መንፈሳዊነት
ኦርቶዶክሳዊነት ርትዕት ሃይማኖት፣ ጽኑ እምነት፣ መልካም ምግባርና መንፈሳዊ እውቀት በአንድነት የተዋሐዱበት፤ አርአያ እግዚአብሔርን አጽንቶ በሐዋርያዊ የሕይወት ተጋድሎ እግዚአብሔርን በግብር ወደ መምሰል የሚታደግበት ፍጹም ሰማያዊ ሕይወት በመሆኑ፤ አባላት በየትኛውም ቦታ፣ ጊዜና ሁኔታ በማሰብ፣ በመናገር እና በመሥራት/በተግባር በሚገለጽ ክርስቲያናዊ ሥነ ምግባር ታንጸው፣ ፍኖተ አበውን ተከትለው፣ በታማኝነት እና በፈሪሐ እግዚአብሔር ቤተ ክርስቲያንን በቅንነት ያገለግላሉ::
የ ቆሙ መቃብሮች
መጋቢት 16 ቀን 2005 ዓ.ም.
በመ/ር ስምዓኮነ መላክ
መቃብር ሰዎች ሲሞቱ ወይም ነፍሳቸው ከሥጋቸው ሲለይ በክብር የሚያርፍበት ቦታ መቃብር ይባላል፡፡ መቃብር የሚላው ቃል የጎደጎደ ምድር ተብሎ ይተረጎማል፡፡ መዝ.14፥4፣ ኢሳ.22፥16 ሲዖልንም መቃብር ሲል ይገኛል፡፡ መትሕተ ታሕቲት ናትና፡፡
በማን ጊዜ እንደተጀመረ ባይታወቅም የሚቀበሩት በርስትነት በያዙት ቦታ ነበር ዘፍ.13፡፡ ያ ልማድ ሆኖልን ዛሬም በአዲስ ኪዳን የምንኖር ክርስቲያኖች እንደ አባቶቻችን ሁሉ በቤተ ክርስቲያን ዙሪያ እንቀበራለን፡፡ ስለምን ቢሉ ሥጋውን ደሙን የበላንበትና የጠጣንበት ብቸኛዋ ርስታችን በምድር ቤተ ክርስቲያናችን ናትና ነው፡፡
ቅድስት
መጋቢት 12 ቀን 2005 ዓ.ም.
በአባ አሥራተ ማርያም ደስታ
የማቴ.6፥16-24 ምንባብ በአንድምታ ትርጓሜ
ቁ.16. በምትጾሙበት ጊዜ እንደ ግብዞች አትሁኑ፡፡ እነዚያ ፊታቸውን አጠውልገው ግንባራቸውን ቋጥረው ሰውነታቸውን ለውጠው ይታያሉና፡፡ እንደ ጾሙ ሰው ያውቅላቸው ዘንድ የወዲህኛውን ውዳሴ ከንቱ አገኙ የወዲያኛውን ዋጋቸውን አጡት ብዬ በእውነት እነግራችኋለሁ፡፡
ዘወረደ
መጋቢት 12 ቀን 2005 ዓ.ም.
በአባ አሥራተ ማርያም ደስታ
የዮሐ.3፥10-21 ምንባብ በአንድምታ ትርጓሜ
ቁ.11. ራሱን ከዮሐንስ አግብቶ፡፡ ያየነውን፣ የሰማነውን እናስተምራለን ብዬ እንድናስተምር በእውነት እነግርሃለሁ፡፡ ምስክርነታችንን ግን አትቀበሉም፡፡
ቁ.12. ምድራዊ ልደታችሁን ስነግራችሁ ብነግራችሁ ያልተቀበላችሁኝ ሰማያዊ ልደታችሁን ብነግራችሁ እንደምን ትቀበሉኛላችሁ፡፡ ለዚህ ምክንያት አለው በጥምቀት፣ በንፍሐት ይሰጣል፡፡ ለዚያ ግን ንቃሕ ዘትነውም ባለው ነው፡፡ ምክንያት የለውምና፡፡
የጸሎት ቤት/ለሕፃናት/
መጋቢት 12 ቀን 2005 ዓ.ም.
ቤካ ፋንታ
ልጆችዬ እንኳን ለዐቢይ ጾም ሦስተኛ ሳምንት በሰላም አደረሳችሁ፡፡ ይህ ሦስተኛው ሳምንት ምኲራብ ተብሎ ይጠራል፡፡ ዛሬ የምንማረውም ትምህርት በዮሐንስ ወንጌል ምዕራፍ ሁለት ከቁጥር 12 እስከ 17 ያለውን የመጽሐፍ ቅዱስ ቃል ነው፡፡
ቤተ ክርስቲያን ማለት የክርስቲያኖች ቤት ማለት ነው፡፡ የእግዚአብሔር ልጆች በአንድነት ተሰብስበው እግዚአብሔርን የሚያመሰግኑበት፣ ከእግዚአብሔር ጋር የሚነጋገሩበት ቤት ስለሆነች የጸሎት ቤት ወይም የእግዚአብሔር ቤት እየተባለች ትጠራለች፡፡
ታላቁ ጾም(ለሕፃናት)
መጋቢት 11 ቀን 2005 ዓ.ም.
ቤካ ፋንታ
ልጆች እንኳን ለጌታችን ጾመ ሁዳዴ በሰላም አደረሳችሁ? ልጆች ዛሬ ስለ ጾም እንማራለን፡፡
ልጆችዬ በዚህ ወቅት የምንጾመው ጾም ብዙ ስሞች አሉት፡፡ እነርሱም፡- ዐቢይ ጾም ሁዳዴ የጌታ ጾምም ይባላል፡፡ የምንጾመውም ለሃምሳ አምስት ቀናት ያህል ነው፡፡
ይህንን ጾም እንድንጾም ያስተማረን አምላካችን ኢየሱስ ክርስቶስ ነው፡፡ ቆሮንቶስ ወደ ሚባል ትልቅ ገዳም ደረሰና ምግብ ሳይበላ፣ ውኃ ሳይጠጣ፣ አርባ ቀንና አርባ ሌሊት ጾመ፡፡ ልጆችዬ ጾም ማለት ውኃ ሳንጠጣ፣ ምግብ ሳንበላ እስከ ዘጠኝ ሰዓት መቆየት ማለት ነው፡፡ በተጨማሪም ሥጋ፣ ቅቤ፣ ወተት፣ እንቁላል…. የመሳሰሉ ምግቦችን የጾሙ ቀናት እስኪያልቅ ድረስ አይበላም፡፡
በሰማዕቱ አቡነ ጴጥሮስ ሐውልት ጉዳይ ውይይት ተደረገ
በዳዊት ደስታ
መጋቢት 9 ቀን 2005 ዓ.ም.
የሰማዕቱ የአቡነ ጴጥሮስ ሐውልት የቴክኒክ ጥናት ኮሚቴ ሐውልቱ ያለምንም ጉዳት እንዴት መነሣት እዳለበት ከባለ ድርሻ አካላት ጋር ውይይት አደረገ፡፡
የቴከኒክ ጥናት ኮሚቴው የካቲት ፲፫ ቀን ፳፻፭ ዓ.ም በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የስብሰባ አዳራሽ ለግማሽ ቀን ባካሔደው ውይይት ሐውልቱ ተነሥቶ ወደ ሥራ ከመገባቱ በፊት በሚያስፈልጉ ጉዳዮች ላይ በስፋት መክሯል፡፡
በሐዊረ ሕይወት መርሐ ግብር ላይ እንዲመለሱ የቀረቡ ጥያቄዎች
የተወደዳችሁ የሐዊረ ሕይወት አዘጋጆች ሰላመ እግዚአብሔር ይብዛላችሁ፡፡ ቤተ ክርስቲያናችን ለማንኛውም ጥያቄ መልስ ለመስጠት ዝግጁ እንደሆነች አምናለሁ፡፡ እናም ሁለት በአእምሮየ የሚመላለሱ ጥያቄዎች አሉኝ፡፡
የመጀመሪያው ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በመስቀል ላይ ተሰቅሎ ዓለምን እንደሚያድን ለሐዋርያት በሚያስተምርበት ወቅት ከአስራ ሁለቱ ሐዋርያት አንዱ የሆነው ቅዱስ ጴጥሮስ ጌታ ሆይ ይህስ አይሁንብህ ብሎ በተናገረ ጊዜ ጌታችን አንተ ሰይጣን ከዚህ ሂድ ብሎ በጴጥሮስ ላይ አድሮ የክርስቶስን የማዳን ሥራ የተቃወመውን ዲያብሎስን ተቃውሞታል፡፡ እኔ እንደገባኝ ከሆነ የቅዱስ ጴጥሮስ ሀዘኔታ ተገቢ እንዳልነበ ነው በጌታችን የማዳን መንገድ ልንደሰት ይገባል እንጅ በስቅለት ወቅትና በሌሎችም ጊዜያት ስለ ጌታችን ስቅለት የሚደረገው የሐዘን ስሜት ከክርስትና አስተምሮ አንጻር ተገቢ ነው ወይ?ሐዊረ ሕይወት ማለት…
ይህ ሁለት ቃል ተናቦ ፫ ሱባዔ (፳፩) ትርጉምን ይሰጠናል።
፩. ቃል በቃል የሕይወት ጉዞ ማለት ነው።
፪. የሕይወት ኑሮ ማለት ይሆናል።
“ሕይወት እንተ አልባቲ ሞት = ሞት የሌለባት የሕይወት ፍሬ/ኑሮ።” ዕዝ. ሱቱ. ፭፥፲፫
ደግሞም “ይኄይስ መዊት እመራር ሕይወት = ከመራር ኑሮ ሞት ይሻላል።” ሢራ ፴፥፲፯
፫. የመዳን ጉዞ፣ ወይም የደኅንነት ጉዞ፣
“ዛቲ ይእቲ ቀዳሚት ሕይወት = ይህች የመጀመሪያዋ ትንሣኤ ድኅነት ናት።” ራእ ፳፥፭
ደግሞም “መጻእኪ ለሕይወትኪ = ለሕይወትሽ፣ ለደኅንነትሽ መጣሽ።” ዮዲ. ፲፮፥፫
፬. የፈውስ ጉዞ፣ ወይም የጤንነት ጉዞ፣
“ወሰሚዖሙ ሕይወተ እሙታን = ከሙታን ተለይቶ መነሣትንም በሰሙ ጊዜ” ግ.ሐዋ. ፲፯፥፴፪
፭. የመኖር ጉዞ፣
የዲላ ዮኒቨርሲቲ ግቢ ጉባኤ የተመሠረተበትን አስራ ስድስተኛ ዓመቱን አከበረ
መጋቢት 6 ቀን 2005 ዓ.ም.
በዲ/ን ቴዎድሮስ ኃይሉ
በማኅበረ ቅዱሳን በዲላ ወረዳ ማእከል ሥር የሚገኘው የዲላ ዮኒቨርሲቲ ግቢ ጉባኤ የተመሠረተበትን ዐሥራ ስድስተኛ ዓመቱን በዋለሜ ደብረ ሰላም ቅዱስ ዑራኤል ቤተ ክርስቲያን በደመቀ ሁኔታ አከበረ፡፡
ግቢ ጉባኤው ከየካቲት 29 ቀን እስከ መጋቢት 1 ቀን 2005 ዓ.ም የተመሠረተበትን በዓል ሲያከብር በማኅበረ ቅዱሳን የአዋሣ ማእከል ለግቢ ጉባኤ ተማሪዎች የእንኳን አደረሳችሁ መልእክት አስተላልፏል፡፡ ማእከሉ በወከለው በአቶ ታደሰ ፈንታ በኩል ባስተላለፈው መልእክት “ዛሬ የምሥረታ በዓላችሁን የምታከብሩ ተማሪዎች ከመደበኛው ትምህርታችሁ ጎን ለጎን መንፈሳዊ ተግባራችሁን አጠናክራችሁ እንድትቀጥሉ ጥሪያችንን በማቅረብ ነው” በማለት የእንኳን አደረሳችሁ መልእክቱን አስተላልፏል፡፡
===== ዜና ሐዊረ ሕይወት ======
የሐዊረ ሕይወት ጉዞ አዘጋጅ ኮሚቴ ወደ ደብረ ኤዶም ቅዱስ ገብርኤል ቤተክርስቲያን በመሄድ የመንገዱንና የቦታውን ምቹነት አረጋግጦ መጣ፡፡ዝግጅቱ በከፍተኛ ሁኔታ እየተከናወነ ሲሆን የትኬት ሥርጭቱም በመጠናቀቅ ላይ ይገኛል፡፡ አጫጭር መረጃዎች ደብረ ኤዶም ቅዱስ ገብርኤል፡- ቦታው : ከአዲስ አበባ ወደ አምቦ መስመር ላይ 40(?) ኪ.ሜ ርቀት ላይ የሚገኝ ሲሆን የመንገዱ ጥራት ለማንኛውም ተጓዥ ምቹ መሆኑ ታይቷል፡፡ […]