መንፈሳዊነት
ኦርቶዶክሳዊነት ርትዕት ሃይማኖት፣ ጽኑ እምነት፣ መልካም ምግባርና መንፈሳዊ እውቀት በአንድነት የተዋሐዱበት፤ አርአያ እግዚአብሔርን አጽንቶ በሐዋርያዊ የሕይወት ተጋድሎ እግዚአብሔርን በግብር ወደ መምሰል የሚታደግበት ፍጹም ሰማያዊ ሕይወት በመሆኑ፤ አባላት በየትኛውም ቦታ፣ ጊዜና ሁኔታ በማሰብ፣ በመናገር እና በመሥራት/በተግባር በሚገለጽ ክርስቲያናዊ ሥነ ምግባር ታንጸው፣ ፍኖተ አበውን ተከትለው፣ በታማኝነት እና በፈሪሐ እግዚአብሔር ቤተ ክርስቲያንን በቅንነት ያገለግላሉ::
በለንደን ያሉ ምእመናን ለቅዱሳት መካናት እርዳታ ሰጡ፡፡
በዩናይትድ ኪንግደም ቀጠና ማዕከል
ለገዳማትና የአብነት ት/ቤቶች መርጃ የሚውል የገቢ ማሰባሰቢያና የምሳ መርሐ ግብር ኅዳር 12 ቀን 2003 ዓ.ም በለንደን ከተማ ተካሂዷል። ይህ ሪፖርት እስከ ተጠናቀረበት ኅዳር 27 /2003 ዓ.ም በጥሬ ገንዘብ £5,000.00 ፣በዓይነት አንድ የአንገት የወርቅ ሐብል እና አንድ የወርቅ የእጅ አምባር ሊገኝ ተችሏል።
ለቅዱስ ቁርባን ስለ መዘጋጀት
ልጆች ልንቆርብ ስንል ምን ማድረግ እንዳለብን ታውቃላችሁ? የሠራነው ኃጢአት ካለ ለእግዚአብሔር እና ለንስሐ አባታችን መናገር አለብን፡፡ የተጣላነው ሰው ካለ ይቅርታ መጠየቅ፣ ውሸት አለመዋሸት አለብን፡፡ ሌላው ልጆች ገላችንን መታጠብና ንጹሕ የሆነ ልብስ መልበስ አለብን፡፡
በተሰደብክ ጊዜ
ይህ ሳሚ የተባለ ሰው ወደ ንጉሡ ወደ ዳዊት ድንጋይ ይወረውርና ትቢያ ይበትን ነበር፡፡ ይህንን ተቃውሞ በሚያሰማበት ወቅት አንደበቱ አላረፈም ነበር፡፡ ይህ ሳሚ በቤተ ክርስቲያናችን የጸሎት መጻሕፍት ላይ በበርካታ ስፍራዎች በተራጋሚነቱ የሚወሳ ሲሆን በቅኔም ተሳዳቢ ሰውን ወክሎ የሚጠቀስ ነው፡፡ በሠራዊት ተከብቦ ያለውን ንጉሥ ዳዊትን ከፍ ዝቅ አድርጎ እየተሳደበና እየተራገመ ነበር፡፡ ‹‹ውጣ! አንተ የደም ሰው ምናምንቴ ሂድ! በፋንታው ነግሠሃልና እግዚአብሔር የሳኦልን ቤት ደም ሁሉ መለሰብህ፤ እግዚአብሔርም መንግሥትህን ለልጅህ ለአቤሴሎም እጅ አሳልፎ ሰጥቶታል፤ እነሆም አንተ የደም ሰው ነህና በመከራ ተይዘሃል!›› እያለ የስድብ ናዳ አወረደበት፡፡
ሐዘን ሲገጥመን ምን እናድርግ? / 2ቆሮ 5÷1-5 /
አይቴ ብሔሩ ለግእዝ?
ሁሉን መርምሩ መልካሙን ያዙ
የምህንድስና አገልግሎት ለቤተክርስቲያን ዕድገት
”የምህንድስና አገልግሎት ለቤተክርስቲያን ዕድገት” በሚል መሪ ቃል መርሐ ግብር ተዘጋጅቷል፡፡ ታኅሳስ 17 ቀን 2003 ዓ.ም ከቀኑ 7፡30—11፡30 በማኅበረ ቅዱሳን ሕንጻ ላይ አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ አዳራሽ፡፡ አዘጋጅ፡- በኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ/በሰንበት ት/ቤቶች ማ/መምሪያ ማኅበረ ቅዱሳን በሙያ አገልግሎትና አቅም ማጎልበቻ ዋና ክፍል::
ሶርያዊው ቅዱስ ኤፍሬም
ዲ/ን ቀለመወርቅ ሚደቅሳ
በኢትዮጵያ ቤተክርስቲያን የረጅም ዘመን ሐዋርያዊ ጉዞ ላይ በጎ ተፅዕኖ ካላቸው የአራተኛው መ/ክ/ዘመን አባቶች መካከል አንዱ ሶርያዊው ቅዱስ ኤፍሬም ነው፡፡ይህ አባት ምንም እንኳን በቋንቋ ውሱንነትና በቦታ ርቀት በርካቶች ሥራዎቹና ጽሑፎቹ የታወቁለት ባይሆንም ሕይወቱን በብሕትውና የመራ የትርጓሜ መጻሕፍትን ፣የቅኔ፣ የግጥምና የወግ ጽሑፍ በማዘጋጀት የኖረ ባለ በጎ ገድል አባት ነው፡፡
የማይቀበሩ መክሊቶች
የልደትን ብርሃን መናፈቅ ስብከት፣ ብርሃን ኖላዊ
ቅዱስ ጳውሎስ በሮሜ መልእክቱ «በሞቱ እንመስለው ዘንድ ከእርሱ ጋር በጥምቀት ተቀበርን እርሱ ክርስቶስ በአባቱ ጌትነት ከሙታን እንደተነሳ እየተወ እንደ እርሱ አዲስ ሕይወት እንኖራለን» /ሮሜ. 6.4/፤ እንዳለው ክርስትና በጥምቀታችን ከክርስቶስ ጋር ሞተን ከእርሱም ጋር ተነስተን በትንሳኤው ብርሃን በአዲስ ሕይወት የምንመላለስበት የእግዚአብሔርን ፍቅር እየቀመስን ያደረገልንን እያደነቅን ፀጋውን እለት እለት እየተቀበልን፣ እኛ ሞተን ክርስቶስ በእኛ ውስጥ ህያው ሁኖ የምንኖረው ኑሮ ነው፡፡