መንፈሳዊነት
ኦርቶዶክሳዊነት ርትዕት ሃይማኖት፣ ጽኑ እምነት፣ መልካም ምግባርና መንፈሳዊ እውቀት በአንድነት የተዋሐዱበት፤ አርአያ እግዚአብሔርን አጽንቶ በሐዋርያዊ የሕይወት ተጋድሎ እግዚአብሔርን በግብር ወደ መምሰል የሚታደግበት ፍጹም ሰማያዊ ሕይወት በመሆኑ፤ አባላት በየትኛውም ቦታ፣ ጊዜና ሁኔታ በማሰብ፣ በመናገር እና በመሥራት/በተግባር በሚገለጽ ክርስቲያናዊ ሥነ ምግባር ታንጸው፣ ፍኖተ አበውን ተከትለው፣ በታማኝነት እና በፈሪሐ እግዚአብሔር ቤተ ክርስቲያንን በቅንነት ያገለግላሉ::
የማኅበሩ መልእክት
የካቲት 14 ቀን 2008 ዓ.ም
በሚመስለን ከተጨባጩ፤ በመላምትም ከእውነታው አንጣላ
በአሁኑ ወቅት በቅድስት ቤተ ክርስቲያናችን ውስጥ ባሉ አማኞችም ሆነ በሀገራችን ውስጥ ባሉ ዜጎች መካከል ልዩነቶችን አጉልቶ በማሳየት የመጠቃቃትን ስሜት ለመፍጠር የሚጣጣሩ መኖራቸውን ለመታዘብ የተለየ ጥናት የሚጠይቅ ነገር አይደለም፡፡ በተለያየ መንገድ የምንሰማቸው ዜናዎችና ወሬዎችም ከዚህ የራቁ አይደሉም፡፡ ምንም እንኳ ልዩነት ተፈጥሮአዊ እስከሚመስል ድረስ ከጥንት ጀምሮ የነበረ ቢሆንም ውጤቱ ግን እንደየዘመኑ የማኅበረሰብና የተቋማት መሪዎች አቅም እንደ ማኅበረሰቡም ግንዛቤ ይለያያል፡፡
በዲላ ማረሚያ ቤት አዳዲስ አማንያን የሥላሴ ልጅነትን አገኙ
የካቲት 3 ቀን 2008 ዓ.ም
ከዲላ ወረዳ ማእከል
የዲላ ወረዳ ማእከል ትምህርትና ሐዋርያዊ አገልግሎት ክፍል ከሰንበት ትምህርት ቤቶች ጋር በመተባበር በዲላ ማረሚያ ቤት ያስተማሯቸውን 48 ኢ አማንያን የነበሩ የሕግ ታራሚዎች ተጠምቀው የሥላሴ ልጅነትን አገኙ፡፡
ቅዱስ ፓትርያርኩ ለጻፉት ደብዳቤ ማኅበረ ቅዱሳን መልስ ሰጠ
ጥር 25 ቀን 2008 ዓ.ም
የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያንን አገልግሎት ለማጠናከር በቅዱስ ሲኖዶስ ይሁንታን አግኝቶ የተቋቋመው ማኅበረ ቅዱሳን ከተቋቋመበት ጊዜ ጀምሮ በተለያየ መልኩ ሲፈተን ኖሯል፡፡ ይሁን እንጂ ፈተናውን በምድራዊ ኃይል ሳይሆን በኃይለ እግዚአብሔር በብፁዓን አበው ጸሎትና በእውነተኞቹ የቤተ ክርስቲያን አባቶች ምክርና ተግሣፅ ሲቋቋመው ቆይቷል፡፡
በኮንሶ ወረዳ ከ540 በላይ ሰዎች ተጠመቁ
አርባ ምንጭ ማእከል
ጥር 23 ቀን 2008 ዓ.ም
በጋሞ ጎፋ ሀገረ ስብከት በኮንሶ ወረዳ ኮልሜ፣ አባሮባ እና ዱሮ (አርፋይዴ፣ኦካይሌ፣ ጉላይዴ፣ ቦይዴ፣ ማደሪያ እና ካሻሌ) ቀበሌያት ከ540 በላይ ሰዎች ጥር 11 ቀን 2008 ዓ.ም ተጠመቁ፡፡የጋሞ ጎፋ ሀገረስ ስብከት በዕለቱ የማጥመቅ ሥነ-ስርዓቱን እንዲፈጽሙ ወደስፍራው ያቀኑትን ሁለት ካህናት የመደበ ሲሆን የኮንሶ ወረዳ ቤተ ክህነት፣ ማኅበረ ቅዱሳን አርባ ምንጭ ማእከል የስብከተ ወንጌል ክፍል፣ ሰባት የግቢ ጉባኤያት ዲያቆናት እና የካራት ወረዳ ማእከል በቦታው በመገኘት ጥምቀቱን አስተባብረዋል፡፡
በተለያዩ ጊዜያት ከአክሱም ዩኒቨርሲቲ ግቢ ጉባኤ ለተመረቃችሁ እህቶችና ወንድሞች በሙሉ
የአክሱም ዩኒቨርሲቲ ግቢ ጉባኤ ኮርስና ልዩ ልዩ መርሐ ግብራትን የሚያከናውንበት የመማሪያ አዳራሽ እያሰራ ይገኛል። ነገር ግን ይህን አዳራሽ በራሱ ሰርቶ ለማጠናቀቅ የሚያስችል አቅም የለውም።
በጅማ ማእከል የጽ/ቤት ግንባታ ለማካሔድ የመሠረት ድንጋይ ተቀመጠ
የማኅበረ ቅዱሳን በጅማ ማዕከል ለሚያስገነባው ባለ አራት ፎቅ ሕንፃ የመሠረት ድንጋይ ታህሳስ 24 ቀን 2008 ዓ.ም ተቀመጠ፡፡የጅማ፣ ኢሊባቦር እና ጋምቤላ አህጉረ ስብከት ሊቀጳጳስ ብፁዕ አቡነ እስጢፋኖስ የመሠረት ድንጋዩን ካስቀመጡ በኋላ በሰጡት ትምህርት “በመከከላችን መደማመጡ፣ መተባበሩ፣ ሲኖር እግዚአብሔር ከእኛ ጋር ይሆናልና ፤የሀገረ ስብከቱን ሁለገብ ሕንፃ ከእለት ጉርሳችሁ ቀንሳችሁ እንደገነባችሁ ይህንንም ሕንፃ በሀገረ ስብከቱ የሚገኙ አድባራት እና መላው ምእመናን ጥረት በማድረግ የቤተ-ክርስቲያኒቷን አገልግሎት እንድታፋጥኑ” በማለት መልእክትና መመሪያ ሰጥተዋል፡፡
የጂንካ ማእከል የመጀመሪያውን የሐዊረ ሕይወት ጉዞ ወደ ስብከት ኬላ አደረገ
ጂንካ ማእከል
በጂንካ ማእከል በማኅበረ ቅዱሳን ጂንካ ማእከል የመጀመሪያውን የሐዊረ ሕይወት ጉዞውን በደቡብ ኦሞ ሀገረ ስብከት፣ በበና ጸማይ ወረዳ፣ ጫሊ ቅድስት ሥላሴ ስብከት ኬላ ታኅሣሥ 17 ቀን 2008 ዓ.ም በደማቅ ሁኔታ ተካሄደ፡፡በጉዞው ላይ የደቡብ ኦሞ ሀ/ስብከት የመምሪያ ሓላፊዎች፣ የጂንካ ከተማ ገዳም፣ አስተዳደርና የአቢያተ ክርስቲያናት አስተዳዳሪዎች እንዲሁም ከአዲስ አበባ የመጡ ተጋባዥ እንግዶች፣ ሰባኬ ወንጌልና ዘማሪያን በአጠቃላይ 1000 ምእመናን ተሳትፈዋል፡፡
የአርባ ምንጭ ማዕከል ሐዊረ ሕይወት አካሄደ
በኢትዮጵያ ኦ/ተ/ቤተ ክርስቲያን ማኅበረ ቅዱሳን አርባ ምንጭ ማዕከል የተዘጋጀው ልዩ መንፈሳዊ የጉዞ መርሐ-ግብር “ሐዊረ ሕይወት” የሕይወት ጉዞ ታህሳስ 24/2008 ዓ/ም ወደ ምዕራብ አባያ ደብረ ብሥራት ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ተደረገ፡፡
የሩቅ ምሥራቅ ግንኙነት ጣቢያ ሐዊረ ሕይወት አካሄደ !
በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን በማኅበረ ቅዱሳን የሩቅ ምስራቅ ግንኙነት ጣቢያ ከዐስራ ሁለቱ ሐዋርያት አንዱ የሆነው ቅዱስ ቶማስ ወደ አስተማረበት ደቡባዊ ሕንድ ኬረላ ግዛት ከታህሣሥ 17 እስከ 25 ቀን 2008 ዓ.ም የሐዊረ ሕይወት ጉዞ አካሂዷል፡፡
የተሐድሶ መናፍቃን ድፍረት የቅዱስ ሲኖዶስን ውሳኔ ለመቀልበስ እስከ መሞከር
ባለፉት ተከታታይ ዕትሞች ስለ ተሐድሶ መናፍቃን እንቅስቃሴ የትኩረት አቅጣጫዎች፣ ስልትና ግብ ማቅረባ ችን ይታወቃል፡፡ በዚህ ዕትም ደግሞ ተሐድሶ መናፍቃን ጥፋታቸውን አምነ ውና ተጸጽተው ከመመለስ ይልቅ የቅ ዱስ ሲኖዶስን ውሳኔ ካለመቀበል አልፎ ውሳኔዎችን ለማስቀልበስ እስከ መሞከር ድረስ የሚያደርጉትን ከንቱ ሩጫ እናቀር ባለን፡፡ መልካም ንባብ!