መንፈሳዊነት
ኦርቶዶክሳዊነት ርትዕት ሃይማኖት፣ ጽኑ እምነት፣ መልካም ምግባርና መንፈሳዊ እውቀት በአንድነት የተዋሐዱበት፤ አርአያ እግዚአብሔርን አጽንቶ በሐዋርያዊ የሕይወት ተጋድሎ እግዚአብሔርን በግብር ወደ መምሰል የሚታደግበት ፍጹም ሰማያዊ ሕይወት በመሆኑ፤ አባላት በየትኛውም ቦታ፣ ጊዜና ሁኔታ በማሰብ፣ በመናገር እና በመሥራት/በተግባር በሚገለጽ ክርስቲያናዊ ሥነ ምግባር ታንጸው፣ ፍኖተ አበውን ተከትለው፣ በታማኝነት እና በፈሪሐ እግዚአብሔር ቤተ ክርስቲያንን በቅንነት ያገለግላሉ::
ቤተ ጣዖቱ ተዘጋ! የቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን የመሠረት ድንጋይ ተቀመጠ
ኅዳር 6 ቀን 2005 ዓ.ም.
በእንዳለ ደምስስ
“በአርሲ ሀገረ ስብከት በመርቲ ወረዳ ልዩ ስሙ ፈረቀሳ በተባለ ሥፍራ ከ120 አመታት በላይ የአርሲዋ እመቤት” በሚል የባዕድ አምልኮ ሥርዓት ሲፈጸምበት በነበረ ሥፍራ ላይ የባዕድ አምልኮ ሥርዓቱን በማጥፋት ብፁዕ አቡነ ናትናኤል የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ዐቃቤ መንበረ ፓትርያርክና የአርሲ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ የቅዱስ ገብርኤልን ቤተ ክርስቲያን ለመገንባት የመሠረት ድንጋይ ኅዳር 1 ቀን 2005 ዓ.ም. አኖሩ፡፡
ራሔል እንዘ ትበኪ በእንተ ውሉዳ፥ ራሔል ስለልጆችዋ አለቀሰች
ኅዳር 6 ቀን 2005 ዓ.ም.
በዲ/ን ኀይለ ኢየሱስ ቢያ
“ራሔል ስለ ልጆችዋ ስታለቅስ ብዙ ልቅሶና ዋይታ በራማ ተሰማ፤ መጽናናትንም እንቢ አለች፤ ልጆችዋ የሉምና” ማቴ.2፥18
ይህ የግፍ ልቅሶ 3 ጊዜ ተፈጽሟል፡፡ይኸውም፡-
1ኛ. በንጉሥ ፈርዖን ዘመን እስራኤላውያን በግብፅ እያሉ ራሔል የተባለች የሮቤል/ ስምዖን ሚስት ነፍሰጡር ሆና ጭቃ ስትረግጥ የወለደቻቸውን መንታ ልጆች ከጭቃ ጋር እንድትረግጥ ተገዳ በመርገጧ “ኢሀሎኑ በዝ ሰማይ አምላከ እስራኤል” በማለት እንባዋን ወደ ሰማይ ረጭታለች ዘዳ.1፥15፡፡ እግዚአብሔርም ልመናዋን ሰምቶ፥ ሊቀ ነቢያት ሙሴን አስነሥቶ ከግብፅ ነፃ አወጣቸው (ዘፀ. 3፥7 ተመልከቱ)
ማኅበሩ የነጻ የትምህርት ዕድል መስጠት ሊጀምር ነው፡፡
ኅዳር 5 ቀን 2005 ዓ.ም.
ዲ/ን ቴዎድሮስ ኃይሉ
ማኅበረ ቅዱሳን ኅዳር 2 ቀን 2005 ዓ.ም ብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳት፣ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ተማሪዎች፣ የሰንበት ትምህርት ቤት ተወካዮችና የማኅበረ ቅዱሳን አባላት በተገኙበት በጠቅላይ ቤተ ክህነት አዳራሽ በተደረገ የማስተዋወቂያ መርሐ ግብር ለአብነት ተማሪዎችና መምህራን የነጻ ትምህርት ዕድል ለመስጠት መዘጋጀቱን ገለጸ፡፡
ቅዱስ ዑራኤል በግሸን አምባ
ጥቅምት 29 ቀን 2005 ዓ.ም.
በመምህር ሳሙኤል ተስፋዬ
ቅዱስ ተብለው የሚጠሩት ደገኛው ንጉሠ ነገሥት ዐፄ ካሌብ የሀገረ ናግራን ክርስቲያኖችን ለመታደግ ዘምተው የአሕዛቡን ንጉሥ ፊንሀስን ድል አድርገው ሲመለሱ በነበራቸው መንፈሳዊ ፀጋ እንዲሁም በአበ ነፍሳቸው ፈቃደ ክርስቶስ ምክር የግሸን ደብረ ከርቤን ክብር በመረዳት ፤በ517 ዓ.ም ታቦተ እግዚአብሔር አብንና ታቦተ ማርያምን ከሀገረ ናግራን ወደ ኢትዮጵያ በማምጣት በግሸን አምባ ላይ ቤተ መቅደስ ሠርተው ቀዳሽና አወዳሽ መድበው ደብረዋታል፡፡ በወቅቱም አምባው መግቢያ ካለመኖሩ የተነሣ ተራራውን ሲዞሩ የንብ መንጋ በማየታቸው “አምባ አሰል” ብለውታል፡፡ ትርጓሜውም የማር አምባ ማለት ነው፡፡ በዚህ ምክንያት አካባቢው አምባ ሰል ሲባል ይኖራል፡፡
የቅድስት ሥላሴ መንፈሳዊ ኮሌጅ የድኅረ ምረቃ መርሐ ግብር ጀመረ
ጥቅምት 29 ቀን 2005 ዓ.ም.
በዲ/ን ዮሴፍ ይኲኖ አምላክ
ቅዳሜ ጥቅምት 24 ቀን 2005 ዓ.ም በቅድስት ሥላሴ መንፈሳዊ ኮሌጅ የመሰብሰቢያ አዳራሽ፤ ብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት የኮሌጁ የቦርድ አባላት፣ የአስተዳደር ሠራተኞች፣ መምህራንና ተማሪዎች እንዲሁም ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች በተገኙበት በጸሎት በተከፈተው ጉባኤ፥ ኮሌጁ የሁለተኛ ዲግሪ መርሐ ግብር መጀመሩ በይፋ ተበስሯል፡፡
የግብጽ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን 118ኛውን ፓትርያርክ መረጠች
ጥቅምት 26 ቀን 2005 ዓ.ም.
በእንዳለ ደምስስ
የግብጽ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ለ40 ዓመታት ቤተ ክርስቲያኗን ሲመሩ የነበሩትንና በቅርቡ ያረፉትን ፓትርያርክ ብፁዕ አቡነ ሺኖዳ ሣልሳዊን ለመተካት 118ኛውን ፓትርያርክ እሑድ ጥቅምት 25 ቀን 2005 ዓ.ም. በታላቅ ሥነ ሥርዓት መረጠች፡፡
በካይሮ አባሲያ ቅዱስ ማርቆስ ካቴድራል በተደረገው የእጣ አወጣጥ ሥነ ሥርዓት በእጩነት ከቀረቡት 3ቱ አባቶች መካከል አንዱን በፓትርያርክነት ለመሾም ዓይኑን በጨርቅ የተሸፈነ ሕፃን እጣውን እንዲያወጣ በማድረግ ብፁዕ አቡነ ታዋድሮስ / ቴዎድሮስ/ የግብጽ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ፓትርያርክ ሆነው ተመርጠዋል፡፡
ቅድስት ቤተ ክርስቲያን በጎቿን ይዛ እንድትዘልቅ …
ጥቅምት 26 ቀን 2005 ዓ.ም.
በየዓመቱ በጥምቀት ወር በቅድስት ቤተ ክርስቲያን የአስተዳደርና ዘርፈ ብዙ አገልግሎት ላይ የሚመክረው አጠቃላይ የሰበካ መንፈሳዊ ጉባኤ ለሠላሳ አንደኛ ጊዜ ተካሂዷል፡፡ በዚህ ጉባኤ ላይ የእናት ቤተ ክርስቲያናቸውን የአገልግሎት ጥሪ የተቀበሉ ምሁራን ልጆቿ፤ በልዩ ልዩ ርእሰ ጉዳዮች ላይ ያተኮሩ ጥናት ጽሑፎቻቸውን አቅርበው ውይይት ተደርጎባቸዋል፡፡ በእንደዚህ ዓይነቱ ታላቅ ጉባኤ ላይ፤ ለቅድስት ቤተ ክርስቲያን ሁለንታዊ አገልግሎት መቃናት የሚበጁ፣ በየሙያ ዘርፉ ዕውቀትና ልምድ ባካበቱ ምሁራን ልጆቿ የሚቀርቡ የጥናት ጽሑፎችና የሚካሄዱ ውይይቶች፤ እናት ቤተ ክርስቲያን ትውልዱን ይዛ ዘመኑን እየዋጀች ጸንታ እንድትቀጥል በማድረግ ረገድ ጠቀሜታቸው የጎላ ነው፡፡
በማኅበረ ቅዱሳን የአርባ ምንጭ ማእከል 14ኛውን ጠቅላላ ጉባኤ እየተካሄደ ነው
ጥቅምት 24 ቀን 2005 ዓ.ም.
ከአርባ ምንጭ ማዕከል
በማኅበረ ቅዱሳን የአርባ ምንጭ ማእከል ከጥቅምት 23-25ቀን 2005 ዓ.ም 14ኛውን ጠቅላላ ጉባኤ በመካሔድ ላይ ነው ፡፡ በመክፈቻ መርሐ ግብሩ ላይ ከሀገረ ስብከት የመምሪያ ሓላፊዎች፣ በአርባ ምንጭ ከተማ የሚገኙ የአድባራት አስተዳዳሪዎች እና ሰበካ ጉባኤያት፣ የሰንበት ትምህርት ቤት ተወካዮች ፤ የ16 ወረዳ ማእከላት እና 3 ግንኙነት ጣቢያዎች ፤ የ10 ግቢ ጉባኤያት ተወካዮች እና ጥሪ የተደረገላቸው ተጋባዥ እንግዶች ተገኝተዋል፡፡
የአዲስ አበባ ማእከል 18ኛ መደበኛ ጠቅላላ ጉባኤ ተካሄደ፡፡
ጥቅምት 22 ቀን 2005 ዓ.ም.
በእንዳለ ደምስስ
የአዲስ አበባ ማእከል 18ኛ ጠቅላላ ጉባኤ ከጥቅምት 17-18 ቀን 2005 ዓ.ም. በጠቅላይ ቤተ ክህነት ስብከተ ወንጌል አዳራሽ ለሁለት ቀናት ተካሄደ፡፡
መርሐ ግብሩ በመንበረ ልዑል ቅዱስ ማርቆስ ቤተ ክርስቲያን ልዑካን ጸሎተ ወንጌል በማድረስ በብፁዕ አቡነ ዮሴፍ የባሌ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ቡራኬና ጸሎት ተጀምሯል፡፡
የጥቅምቱ ቅዱስ ሲኖዶስ ጉባኤ ተጠናቀቀ
ጥቅምት 21 ቀን 2005 ዓ.ም.
በዲ/ን ዮሴፍ ይኲኖ አምላክ
በፍትሕ መንፈሳዊ አንቀጽ 5 ቁጥር 164 በተደነገገው መሠረት ጥቅምት 11 ቀን 2005 ዓ.ም. ጀምሮ ለአሥር ቀናት ያህል በ17 አጀንዳዎች ላይ ሲነጋገር የሰነበተው የቅዱስ ሲኖዶስ ምልአተ ጉባኤ አስፈላጊ ናቸው ያላቸውን ውሳኔዎችን በማስተላለፍ ዛሬ ከቀትር በፊት ተጠናቀቀ፡፡
ባለፈው ዓመት የተከናወነውን ሥራ ለመገምገምና የወደፊቱንም እቅድ ለመንደፍ እንዲችል ከየአህጉረ ስብከቱ ጽ/ቤቶች የቀረቡለትን ሪፓርቶች አዳምጦ አስፈላጊውን መመሪያ የሰጠው ቅዱስ ሲኖዶስ በሰሜን አሜሪካ ከሚገኙት አባቶች ጋር የተጀመረው የእርቀ ሰላም ድርድር ተጠናክሮ ይቀጥል ዘንድ ውሳኔ አሳልፏል፡፡