መንፈሳዊነት
ኦርቶዶክሳዊነት ርትዕት ሃይማኖት፣ ጽኑ እምነት፣ መልካም ምግባርና መንፈሳዊ እውቀት በአንድነት የተዋሐዱበት፤ አርአያ እግዚአብሔርን አጽንቶ በሐዋርያዊ የሕይወት ተጋድሎ እግዚአብሔርን በግብር ወደ መምሰል የሚታደግበት ፍጹም ሰማያዊ ሕይወት በመሆኑ፤ አባላት በየትኛውም ቦታ፣ ጊዜና ሁኔታ በማሰብ፣ በመናገር እና በመሥራት/በተግባር በሚገለጽ ክርስቲያናዊ ሥነ ምግባር ታንጸው፣ ፍኖተ አበውን ተከትለው፣ በታማኝነት እና በፈሪሐ እግዚአብሔር ቤተ ክርስቲያንን በቅንነት ያገለግላሉ::
ለገዳማት የመብዐና አልባሳት ድጋፍ ተደረገ
በቅዱሳት መካናት ልማትና ማኅበራዊ አገልግሎት ዋና ክፍል በየወሩ እየተዘጋጀ የሚቀርበው የዜና ገዳማት መርሐ ግብር ግንቦት 7 ቀን
2004 ዓ.ም. ተካሔደ፡፡ በዋነኛነት ከየካቲት 24 እስከ መጋቢት 4 ቀን 2004 ዓ.ም. ድረስ በቆየው የመብዐ ሳምንት በሚል በችግር ላይ ለሚገኙ 400 አድባራትና ገዳማትን ለመርዳት ከምእመናን የተሰበሰበን መብዐ እና አልባሳት /ልብሰ ተክህኖ/ ስርጭት ላይ ያተኮረ ነበር፡፡ 800 ሺህ ብር ለመሰብሰብ የተቻለ ሲሆን እስከ 750 ምእመናን ተሳትፎ አድርገዋል በማለት የገለጹት የቅዱሳት መካናት ልማትና ማኅበራዊ አገልግሎት ዋና ክፍል የቦርድ ሰብሳቢ ወ/ሮ ዓለም ፀሐይ መሠረት ናቸው፡፡ በተገኘው ገቢ መሠረት ስርጭቱን በ4 ዙር ለማከናወን የታቀደ ሲሆን በመጀመሪያው ዙር በትግራይ 7 ሀገረ ስብከቶች ውስጥ ለሚገኙ 50 አድባራትና ገዳማት እንዲሁም አብያተ ክርስቲያናት ለአንድ ዓመት የሚሆን የመብዐ ስጦታ ተሰጥቷል፡፡
ስጦታው የተከፋፈለው ለአንድ ሳምንት የቆየ ጉዞ በማከናወን በየአድባራቱና ገዳማቱ በመገኘት ሲሆን ስርጭቱ ካካተታቸው ሀገረ ስብከቶች መካከል በደቡብ ትግራይ አርማጭሆ፤ እንደርታ፤ አዲግራት፣ አክሱም፣ ሽሬና ሁመራ ይገኙበታል፡፡ ከገዳማቱ መካከል ደብረ ሳሙኤል ዘሃሌ ሉያ፣ ደብረ በንኮል አቡነ መድኀኒነ እግዚእ፤ አባ ዮሃኒ ዘቆላ ተንቤን፣ አባ ቶማስ ዘደብረ ማርያም ዘሃይዳ፣ ፀአዳ አምባ አቡነ መርአዊ ክርስቶስ፣ እንደቆርቆር ቅድስት ማርያም ገዳማት ይገኙበታል፡፡
የእግር ጉዞው ምዝገባ ሊጠናቀቅ ቀናት ቀሩት
ግንቦት 16/2004 ዓ.ም.
በእንዳለ ደምስስ
{gallery count=1 width=350 height=300 counter=1 links=0 alignment=center animation=3000}yeger guzo{/gallery}
በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ሰንበት ትምህርት ቤቶች ማደራጃ መምሪያ የማኅበረ ቅዱሳን 20ኛ ዓመት ምሥረታን ምክንያት በማድረግ “ለሁለንተናዊ የቤተ ክርስቲያን አገልግሎት አብረን እንሥራ” በሚል መሪ ቃል ግንቦት 26 ቀን 2004 ዓ.ም. የእግር ጉዞ መዘጋጀቱ ይታወቃል፡፡ የመርሐ ግብሩ ዐቢይ ኮሚቴ አስተባባሪ ዲ/ን ዋሲሁን በላይ የእግር ጉዞው ምዝገባ በፍጥነት እየተካሔደ መሆኑንና በርካታ ቲኬቶችና ካናቴራዎች በመሠራጨት ላይ እንደሚገኙ እንዲሁም ሊጠናቀቅ ቀናት እንደ ቀሩት ገልጸዋል፡፡
ማኅበረ ቅዱሳን ከሰ/ት/ቤቶች ማደራጃ መምሪያ ወጥቶ በጠቅላይ ቤተ ክህነት ሥራ አስኪያጅ ሥር እንዲመራ ቅዱስ ሲኖዶስ ወሰነ፡፡
ማኅበረ ቅዱሳን ከሰ/ት/ቤቶች ማደራጃ መምሪያ ወጥቶ በጠቅላይ ቤተ ክህነት ሥራ አስኪያጅ ሥር እንዲመራ ቅዱስ ሲኖዶስ ወሰነ፡፡ በዓመት ሁለት ጊዜ የሚካሄደው የቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ የዘንድሮውን መደበኛ የርክበ ካህናት ስብሰባ በልዩ ልዩ የአጀንዳ ነጥቦች ላይ ተወያይቶ ውሳኔ በማሳለፍ ተጠናቀቀ፡፡ ከጉባኤው መጠናቀቅ በኋላ ውሳኔዎቹን በተመለከተ ከልዩ ልዩ የመገናኛ ብዙሃን ለተወከሉ ጋዜጠኞች መግለጫ የሰጠው የቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ […]
ሰበር ዜና
ግንቦት 15/2004 ዓ.ም. ማኅበር ቅዱሳን በቤተ ክህነት ጠቅላይ ሥራ አስኪያጅ እንዲመራ የቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ ወሰነ፡፡ የቅዱስ ሲኖዶስን መግለጫ ከዚህ ይመልከቱ፡፡ ዝርዝሩን እንደደረሰን እናቀርባለን፡፡
በዋልድባ ገዳምና በወልቃይት ስኳር ልማት ፕሮጀክት መካከል የተፈጠረውን አለመግባባት አስመልክቶ ማኅበረ ቅዱሳን ያደረገው ጥናት ዘገባ
ግንቦት 10/2004 ዓ.ም. ካለፉት ሁለትና ሦስት ወራት ወዲህ ከዋልድባ ገዳም ጋር በተያያዘ በመንግሥትና በገዳሙ መካከል አለመግባባት ተከስቷል፡፡ አለመግባባቱም ብዙዎችን አነጋግሯል፣ አከራክሯል፡፡ ከጉዳዩ መግዘፍ የተነሣ በርካቶችን ሲያስጨንቅና ሲያሳስብ ቆይቷል፡፡ የበርካታ ኢትዮጵውያንን ትኩረት የሳበ ሀገራዊ ጉዳይም ሆኗል፡፡ አለመግባባቱን ለማወቅ ከመጓጓት አንጻርም፤ የጉዳዩን ምንጭና መፍትሔ ነጣጥሎ ማየት እስከ ሚከብድ ድረስ በሰው ልቡና ሲመላለስ ቆይቷል፡፡ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ […]
“ዝክረ ገብረ እግዚአብሔር” በሚል ርዕስ ጉባኤ ተካሄደ፡፡
ግንቦት 10/2004 ዓ.ም.
በዲ/ን ዮሴፍ ይኲኖአምላክ
የቅዱስ ያሬድ መታሰቢያ ዐውደ ርዕይ ተከፈተ
ግንቦት 8/2004 ዓ.ም.
በእንዳለ ደምስስ
ቅዱስ ያሬድ የተሠወረበትን መታሰቢያ ዓመት ምክንያት በማድረግ ከግንቦት 5-12 ቀን 2004 ዓ.ም. የሚቆይ ዐውደ ርዕይ አዲስ አበባ በሚገኘው ደብረ ይባቤ ቅዱስ ያሬድ ቤተ ክርስቲያን ተዘጋጀ፡፡ የቅዱስ ያሬድ 1500ኛ ዓመት የልደት በዓል በተለያዩ መንፈሳዊ መርሐ ግብሮች በደማቅ ሁኔታ በሚቀጥለው ዓመት ለማክበር የደብሩ አስተደደር የደብሩ ስብከተ ወንጌል ጽ/ቤት ሰበካ ጉባኤውና ሰንበት ትምህርት ቤቱ ተቀናጅተው እየሠሩ የሚገኙ ሲሆን ይህ አውደ ርዕይ የመርሐ ግብሩ አንድ አካል መሆኑን አዘጋጆቹ ገልጸዋል፡፡
የአሰቦት ገዳምን ለመርዳት ጉባኤ ሊካሄድ ነው፡፡
ግንቦት 8/2004 ዓ.ም.
በእንዳለ ደምስስ
የአሰቦት ደብረ ወገግ ቅድስት ሥላሴና አቡነ ሳሙኤል ገዳምን ለመርዳት ታላቅ መንፈሳዊ ጉባኤ በጠቅላይ ቤተ ክህነት ስብከተ ወንጌል አዳራሸ ሰኔ 3 ቀን 2004 ዓ.ም. ከቀኑ 7 ሰዓት ጀምሮ ይካሄዳል፡፡ ከ800 ዓመታት በላይ እድሜ ያስቆጠረው ገዳም በፃድቁ አቡነ ሳሙኤል ዘደብረ ወገግ የተመሠረተ ሲሆን በቅርቡ የገዳሙ ደን ተቃጥሎ ከፍተኛ ጉዳት የደረሰበት መሆኑ ይታወሳል፡፡
በሕገወጦች በጨለማ የተዘጋጀው ደብዳቤ ተበተነ፡፡
ግንቦት 7/2004 ዓ.ም.
ከጥቂት ቀናት በፊት ማኅበረ ቅዱሳን ለጠቅላይ ቤተ ክህነት ማእከላዊ አስተዳደር ተገዥ ካለመሆን አልፎ የተቋሙን ሕልውና ወደ መፈታተን እንደ ደረሰ በማተት የሚከስ ደብዳቤ ለሕግ ተገዢ ባልሆኑ ግለሰቦች በጨለማ ተረቅቆ በመምሪያው ሓላፊ እንዲፈረም ተደርጎ ሊወጣ እንደ ነበር፤ ነገር ግን በመምሪያው ሓላፊው በቆሞስ መልአከ ጽዮን አባ ኅሩይ መታገዱን ገልጸን ነበር፡፡ ከዚያ በኋላ እስከ አሁን ምክንያቱ ግልጽ ባልሆነ ሁኔታ “ፍጹም ሕገ ወጥ ድርጊት በሕጋዊዋና በእውነተኛዋ ቤተ ክርስቲያን መፈጸም የለበትም፤ ይቁም” ያሉትን የመመሪያ ሓላፊ አስተዳደሩ ከቦታቸው አንሥቷል፡፡ በምትካቸውም ከግብረ አበሮቻቸው ጋር በመሆን ደብዳቤውን በወቅቱ በተገለጠው ሁኔታ በማርቀቅ፣ እንዲፈረምና እንዲሠራጭ የሞት ሽረት ትግል ሲያደርጉ ከነበሩት ግለሰቦች አንዱ የሆኑትን መምህር ዕንቊ ባሕርይ ተከሥተን ሾሟል፡፡
ቤተ ክርስቲያን በኦሮሚያ ክልል ስለምትገኝበት ሁኔታ ዐውደ ጥናት ተካሄደ
ግንቦት 7/2004 ዓ.ም.
በእንዳለ ደምስስ