intro
/in ስብከት /by Mahibere Kidusanintro page…
ጾመ ፍልሰታን እንዴት እናክብር?
/in ስብከት /by Mahibere Kidusanበሕይወተ ሥጋ ሳለን ካልጾምንና ካልጸለይን ነፍሳችን ልትለመልም አትችልም፡፡ በጾም በጸሎት ዲያብሎስን፣ ዓለምንና ፍትወታት እኩያትን ድል መንሣት ይቻላል፡፡ እንደዚሁም በጾም አማካኝነት መንፈሳዊ ሕይወትን ማሳደግ ይቻላል፡፡
ውድ አንባቢያን ለመግቢያ ያህል ስለጾም ይህን ያህል አልን እንጂ ጾም በራሱ ምንድን ነው? ለምንስ ይጾማል? ምንስ ጥቅም ያስገኛል? ባንጾምስ ምን ጉዳት አለው? የሚሉትን በአጭር በአጭሩ ከገለጽን በኋላ በዋናነት ስለተነሣንበት ዐቢይ ርእስ ስለ ፍልሰታ ጾም በስፋት ለመዳሰስ እንሞክራለን፡፡
የፍልሰታ ጾም ከሰባቱ አጽዋማት አንዷ ነች፡፡ በደመቀና በተለየ ሁኔታ የምትጾምበት ምክንያት ምን እንደሆነና ሌሎች ተያያዥ ጥያቄዎች በማንሳት የቤተ ክርስቲያንን ሊቃውንት መልስ ጭምር ይዘን ቀርበናል መልካም ንባብ፡፡
ምኩራብ
/in ወቅታዊ ትምህርት /by Mahibere Kidusanሦስተኛው ሰንበት ምኩራብ ተብሎ የተሰየመበት ምክንያት በዚሁ ዕለት የሚዘመረው ጾመ ድጓ ከዋዜማው ጀምሮ እስከ ሰላሙ ድረስ በዕለተ ሰንበት «ቦአ ኢየሱስ ምኩራበ አይሁድ»
«ኢየሱስ በሰንበት ቀን ወደ አይሁድ ምኩራብ ገባ» እያለ ኢየሱስ በአይሁድ ምኩራብ ማስተማሩን እየጠቃቀሰና እያነሣሣ ስለሚዘምር ይህን ሰንበት ለዚህ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በምኩራብ እየገባ ለማስተማሩና በምኩራብ የሚሸጡ የሚለውጡ ነጋዴዎችን ለማስወጣቱ ቤተ መቅደሱን ለማስከበሩ መታሰቢያ ሆኖ ስለተሰጠ ነው፡፡ የዚህም በዓል ታሪክ ዝርዝር ሁኔታው በማቴዎስ ወንጌል ምዕ 21፡12-13 ተጠቅሷል፡፡
የቅርሶች ዘረፋን ለመከላከል
/in ርዕሰ አንቀጽ /by Mahibere Kidusanየኢትየጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን የረጅም ዘመን ታሪክና የበርካታ ውድና ምትክ የሌላቸው እንዲሁም ማንኛውም መጠን ያለው ገንዘብ የማይተካቸው ታሪካዊና ዓለማቀፋዊ እውቅና ያላቸው ቅርሶች ባለቤት ነች፡፡ እነዚህ ሃይማኖታዊ እና ተፈጥሮአዊ ቅርሶቻችን ከቀደምት አባቶቻችንና አያቶቻችን የወረሰናቸው እኛም በተራችን ጠብቀንና ተንከባክበን ለቤተክርስቲያን ዕድገትና ለሀገራዊ ልማት እያዋልን ለመጪው ትውልድ የምናስተላልፋቸው መተኪያ የሌላቸው እሴቶቻችን ናቸው፡፡ ቅርሶች ያለፈውን፣ ነባሩንና ተተኪውን ትውልድ የሚያገናኙ የኅብረ ትውልድ ድልድዮች ናቸው፡፡ ቤተ ክርስቲያን የእነዚህ ንዋይ ሊተምነው የማይችል ቅርሶች ግምጃ ቤት መሆኗ እና እኛም ልጆቿ የዚህ ታሪክ ተረካቢዎች በመሆናቸን መንፈሳዊ ፍስሐ ይሰማናል፡፡
የተዘጉ በሮች ይከፈቱ
/in የማኅበሩ መልእክት /by Mahibere Kidusanየይሁዳ ሰላምታ የቀሪ ሒሳብ ማስተካከያ ነው
/in የማኅበሩ መልእክት /by Mahibere KidusanCharacters display problem
/in ስብከት /by Mahibere KidusanProblem Descirption
The problem with display of characters is based on fonts that are installed on your machine. Fonts can be considered as the drawing instruction/picture for the computer so as to give us the display of the characters we …
ማኅበረ ቅዱሳን አምስት መጻሕፍትን አስመረቀ
/in ስብከት /by Mahibere Kidusanበኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን በሰንበት ት/ቤቶች ማደራጃ መምሪያ ማኅበረ ቅዱሳን የሚዲያና ሕዝብ ግንኙነት ዋና ክፍል አምስት አጻሕፍትን ጥር 30 ቀን 2001 ዓ.ም. አምስት ኪሎ በሚገኘው ብሔራዊ ሙዚየም አዳራሽ አስመረቀ
…
በቤተ ክርስቲያን ሥዕላት ዙሪያ የውይይት መርሐ ግብር ተካሄደ
/in ስብከት /by Mahibere Kidusanየኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የራሷን የአሳሳል ዘይቤ ጠብቃ ተንከባክባ ለቀጣዩ ትውልድ ማስተላለፍ እንዳለባት በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የሰንበት ት/ቤቶች ማደራጃ መምሪያ ማኅበረ ቅዱሳን ባዘጋጀው የውይይት መርሐ ግቭር ተገለጸ …