መንፈሳዊነት
ኦርቶዶክሳዊነት ርትዕት ሃይማኖት፣ ጽኑ እምነት፣ መልካም ምግባርና መንፈሳዊ እውቀት በአንድነት የተዋሐዱበት፤ አርአያ እግዚአብሔርን አጽንቶ በሐዋርያዊ የሕይወት ተጋድሎ እግዚአብሔርን በግብር ወደ መምሰል የሚታደግበት ፍጹም ሰማያዊ ሕይወት በመሆኑ፤ አባላት በየትኛውም ቦታ፣ ጊዜና ሁኔታ በማሰብ፣ በመናገር እና በመሥራት/በተግባር በሚገለጽ ክርስቲያናዊ ሥነ ምግባር ታንጸው፣ ፍኖተ አበውን ተከትለው፣ በታማኝነት እና በፈሪሐ እግዚአብሔር ቤተ ክርስቲያንን በቅንነት ያገለግላሉ::
ብፁዕነታቸው አዲሱን ዓመት አስመልክቶ ቃለ ምዕዳንና ቡራኬ ሰጡ፡፡
ጳጉሜን 5 ቀን 2004 ዓ.ም.
በዲ/ን ዮሴፍ ይኲኖ አምላክ
የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ዐቃቤ መንበረ ፓትርያርክና የአርሲ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ናትናኤል ለመላው ኢትዮጵያውያንና ኢትዮጵያውያት ባስተላለፉት መልእክት፡- “የዘመናት ጌታ እግዚአብሔር አምላካችን እንኳን ከዘመነ ዮሐንስ 2004 ዓ.ም. ወደ ዘመነ ማቴዎስ 2005 ዓ.ም. በሰላም አደረሳችሁ፤ ለሚቀጥለውም ዘመን በቸርነቱ ጠብቆ በሰላምና በጤና እንዲያደርሳችሁ ቤተ ክርስቲያናችን ዘወትር ያለ ማቋረጥ ጸሎቷን ወደ ፈጣሪ ታቀርባለች” ካሉ በኋላ ሁሉም ኅብረተሰብ መልካም ታሪክን ለማስመዝገብ በተሰለፈበት ዓላማ የሚጠበቅበትን ድርሻ ማበርከት እንደሚገባው አሳስበዋል፡፡
የመግለጫውን ሙሉ ቃል ከዚህ በታች ያንብቡ፡፡
አዲስ ዓመት
ጳጉሜን 5 ቀን 2004 ዓ.ም.
በዳዊት ደስታ
ኢትዮጵያ የወራት ሁሉ መጀመሪያ መስከረም ነው፡፡ ይህ ወር ዘመን መለወጫ፣ ዕንቁጣጣሽ፣ ቅዱስ ዮሐንስ እየተባለ ይጠራል፡፡ ስለ አዲስ ዓመት በተለያየ ስም የመጠራቱ ታሪካዊ አመጣጥና ስያሜ መነሻ አሳቡ ምን እንደሆነ እንደሚከተለው እንመለከታለን፡፡
ዘመን መለወጫ
ዘመን መለወጫ መስከረም ወር የሆነበት ምክንያት “ብርሃናት /ፀሐይ፣ ጨረቃ፣ ከዋክብት/ የዓመት ዑደታቸውን በጳጉሜ ወር ጨርሰው በመስከረም ወር ስለሚጀምሩ ነው፡፡ ሌሊቱ ከቀኑ ጋር ይተካከላል፡፡ ዓመቱን ጠንቅቀው ቢቆጥሩ 364 ቀናት ይሆናል፡፡ “ሌሊቱም ከቀኑ ጋራ ይተካከላል፡፡ ዓመቱም ጠንቅቆ ቢቆጥሩት ሦስት መቶ ስልሳ አራት ቀን ይሆናል፡፡ /ሄኖክ.26፥44/ “ዘመናችንን እንደ ቀድሞ አድሱ” /ሰ.ኤር.5፥21/ እንዲል፡፡
ማኅበረ ቅዱሳን የሥራ አመራር ጉባኤ ምርጫ አካሄደ
ጳጉሜን 2 ቀን 2004 ዓ.ም
በእንዳለ ደምስስ
ከነሐሴ 30 ቀን 2004 ዓ.ም. ጀምሮ እየተካሄደ የሚገኘው የማኅበረ ቅዱሳን 10ኛ መደበኛ ጠቅላላ ጉባኤ በመጠናቀቅ ላይ ነው፡፡
ጳጉሜን 1 ቀን 2004 ዓ.ም. ጠዋት በተካሄደው የጠቅላላ ጉባኤው ስብሰባ “በማኅበረ ቅዱሳን የአገልግሎት ጉዞ የአባላት ተሳትፎና የወደፊት ሁኔታ” በተመለከተ ጥናት የቀረበ ሲሆን በአባላት ሰፋ ያለ ውይይት ተካሂዷል፡፡ ከሰዓት በኋላ በቀጠለው ስብሰባም “ስልታዊ ለውጥ ለሁለንተናዊ የቤተ ክርስቲያን እድገት ከማኅበረ ቅዱሳን ተልእኮና አቅም አንጻር” በሚል በዲ/ን ያረጋል አበጋዝና ዲ/ን ብርሃኑ አድማስ ጥናታዊ ጽሑፍ ቀርቦ በአባላት ውይይት ተደርጎበታል፡፡ በመጨረሻም የጽ/ቤት ግንባታ ሪፓርት ቀርቦ የመርሐ ግብሩ ፍጸሜ ሆኗል፡፡
መልአከ ሰላም ወጥኢና
ጳጉሜን 2 ቀን 2004 ዓ.ም.
በዲ/ን ዮሴፍ ይኲኖ አምላክ
ጳጉሜን፡- “ጭማሪ፣ ተወሳክ፣ አምስት ቀን ተሩብ” የሚል ትርጉም አለው፡፡ ጳጉሜን 13ኛ ወር ትባል እንጂ በውስጧ የያዘቻቸው ቀናት ቁጥር በአንድ ሳምንት ካሉ ቀናት ያነሱ ናቸው፡፡ እንደዚያም ሆኖ ኢትዮጵያን ብቸኛዋ የዓለማችን ባለ 13 ወራት ሀገር እንድትሆን ያስቻለች ልዩ ወር ናት፡- ወርኀ ጳጉሜን፡፡
ጳጉሜን ገዝፋና ጎልታ የምትታየው በመንፈሳዊ ዓለም ነው ማለት ይቻላል፡፡ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የዓለም ፍጻሜ መታሰቢያ ተደርጋ ትታሰባለች፡፡ በዚህ የተነሣ በርካታ የቤተ ክርስቲያኒቱ ተከታዮች ወርኀ ጳጉሜን በጾምና በጸሎት /በሱባኤ/ ያሳልፏታል፡፡ በተለይም እንደ ቤተ ክርስቲያን አስተምህሮ በቅዱስ ሩፋኤል ዕለት ሰማያት የሚከፈቱበት /ተርኅዎ ሰማይ/ መሆኑን በማመን ምእመናን ወደ ፈፍላጋት በመሄድ እንዲሁም በጳጉሜን ቀናት በሚዘንበው ዝናብ በመጠመቅና በረከትን ይሻሉ፡፡ ጸሎታቸውንም ከምንገባም በበለጠ ያቀርባሉ፡፡
የማኅበረ ቅዱሳን 10ኛ መደበኛ ጠቅላላ ጉባኤ ተጀመረ
ጳጉሜን 1 ቀን 2004 ዓ.ም.
በእንዳለ ደምስስ
በዋዜማው ነሐሴ 29 ቀን 2004 ዓ.ም. ከተለያዩ የሀገሪቱ አካባቢዎች የመጡ የማኅበሩ አባላት ከምሽቱ 12፤00 ስዓት ጀምሮ የጠቅላላ ጉባኤው አስተባባሪ ኮሚቴ ባዘጋጀው ትራንስፖርት ከማኅበሩ ዋናው ማእከል አቧሬ ወደሚገኘው አቡነ ጎርጎርዮስ የትምህርትና ሥልጠና ማእከል በመጓዝ የእንኳን ደህና መጣችሁ መልእክት፤ የመርሐ ግብር ትውውቅ፤ ሕጽበተ እግርና የእራት መርሐ ግብር ተከናውኗል፡፡
ቅዱስ ሲኖዶስ ጸሎተ ምህላ እንዲደረግ ወሰነ
የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ ጽ/ቤት ነሐሴ 30/2004 ዓ.ም. ለመገናኛ ብዙኅን በሰጠው መግለጫ ከጳጉሜ 1 ቀን 2004 ዓ.ም. እስከ መስከረም 10/2005 ዓ.ም. ድረስ ምእመናን ለሁለት ሱባኤያት በመላዋ ኢትዮጵያና በውጭ ሀገር በሚገኙ አህጉረ ስብከቶች በሚገኙ ገዳማት፣ አድባራትና አብያተ ክርስቲያናት ጸሎተ ምህላ እንዲደረግ ወስኗል፡፡ ቅዱስ ሲኖዶስ ጸሎተ ምኅላውን ያወጀበት ምክንያት ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ጳውሎስ […]
ማኅበረ ቅዱሳን በዝዋይ ተተኪ ሰባክያንን አስመረቀ
ነሐሴ 28 ቀን 2004 ዓ.ም.
በዳዊት ደስታ
ሊቀ መዘምራን ላእከ ማርያም ወልደ ኢየሱስ ዐረፉ
ነሐሴ 28 ቀን 2004 ዓ.ም.
በእንዳለ ደምስስ
ሊቀ መዘምራን ላእከ ማርያም ወልደ ኢየሱስ በአርሲ ክፍለ ሀገር በጢዮ ወረዳ ልዩ ስሙ ጨቢ አቦ በተባለ አካባቢ ከአባታቸው መምህር ወልደ ኢየሱስ ዘነበ እና ከእናታቸው ከወ/ሮ ወለተ ሩፋኤል ብስራት ነሐሴ 16 ቀን 1915 ዓ. ም. ተወለዱ፡፡
የሆሳዕና ደብረ ገነት ቅድስት ማርያም ቤተ ክርስቲያን የንባብና የቅዳሴ ትምህርት ቤት ተመረቀ
ነሐሴ 28 ቀን 2004 ዓ.ም.
በእንዳለ ደምስስ
ቤተ ክርስቲያንና የፓትርያርክ ምርጫ
ነሐሴ 25 ቀን 2004 ዓ.ም.
በዲ/ን ብርሃኑ አድማስ
ቤተ ክርስቲያን አንዲት፣ ቅድስት፣ ኩላዊትና ሐዋርያዊት መሆኗን ጥንታውያን አብያተ ክርስቲያን ሁሉ ይቀበላሉ፤ በመሠረተ እምነታቸው ውስጥም አካትተው በጸሎትና በአስተምህሮ ይጠቀሙበታል፡፡የዚህ መሠረታዊ ምክንያቱ ደግሞ ከዘመነ ሐዋርያት ጀምሮ ይህ ትምህርት ቢኖርም ነገር ግን መልእክቱን በአግባቡ ካለመረዳት የተነሣ እነ አርዮስና መቅዶንዮስ በትውፊት ከሐዋርያት ጀምሮ የመጣውን የቅዱሳት መጻሕፍት ትርጓሜ መሠረት መቀበልን ቸል ብለው በራሳቸው መንገድ ሔደው ስለሳቱ በጉባኤ ኒቅያ በማያሻማ መንገድ ቤተ ክርስቲያን አንዲት፣ቅድስት፣ ሐዋርያዊት እና ኩላዊት መሆኗን አስቀመጡ፡፡ በኋላ በጉባኤ ቁስጥንጥንያ ደግሞ ሁላችንም እንድንጸልይበት በተዘጋጀው አንቀጸ ሃይማኖት ላይ (ጸሎተ ሃይማኖት) ‹‹ ወነአምን በአሐቲ ቅድስት ቤተ ክርስቲያን እንተ ላዕለ ኩሉ ጉባኤ ዘሐዋርያት›› የሚለው የጸሎታችን መፈጸሚያ እንዲሆን ተደነገገ፡፡ በዚህም መሠረት እነዚህን ዓለም አቀፍ ጉባኤያት የሚቀበሉ ሁሉ የሚቀበሉትና የሚመሩበት መሠረታዊ ትምህርተ ሃይማኖት /doctrine/ ሆነ፡፡