፣45)፡፡ እርሱ የሰማይ ወፎችን ይመጋባቸዋል ፤ የሜዳ አበቦችንና የሜዳውን ሣር ሁሉ በልዩ ልዩ ኅብረ ቀለም ያስጌጣቸዋል ፣ ያለብሳቸዋልም […]

የትምህርተ ሃይማኖት መቅድም

በሊቀ ጉባኤ አባ አበራ በቀለ አሚንሰ መሰረት ይእቲ ወካልአኒሃ ሕንጻ ወንድቅ እሙንቱ- እምነት መሠረት ናት ፤ ሌሎቹ ግን ሕንጻና ግንብ ናቸው:: በማለት ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ የሚያስገነዝበን እንደ ሕንጻና ግንብ ከሚቆጠሩት ከምግባርና ከትሩፋት ሁሉ በፊት የሃይማኖትን ቀዳሚነትና መሠረትነት ነው፡፡ መሠረት ሕንጻውን ሁሉ እንደሚሸከም እምነትም ምግባራትን ሁሉ ትይዛለች ፤ ሕንጻ ያለ መሠረት እንደማይቆም ምግባርም ያለ ሃይማኖት አይኖርም፡፡ […]

በፌስቡክ የትስስር ገጽ ያግኙን

ስለ ማኅበረ ቅዱሳን መሰረታዊ መረጃዎች

ስያሜ

ማኅበረ ቅዱሳን እግዚአብሔር ያከበራቸው የነቢያት፣ የሐዋርያት፣ የጻድቃንና የሰማዕታት በአጠቃላይ የቅዱሳን ገድል፣ ትሩፋትና አማላጅነት የሚዘከርበት በመሆኑ ‹‹ማኅበረ ቅዱሳን›› የሚል ስያሜውን አግኝቷል፡፡

የማኅበሩ ርእይ

ቤተ ክርስቲያን ሁለንተናዊ የመሪነት ሚናዋን ስትወጣ ማየት

ተልእኮ

ለቤተ ክርስቲያን ተልእኮ መሳካት እና ለሕልውናዋ የሚተጋ፣ የተደራጀ ፣ ምሉዕ ኦርቶዶክሳዊ፤ ርቱዕ ዘመናዊ፤ ሁለገብ መሪ ትውልድ ማፍራት እና ማሰማራት

እሴቶች

  • መንፈሳዊነት

    ኦርቶዶክሳዊነት ርትዕት ሃይማኖት፣ ጽኑ እምነት፣ መልካም ምግባርና መንፈሳዊ እውቀት በአንድነት የተዋሐዱበት፤ አርአያ እግዚአብሔርን አጽንቶ በሐዋርያዊ የሕይወት ተጋድሎ እግዚአብሔርን በግብር ወደ መምሰል የሚታደግበት ፍጹም ሰማያዊ ሕይወት በመሆኑ፤ አባላት በየትኛውም ቦታ፣ ጊዜና ሁኔታ በማሰብ፣ በመናገር እና በመሥራት/በተግባር በሚገለጽ ክርስቲያናዊ ሥነ ምግባር ታንጸው፣ ፍኖተ አበውን ተከትለው፣ በታማኝነት እና በፈሪሐ እግዚአብሔር ቤተ ክርስቲያንን በቅንነት ያገለግላሉ::
  • አገልጋይነት

    የማኅበሩ አባላት አገልግሎትን የክርስቲያናዊ ሕይወታቸው መገለጫ አድርገው በመቀበል በበጎ ፈቃድ ሰማያዊውን ክብርና ጸጋ በመሻት፣ ምድራዊ ክብርና ውዳሴ ከንቱን ሳይፈልጉ፣ በትሕትና እና በክርስቲያናዊ ፍቅር በታማኝነት ያገለግላሉ::
  • የሐሳብ መሪነት

    ማኅበሩ ለቤተ ክርስቲያን ዘላቂ አገልግሎት የሚያስፈልጉ፣ ኦርቶዶክሳዊ እሳቤን የተከተሉና ዘመኑን የዋጁ የመሪነት ሐሳቦችን በማፍለቅ ከሚመለከታቸው የቤተ ክርስቲያን መሪዎች ጋር በመመካከር ይሠራል::
  • ተባባሪነት

    ማኅበሩ የቤተ ክርስቲያን አገልግሎት የሁሉም የቤተ ክርስትያን አካላት የወል ተግባር ነው ብሎ ያምናል:: በመሆኑም እንደየጉዳዩ አግባብነት ካላቸው ባለ ድርሻ እና አጋር አካላት ጋር በመግባባት፣ በመመካከር እና በቅንነት ለተልእኮ አንድነት ብዝኃ ጸጋን በማክበር አብሮ ይሠራል::
  • ሙያ አክባሪነት

    የማኅበሩ አባላት ባላቸው ልዩ ልዩ ሙያ /ዕውቀት/ ቤተ ክርስቲያንን ለማገልገል የተሰባሰቡ በመሆናቸው፣ በማኅበሩ አሠራሮች ሁሉ ከኦርቶዶክሳዊው ትምህርተ ሃይማኖት ጋር በማይጋጩ በእውነተኛ መረጃ ለሚደገፉ ሙያዊ ምክረ ሐሳቦች ተገቢውን ክብርና ቅድሚያ ይሰጣል:: በቤተ ክርስቲያንም ለመንፈሳዊ እና ለዘመናዊው (አስኳላ) ሙያ ተገቢው ክብር እንዲሰጥ ይሠራል::
  • ምክንያታዊ ሞጋችነት

    ማኅበሩ በእውነተኛ መረጃ ላይ ተመሥርቶ ቤተ ክርስቲያንን ከውስጥም ሆነ ከውጭ የሚፈትኑ አስተሳሰቦችን፣ አሠራሮችን፣ ልማዶችን እና ትርክቶችን በግልጽና በመንፈሳዊ ጥብዓት እና በእውነት እንዲሞገቱና መፍትሔ ላይ እንዲደረስ ይሠራል::
  • ተጠያቂነት

    የማኅበሩ አገልግሎት ግብ ሰማያዊ ዋጋ ማግኘት ስለሆነ ኀላፊነትን በአግባቡ አለመወጣት በእግዚአብሔር እና በሰዎች ዘንድ የሚያስጠይቅ በመሆኑ በየትኛውም እርከን ላይ ያለ አባል እና አመራር በማኅበሩ አሠራር መሠረት በተሰጠው ኀላፊነት ተጠያቂ ይሆናል፡፡

ዓላማዎች

  • የቤተ ክርስቲያን ተቋማዊ አስተዳደር፣ የአሠራር ሥርዐትና አስተሳሰብ፣ በቴክኖሎጂ እና በልዩ ልዩ መንገዶች በመደገፍ ዘመኑን ለዋጀ ጠንካራ አገልግሎት ማብቃት፤
  • የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ተማሪዎችን ሙሉ ሰብእናን የሚገነባ ሥርዐተ ትምህርት በማስተማር ዘመኑን የዋጁ ምሉዕ ኦርቶዶክሳዊ የሆኑ በቤተ ክርስቲያን አስተዳደራዊ መዋቅር የሚያገለግሉ እንዲሁም በማኅበራዊ፣ በኢኮኖሚያዊ በፖለቲካዊ እና በሀገር አስተዳደር ጉዳዮች መሪ/ንቁ ተሳታፊ አገልጋዮችን ማፍራት እና ማሠማራት፤
  • የተተኪውን ትውልድ ምንጭ ለማጎልበት የሰ/ት/ቤቶችን አቅም በማጠናከር የሕጻናት እና የወጣቶችን የተተኪነት ሚና ማሳደግ፤
  • ኦርቶዶክሳዊ መንፈሳዊነትን በተግባር የሚገልጽ ቤተሰብ እና አንድነቱን የጠበቀ ኦርቶዶክሳዊ ማኅበረሰብ በመገንባት የተደራጀ እና የተናበበ አገልግሎት መስጠት፤
  • በተደራጀ እና ተደራሹን ማእከል ባደረገ መንገድ ስብከተ ወንጌልንና ሐዋርያዊ ተልእኮን ዘርፈ ብዙ በሆኑ መንገዶች በመላው ዓለም ማስፋፋት፤
  • በቤተ ክርስቲያን ላይ የሚነዙትን የርእዮተ ዓለም፣ የሐሰት ትርክቶች እና የአጽራረ ቤተ ክርስቲያንን እንቅስቃሴ ጥናት እና ምርምር ላይ ተመርኩዞ መሞገት እና የተሳሳቱትን በማረም፣ በጠንካራ የዕቅበተ እምነት አገልግሎት የቤተ ክርስቲያንን ሕልውና ማስጠበቅ፤
  • በተመረጡ ገዳማት እና አብነት ትምህርት ቤቶች የልኅቀት ማእከል እና የተለየ ክርስቲያናዊ ተልእኮ የሚፈጽሙ እንዲሆኑ የሚያስችል ሁለገብ የአእምሮ ልማት ድጋፍ ማድረግ፤
  • ማኅበሩ ዘመኑን የዋጀ ተቋማዊ የአሠራር ሥርዓት በመዘርጋት ተልእኮውን ማሳካት የሚችልበት አቅም መፍጥር ( በአመራር፣ በሰው ኃይል፣ በመንፈሳዊነት፣ በግንኙነት፣ በዕውቀት፣በልማት፣ በፋይናንስ፣ በቴክኖሎጂ)፤
  • ዓለም አቀፍ ግንኙነትና የትብብር አገልግሎትን መርሕ ያደረገ የኦርቶዶክሳውያን ኢኮኖሚያዊ፣ ማኅበራዊና ፖለቲካዊ ተሳትፎ ማሳደግ፣

አቡነ ጎርጎርዮስ ካልዕ
የሸዋ ሊቀ ጳጳስ ፲፱፻፴፪-፲፱፻፹፪ዓ.ም.

የማኅበሩ ህንጻ