መንፈሳዊነት
ኦርቶዶክሳዊነት ርትዕት ሃይማኖት፣ ጽኑ እምነት፣ መልካም ምግባርና መንፈሳዊ እውቀት በአንድነት የተዋሐዱበት፤ አርአያ እግዚአብሔርን አጽንቶ በሐዋርያዊ የሕይወት ተጋድሎ እግዚአብሔርን በግብር ወደ መምሰል የሚታደግበት ፍጹም ሰማያዊ ሕይወት በመሆኑ፤ አባላት በየትኛውም ቦታ፣ ጊዜና ሁኔታ በማሰብ፣ በመናገር እና በመሥራት/በተግባር በሚገለጽ ክርስቲያናዊ ሥነ ምግባር ታንጸው፣ ፍኖተ አበውን ተከትለው፣ በታማኝነት እና በፈሪሐ እግዚአብሔር ቤተ ክርስቲያንን በቅንነት ያገለግላሉ::
የደሴ ማዕከል ግቢ ጉባኤያት ማስተባበሪያ ክፍል “መራኄ ፍኖት” የአንድነት የጉዞ መርሐ ግብር አካሔደ
ታኅሣሥ 3 ቀን 2007 ዓ.ም.
ከደሴ ማእከል
የደሴ ማዕከል ግቢ ጉባኤያት ማስተባበሪያ ክፍል እስከ ዛሬ ከተለመደዉና ግቢ ጉባኤያት ከሚያደርጉት ጉዞ ለየት ባለ መልኩ ደሴና ኮምቦልቻ የሚገኙ 9 ግቢ ጉባኤያትን፣ የደሴ ወረዳ ማዕከል አባላትን፣ አባቶችን እንዲሁም የሰንበት ትምህርት ቤት አባላትን በአንድነት ያሳተፈ መራኄ ፍኖት የግቢ ጉባኤያት የአንድነት የጉዞ መርሐግብር ኅዳር 14 ቀን 2007 ዓ.ም በደብረ ነጎድጓድ ሐይቅ እስጢፋኖስ አቡነ ኢየሱስ ሞዓ ገዳም አካሄደ፡፡
ለአብነት ደቀመዛሙርት የሕክምና አገልግሎትና የጤና አጠባበቅ ሥልጠና ተሰጠ
ታኅሣሥ 3 ቀን 2007 ዓ.ም.
ዲ/ን ደስታ ይዲ/ትባረክ /ከወልድያ ማዕከል/
በማኅበረ ቅዱሳን የወልድያ ወረዳ ማዕከል ቅዱሳት መካናት ልማትና ማኅበራዊ አገልግሎት ክፍል ኅዳር 14 ቀን 2007 ዓ.ም. በምሥራቀ ፀሐይ ወይብላ ማርያም ቤተ ክርስቲያን የአቋቋም ጉባኤ ቤት የአቋቋም ትምህርት በመማር ላይ ለሚገኙ ሃምሳ የአብነት ትምህርት ደቀመዛሙርት የሕክምና አገልግሎት፣ የጤና አጠባበቅ ሥልጠና እና የመጸዳጃ ቁሳቁሶች ድጋፍ አደረገ፡፡
“ስለ ሃይማኖታችንና ስለ ቤተ ክርስቲያናችን ዘብ የምንቆምበት ወቅት አሁን ነው”
/ብፁዕ አቡነ ሉቃስ/
ኅዳር 26 ቀን 2007 ዓ.ም.
የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን በታሪክ ከገጠሟት ልዩ ልዩ ፈተናዎች ይልቅ በዚህኛው ትውልድ የደረሰባት ፈተና (ሙስናና ብልሹ አሠራር፤ የመልካም አስተዳደር እጦት፣ በውጭ ካሉ አባቶች ጋር ያልተቋጨው ዕርቀ ሰላም) ወደ ፊት እንዳትራመድ አድርጓታል፡፡ በእርግጥ የቤተ ክርስቲያኒቱ ወቅታዊ ችግሮች እነዚህ ብቻ ናቸው ማለት አይደለም፡፡ ችግሮችን ከማውራት ይልቅ መፍትሔው ላይ ማተኮር ለቤተ ክርስቲያኒቱም ለመንጋውም ጠቃሚ ስለሚሆን ነው እንጂ፡፡
በአገልግሎታችን የሚከሰቱ ፈተናዎችን የምናልፋቸው በእግዚአብሔር ኃይል ነው
ኅዳር 23 ቀን 2007 ዓ.ም.
ማኅበረ ቅዱሳን ከተመሠረተበት ጊዜ ጀምሮ ለቅድስት ቤተ ክርስቲያን አገልግሎት መጠናከር በርካታ ተግባራትን እንደ አንድ የቤተ ክርስቲያን ልጅነቱ ሲፈጽም የቆየ የአገልግሎት ማኅበር መሆኑ ይታወቃል፡፡ ምንም እንኳን ማኅበሩ እንደ እግዚአብሔር ፈቃድ ለመንፈሳዊ ዓላማ የተቋቋመ ቢሆንም መልካም ነገርን የማይወደው ጥንተ ጠላት ሰይጣን ዲያብሎስ የተለያዩ ፈተናዎችን ሲጋርጥበት ኖሯል፡፡ ማኅበሩም የሚደርሱበትን ፈተናዎች ከምእመናን፣ ከካህናትና ከብፁዓን አባቶች ጋር በመሆን በትዕግሥትና በጸሎት ሲያልፋቸው ቆይቷል፡፡
የባሕር ዳር ማእከል የጽ/ቤት ግንባታ በቅርቡ እንደሚጠናቀቅ ተገለጸ
ኅዳር 16 ቀን 2007 ዓ.ም.
ግዛቸው መንግሥቱ /ከባሕር ዳር ማእከል/
በማኅበረ ቅዱሳን የባሕር ዳር ማእከል በደብረ ጽዮን ሰላም አድርጊው ማርያም ገዳም በተሠጠው ቦታ በመገንባት ላይ የሚገኘው ጽሕፈት ቤት በቅርቡ እንደሚጠናቀቅ የጽ/ቤት ግንባታ ኮሚቴ የቴክኒክ ክፍል አስተባባሪ አቶ አስናቀ ለወየ አስታወቁ፡፡
‹‹አንተ በጎና ታማኝ አገልጋይ›› ማቴ:25
መ/ር ሳሙኤል ተስፋዬ
ህዳር 15 ቀን 2007 ዓ᎐ም
ልዑል እግዚአብሔር አምላካችን በክቡር ዳዊት አድሮ፤ “እከሥት በምሳሌ አፉየ፤ ወእነግር አምሳለ ዘእምትካት፤ አፌን በምሳሌ እከፍታለሁ፤ ከቀድሞ ጀምሮ ያለውንም ተምሳሌት እናገራለሁ” ብሏል፡፡ /መዝ. 77፡2/
በዚሁ መሠረት ጌታችን ወንጌለ መንግሥተ ሰማያትን በልዩ ልዩ ምሳሌ አስተምሯል፤ በማቴዎስ ወንጌል ምዕራፍ 25 ሁለት ምሳሌያትና አንድ ትንቢት ቀርበዋል፡፡
ከምሳሌያቱ የመጀመሪያው በዐሥሩ ደናግል አንጻር የቀረበው ሲሆን ሌላኛው ደግሞ ወጥተው ወርደው ነግደው ያተርፉበት ዘንድ ገንዘቡን ስለሰጠ ነጋዴ የሚናገረው ነው፡፡ ትንቢቱም ስለ ኅልቀተ ዓለም የተነገረ ነው፡፡ እንግዲህ በዚህ ዕትማችን ነግደው እንዲያተርፉበት ከጌታቸው የተሰጣቸውን መክሊት ስለተቀበሉት አገልጋዮች እንመለከታለን፡፡ ፈጣሪያችን ለብዎውን ማስተዋሉን ያድለን፡፡ ጌታችን መድኀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ለደቀ መዛሙርቱ ያስተማራቸውን ምሳሌያዊ ትምህርቶችን በሰፊው ተጽፎ እናገኛለን፡፡
1ዐ.2 የአንዳንድ አገናዛቢ አጸፋዎች ዝርዝር
ኅዳር 12 ቀን 2007 ዓ.ም.
በመ/ር ደሴ ቀለብ
በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ የፊሎሎጂ መምህር
ካልእ = ሌላ፣ ካልእከ / ሌላህ/፤ ካልእኪ የሌላሽን
ቀደምት =/የቀድሞ ሰዎች/፤ ቀደምትክሙ / የቀድሞ ሰዎች የሆኗችሁ ለእናንተ/
ክልኤ = ሁለት፣ ክልኤሆሙ / ሁለታቸው/፤ ክልኤነ / ሁለታችን /፤ ክልኤክሙ / ሁለታችሁ/
በበይናት = በመካከል እርስ በርስ፤ በበይናቲነ/ እርስ በርሳችን /፤ በበይናቲሆሙ / እርስ በርሳቸው/፤ በበይናቲክሙ / እርስ በርሳችሁ/
ማኅበረ ቅዱሳን በትግራይ ሦስት ገዳማት የተገበራቸውን ፕሮጀክቶች አስመረቀ
•ለፕሮጅክቶቹ ማስፈጸሚያ ከ3 ሚሊዮን 180 ሺሕ ብር በላይ ወጪ ሆኗል፡፡
ኅዳር 11 ቀን 2007 ዓ.ም.
በእንዳለ ደምስስ
ማኅበረ ቅዱሳን በቅዱሳት መካናት ልማትና ማኅበራዊ አገልግሎት አማካይነት በምሥራቃዊ ትግራይ ሀገረ ስብከት በደብረ ገሪዛን ጉንዳጉንዲ ቅድስት ማርያም፤ በሰሜን ምዕራብ ትግራይ ሽሬ እንዳሥላሴ ሀገረ ስብከት በአስገደ ጽምባላ ወረዳ በአቡነ ቶማስ ደብረ ማርያም ዘሃይዳ፤ በምሥራቃዊ ትግራይ ሀገረ ስብከት በማቅናት አጽቢ ወምበርታ ወረዳ በደብረ ቅዱሳን ዲቦ ቅድስት ማርያም አንድነት ገዳማት ያከናወናቸውን ፕሮጀክቶች አስመረቀ፡፡
የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ አቀባበል ተደረገላቸው
መ/ር ሳሙኤል ተስፋዬ ህዳር 09 ቀን 2007 ዓ.ም. በ2007 ዓ.ም የጥቅምት ሲኖዶስ የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ሆነው የተመደቡት ብፁዕ አቡነ ቀሌምንጦስ ሥራ ለመጀመር ከሀገረ ስብከቱ ሠራተኞች፣ ከአጥቢያ ገዳማትና አድባራት ሓላፊዎች፣ ጸሐፊዎችና ምእመናን ጋር ትውውቅ አድርገዋል፡፡ ብጹዕነታቸው የሥራ መጀመሪያቸው ለሆነው የትውውቅ መርሐ ግብር ወደ ሀገረ ስብከታቸው ሲሔዱ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማቲያስ ፓትርያርክ ዘኢትዮጵያ […]
ከ2004- 2007 ዓ.ም. በደቡብ ኦሞ ሀገረ ስብከት 16,630 አዳዲስ አማንያን ተጠመቁ
ኅዳር 8 ቀን 2007 ዓ.ም.
በእንዳለ ደምስስ
የደቡብ ኦሞ ሀገረ ስብከት ከማኅበረ ቅዱሳን ጋር በመተባበር ከ2004- 2007 ዓ.ም. 16,630 አዳዲስ አማንያንን በማስተማር መጠመቃቸውን የሀገረ ስብከቱ ሥራ አስኪያጅ አስታወቁ፡፡