መንፈሳዊነት
ኦርቶዶክሳዊነት ርትዕት ሃይማኖት፣ ጽኑ እምነት፣ መልካም ምግባርና መንፈሳዊ እውቀት በአንድነት የተዋሐዱበት፤ አርአያ እግዚአብሔርን አጽንቶ በሐዋርያዊ የሕይወት ተጋድሎ እግዚአብሔርን በግብር ወደ መምሰል የሚታደግበት ፍጹም ሰማያዊ ሕይወት በመሆኑ፤ አባላት በየትኛውም ቦታ፣ ጊዜና ሁኔታ በማሰብ፣ በመናገር እና በመሥራት/በተግባር በሚገለጽ ክርስቲያናዊ ሥነ ምግባር ታንጸው፣ ፍኖተ አበውን ተከትለው፣ በታማኝነት እና በፈሪሐ እግዚአብሔር ቤተ ክርስቲያንን በቅንነት ያገለግላሉ::




ሰርግ በቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ ትምህርት
ዲ/ን ሽመልስ መርጊያ
ኅዳር 06/2004 ዓ.ም.
ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ ቅዱስ ጳውሎስ ለቈላስይስ ሰዎች በላከው መልእክት ም.፬፥፲፪ ላይ ያለውን ኃይለ ቃል በተረጎመበት ፲፪ኛው ድርሳኑ በዘመኑ የሚፈጸመውን የሰርግ ሥርዐት መሠረት በማድረግ ሰርግን አስመልክቶ ሰፋ ያለ ትምህርትን ሰጥቶአል ፡፡ ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ በሰርግ ምክንያት የሚወጡትን ወጪዎችና ግርግርና ሁካታ አጥብቆ የሚቃወም አባት ነው ፡፡ በዚህም ጽሑፍ ይህን ወደማስተዋል ልንመጣም እንችላልን ፡፡ መልካም ንባብ
ስለዚህ እንዲህ ብሎ ያስተምራል ፡- ትዳር ምንድን ነው? ትዕይንት(ትያትር) ነውን ? አይደለም፡፡ ምንም እንኳ እናንተ ለትዳርና ለምሳሌው
አክብሮት ባይኖራችሁ ትዳር ግሩም ምሥጢርና የታላቅ መንፈሳዊ ምሥጢር ምሳሌ ነው ፡፡ ቅዱስ ጳውሎስ ስለዚህ ሲያስተምር “ይህ ምሥጢር ታላቅ ነው” ይልና ጨምሮ “እኔ ግን ስለ ክርስቶስና ስለ ቤተ ክርስቲያን እላለሁ” ይላል ፡፡(ኤፌ.፭፥፴፪) ጋብቻ የቤተ ክርስቲያንና የክርስቶስ ምሳሌ ነው ፤ እንዲህ በከበረ ምሥጢር ላይ ዳንኪረኞችን በመጋበዝ ዝሙትን ታስተዋውቁበታላችሁን ? ነገር ግን ከእናንተ መካከል አንዱ እኔን፡- እንዲህ ስትል ደናግል ወይም ያገቡት አይጨፍሩ እያልክ ነው ፤ እንግዲያ እነርሱ በዚህ ሰርግ ላይ ካልጨፈሩ ማን ሊጨፍር ነው ? ብሎ ሊጠይቅ ይችላል ፡፡ ማንም አይጨፍር ነው መልሴ ፡፡
የቅዱስ ኤፍሬም ቅኔያዊ መዝሙራት
ጥቅምት 30/2004 ዓ.ም
መግቢያ
ቅዱስ ኤፍሬም 299 ዓ.ም ገደማ ንጽቢን በምትባለው ታላቅ ከተማ ተወለደ፡፡ ንጽቢን በጥንታዊቱ የሮም ግዛት በምሥራቅ የምትገኝ ከተማ ነበረች፡፡ አብዛኞቹ የታሪክ ጸሐፍት እንደሚስማሙበት ቅዱስ ኤፍሬም ከክርስቲያን ቤተሰብ የተገኘ ሲሆን በተወለደባት ከተማ በድቁና ሲያገለግል ረጅም የእድሜ ዘመኑን ያሳለፈ ቅዱስ ነው፡፡ አንዳንድ የታሪክ ጸሐፍት ግን የቅስና ማዕረግ አንዳለውም ይተርካሉ፡፡ ነገር ግን በአብዛኛዎቹ የሶርያ የታሪክ ጸሐፊያን ዘንድ ቅዱስ ኤፍሬም ዲያቆን እንደነበረ ተጽፎ እናገኛለን፡፡ ስለዚህም እስካሁን ድረስ በሶርያውያን ክርስቲያኖች ዘንድ የድቁና ማዕረግ በቅዱስ ኤፍሬም ምክንያት ትልቅ ቦታ የሚሰጠው ማዕረግ ሆኖ እናገኘዋለን፡፡
«ወአድኀነ ሕዝቦ በመስቀሉ»
3. ክብረ መስቀል
«ወአድኀነ ሕዝቦ በመስቀሉ»
መስከረም 2002 ዓ.ም.
በቤተክርስቲያናችን መስከረም 17 ቀን የመስቀል በዓል ይከበራል፡፡ እኛም በዚህ ትምህርት የመስቀሉን ነገር እና የበዓሉን ታሪክና አከባበር እንመለከታለን፡፡ ከዚያ በፊት ግን የነገረ መስቀሉ መነሻው ነገረ ድኅነት ነውና ጥቂት ነገሮችን ስለዚያ እንበል፡፡
ታላቅ የቪሲዲ ምርቃት
አዘጋጅ፡- በኢ/ኦ/ተ/ቤተ ክርስቲያን ሰ/ት/ቤቶች ማደራጃ መምሪያ ማኅበረ ቅዱሳን ሙያ አገልግሎትና አቅም ማጎልበቻ ዋና ክፍልቦታ፡-ጠቅላይ ቤተ ክህነት አዳራሽሰዓት፡- ቅዳሜ ኅዳር 02/03/2004 ዓ.ም ከቀኑ 7፡30 ጀምሮ
“አባታችን ሆይ” ክፍል አንድ
መግቢያ
ቅዱስ እሰጢፋኖስ በቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ አስተምህሮ
በዲ/ን ሽመልስ መርጊያ
(የሐዋ.6፡8-ም.7፡53)
መግቢያ
በሐዋርያት ስብከት ቤተ ክርስቲያን ስትስፋፋ በትምህርታቸውና በተዐምራታቸው ተስበው ወደ ክርስትና እምነት የተመለሱ ከአይሁድና ከአሕዛብ ወገን የሆኑ ክርስቲያኖች መሬታቸውንና ጥሪታቸውን በመሸጥ ያላቸውን ሀብት አንድነት በማድረግ በኢየሩሳሌም የአንድነት ኑሮን ይኖሩ ነበር፡፡ በሕብረትም የሐዋርያት ትምህርትን በመስማትና በጸሎት ይተጉ እንዲሁም ማዕድን በመባረክ በጋራ ይመገቡ ነበር፡፡ መጽሐፍ ቅዱስም “አንድ ልብና አንዲትነፈስ አላቸው በማለት (የሐዋ.4፡32) ስለአንድነታቸው ፍጹምነት ይነግረናል፡፡
ኢይብቁል ብክሙ መሪር ሥርው /መራራ ሥር አይብቀልባችሁ/ /ዕብ.12፡15/
ዘገብርኤሏ የአብርሃም ልጆች ነን የሚሉ ነገር ግን የአብርሃምን ሥራ የማይሠሩና የነቢዩ ዳዊት ልጆች ነን የሚሉ የእርሱን ፈለግ የማይከተሉ ዕብራውያንን ቅዱስ ጳዉሎስ «መራራ ሥር አይብቀልባችሁ» ሲል መከራቸው፡፡ ዕብራውያን በእግዚአብሔር እናምናለን፤ የእሱ ልጆች ነን እያሉ ይመጻደቁ ስለነበሩ መልካም ሥራ በመሥራት ወደ እግዚአብሔር እንዳይቀርቡ የከለከላቸውን መራራውን ሥር እንዲያስወግዱ አሳሰባቸው፡፡ ሁሉን የሚያይና የሚያውቅ አምላከ ሰማይ ወምድር ኢየሱስ ክርስቶስ እነዚህን […]
30ኛው አጠቃላይ ሰበካ መንፈሳዊ ጉባኤ ተጀመረ
{gallery count=1 width=350 height=300 counter=1 links=0 alignment=center animation=3000}smg30{/gallery}
የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን 30ኛው መደበኛ መንፈሳዊ ጉባኤ ጥቅምት 7 ቀን 2004 ዓ.ም በመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተ ክህነት የስብከተ ወንጌል አዳራሽ ከጠዋቱ 3 ሰዓት በብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ጳውሎስ ጸሎተ ቡራኬ ተጀምሯል፡፡
ቤተ ክርስቲያን የደረሰችበት ወቅታዊ ሁኔታ