የግብጽ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያንን የፖትርያርክ ምርጫ የሚመለከት ረቂቅ ሕግ
መስከረም 10 ቀን 2005 ዓ.ም.
ወልደ ማርያም
ምዕራፍ 1
የዐቃቤ መንበሩን ምርጫ በተመለከተ
አንቀጽ 1
-
መንበረ ፓትርያርኩ በሞት ወይም በሌላ ምክንያት በመንበሩ ላይ ባይኖር ቅዱስ ሲኖዶስና ሚሊ ካውንስሉ /የምዕመናን ጉባኤ/ በዕድሜ አንጋፋ በሆነው ጳጳስ በሚጠራው ጉባኤ ሰብሳቢነት ቅዱስ ሲኖዶሱ ተሰይሞ ከ7 ቀን ባልበለጠ ጊዜ ውስጥ ዐቃቤ መንበር ይሰይማል፡፡ የተመረጠውም አባት ዐቃቤ መንበር በመሆን ያገለግላል፡፡ ብሔራዊ ዐዋጅ /republican decree/ ታውጆ በቤተ ክርስቲያኒቱ ሕግ፣ ትውፊትና ሥርዓት መሠረት ሕጋዊ የሆነው ፓትርያርክ ሹመት ይፈጸማል፡፡
ምዕራፍ 2
ለመንበሩ የሚመጥን ሰው ምርጫ
አንቀጽ 2
ለፓትርያርክነት ሹመት የሚወዳደር ሰው የሚከተሉትን ቅድመ ሁኔታዎች ማሟላት ይጠበቅበታል፡፡
-
በትውልድ ግብጻዊ በሃይማኖቱም የግብጽ ኦርቶዶክስ ክርስትና ሃይማኖት አባል የሆነ፡፡
-
የቤተ ክርስቲያንን ሕግ፣ ሥርዓትና ትውፊት የሚያዘውን የሚያሟላ፣ መነኩሴ የሆነ በጋብቻ ሕይወት ያልተወሰነ /ሜትሮፓሊታንም ሆነ ጳጳስ/ ይህ ቅድመ ሁኔታ ይጠበቅበታል፡፡
-
ዕድሜው ከአርባ ዓመት ያላነሠ በገዳም ከ15 ዓመት ላላነሠ ጊዜ የኖረ፡፡
አንቀጽ 3
-
ዐቃቤ መንበሩ የሚመራው 18 አባላት ያሉት ቅዱስ ሲኖዶስ የመረጠው የሜትሮፓሊታን የጳጳስነትና ከሚሊ ካውንስሉ /ከምእመናን ጉባኤ/ የተውጣጣ 18 አባላት ያሉት ጉባኤ ለመንበረ ጵጵስናው የሚወደደሩ እጩዎችን ዝርዝር ይይዛል፡፡
-
ኮሚቴው በመንበሩ ላይ ተቀምጦ የነበረው ፓትርያርክ ሥፍራው በሞት ወይም በሌላ ሁኔታ በለቀቀ በአንድ ወር ጊዜ ውስጥ መሰየም ይኖርበታል፡፡ የዚህን ኮሚቴ ስብሰባ የሚጠራው ሊቀ መንበሩ ነው፡፡ ሊቀ መንበሩ ከሌለ ወይም ከአቅም በላይ የሆነ ችግር ከተፈጠረበት አስቀድሞ የተመረጠው ሜትሮ ፓሊተን የሊቀ መንበሩን ሥፍራ ተክቶ ይሠራል፡፡ ጉባውንም ይጠራል፡፡
-
ጉባኤው የሚካሄደው የሁለቱም ጥምር ጉባኤ አባላት 2/3ኛው ያህል ሲገኙ ነው፤ ምልዓተ ጉባኤው ካልተሟላ ስብሰባው ለሌላ ጊዜ ይቀጠራል፡፡ ሁለተኛው ምልአተ ጉባኤ ስብሰባውን የሚካፈሉት አባላት ቢሟሉም ባይሟሉም የተገኙት አባላት በአብላጫ ድምጽ የሚወስኑት ውሳኔ ተቀባይነት ይኖረዋል፡፡
አንቀጽ 4
-
ለፓትርያርክነት የሚወዳደረው እጩ በሁለት ወር ጊዜ ውስጥ በስድስት ሜትሮ ፓሊታን ጳጳሳትና የገዳማት አስተዳዳሪዎች ወይም በሚሊ ካውንስሉ /የምእመናን ጉባኤ/ አስቀድመው ተመርጠው ያገለገሉ ወይም አሁን እያገለገሉ ያሉ አባላትን ይሁንታ የያዘ የጽሑፍ ድጋፍ ማቅረብ ይኖርበታል፡፡
-
ይሁንታ ያገኙበትን ድጋፍ ሲያቀርቡ የድጋፍ ደብዳቤ የተሰጠበት ቀንና ሰዓት ተመዝግቦ ደረሰኝ ይሰጣቸዋል፡፡
አንቀጽ 5
-
የምርጫ አስፈጻሚ ኮሚቴው በአንቀጽ 4 ላይ በተቀመጠው መሠረት በ15 ቀን ውስጥ ተሰብስቦ የድጋፍ ደብዳቤዎችን ይመረምራል፤ ሕጉን የተላለፈውን ያስወግዳል፡፡ በሕጉ መሠረት የመጡለትን ድጋፎች ይቀበላል፡፡
-
ኮሚቴው በተቀመጠው የማስረከቢያ ቀን የእጩዎችን ዝርዝር ካይሮ ለሚገኘው የፓትርያርክ ጽ/ቤትና በሌሎችም ሥፍራዎች ላሉ ጽ/ቤቶች ያስረክባል፡፡ የደረሰበትንም ውሳኔ በአረብኛ ቋንቋ ካይሮ ውስጥ በጋዜጣ እንዲታተም ያደርጋል፡፡
አንቀጽ 6
-
ለፓትርያርክነት መንበር የሚወዳደር ማንኛውንም እጩ የነጋሪት ጋዜጣ በወጣ በ15 ቀን ውስጥ ለመንበረ ጵጵስናው የማይመጥን ተወዳዳሪ አለ ብሎ ካመነ ለኮሚቴው ሊቀ መንበር /ሰብሳቢ/ ማስታወሻ ሊጽፍ ይችላል፡፡ አሳማኝ የሆነ ነጥብም ማቅረብ ይጠበቅበታል፡፡ ለአመልካቹ ደረሰኝ ይሰጠዋል፡፡
-
የቀረበውን ቅሬታ ኮሚቴው ተቀብሎ ከመረመረ በኋላ ኮሚቴው ውሳኔውን ያሳውቃል ኮሚቴው በአንቀጽ 2 ላይ የተቀመጡትን ነጥቦች ያላሟላ እጩ ካገኘ የማንንም ውሳኔ ሳይጠብቅ እጩውን የመሰረዝ ሥልጣን አለው፡፡ ለፓትርያርክነት እጩ ለመሆን ሁኔታዎችን ያሟሉ የመጨረሻዎቹን እጩዎች ያሳውቃል፡፡ የመጨረሻዎች ተወዳዳሪዎች የድጋፍ ደብዳቤ ያላቸው ሁነው ቁጥራቸው ቢያንስ አምስት ቢበዛ ሰባት መሆን ይኖርበታል፡፡ ስማቸውም በፊደል ተራ ቁጥር ይቀመጣል፡፡
አንቀጽ 7
-
ኮሚቴው የመጨረሻውን የፓትርያርክ ምርጫ ቀን ያሳውቃል፡፡ የመጨረሻውን ዝርዝር በፓትርያርኩ መኖሪያ በር ካይሮና በሌሎች አካባቢዎች ባሉ ጽ/ቤቶች ይለጥፋል፡፡ በዝርዝሩ ግርጌ ኮሚቴው ዕጩው የተመረጠበትን ቀን በማሳወቅ መራጮች ድምጽ እንዲሰጡ ይጋብዛል በተቀመጠው ቀንና ሥፍራ በየቀኑ ታትመው በሚወጡ ሦስት ጋዜጦች ካይሮ ውስጥ የምርጫውን ቀንና ሥፍራ ያሳውቃል፡፡ የምርጫ ቀኑ የእጩዎች ዝርዝር ከተገለጠበት ጀምሮ ከ30 ቀናት ባልበለጠ ጊዜ ውስጥ ይከናወናል፡፡
ምዕራፍ ሦስት
የፓትርያርኩ ምርጫ ድምጽ ሰጪዎች
አንቀጽ 8
-
በፓትርያርኩ ጽ/ቤት መራጮች ድምጽ የሚሰጡበት ሳጥን ይዘጋጃል፤ መራጮች በትውልድ ግብጻውያንና የኦርቶዶክስ እምነት ተከታዮች መሆን ይኖርባቸዋል፡፡ ከቤተ ክርስቲያኑ ጋር ባላቸው ግንኙነት በሃይማኖታቸውና በመልካም ግብራቸው የተመሰከረላቸው ሊሆኑ ይገባል፡፡
ድምጽ ከሚሰጥበበት ጠረጴዛ የሚቀመጡ አስመራጮች
- የፓትርያርኩ መንበር ባዶ ከሆነበት ጊዜ ጀምሮ በጎርጎራውያን ቀመር መሠረት ዕድሜው 35 ዓመት የሞላው፡፡
- የዩኒቨርሲቲ ዲግሪ ምሩቅ ወይም በግብጽ መንግሥታዊ ተቋም ተቀጥሮ ያገለገለ ወርሃዊ ገቢው 480 የግብጽ ፓውንድ ያላነሰ ወይም በባንክ፣ በካምፓኒ ተቀጥሮ የሚሠራ፣ ወይም በተመሳሳይ የሥራ ገበታ የተሰማራ፣ ገቢው ከ600 የግብጽ ፓውንድ ያላነሰ፣ ወይም ታክስ የሚከፍል ግብጻዊ ሆኖ ገቢው ከ100 የግብጽ ፓውንድ ያላነሰ መሆን ይኖርበታል፡፡
- በአንቀጽ 2 በተቀመጠው መሠረት በአስመራጭ ኮሚቴው ተቀባይነትን ያገኘ፡፡
አንቀጽ 9
-
ሦስት ካህናት፣ ሁለት የጠቅላላ ሚሊ ካውንስሉ/ የምእመናን ጉባኤ/ አባላት ወይም አሁን ወይም አስቀድሞ አባል የነበሩ ተመራጮች ያሉበት ኮሚቴ ድምጽ ሰጪዎች የሰጡትን ድምጽ ለመቁጠር ይሰየማል፡፡ ዐቃቤ መንበሩ የኮሚቴውን አባላት ይመርጣል ከካህናት መካከል በዕድሜ፣ ወይም በሌላ ቅድመ ሁኔታ ከፍ ካለው ጀምሮ ወደታች ያሉትን ሁሉ ሊመለከት ይችላል፡፡
ይህ ኮሚቴ በጽሑፍ በቀረበው ዳታ መሠረት የድምጽ ሰጪዎችን ድምጽ ከሚከተሉት ክፍሎች ይወስዳል፡፡
-
ሜትሮ ፓሊታን፣ ጳጳሳት፣ የገዳማት አስተዳዳሪዎች ተመራጮችና ፍላጎት ያላቸው መራጮች፡፡
-
ካይሮ ከሚገኙ መንፈሳውያት ማኅበራት ጉባኤ አባላትን፣ የአህጉረ ስብከት ተመራጮችን፣ በከተማዎች ያሉ የክርስቲያናዊ ሕግ አስፈጻሚዎች፣ በከተማ ያሉ ታዋቂ መራጮችን፡፡
-
ከመላው ካይሮ 24 ቀሳውስት 7ቱ ከአሌክሳንድርያ የሆኑ፡፡
-
የቀድሞ ጊዜና የአሁን የመጅሊስ አልሚሊስ የኮፕቲክ ፓርላማ አባላት፡፡
-
የጠቅላላ ሚሊ ጉባኤ የቀድሞና የአሁን አባላት፡፡
-
የጠቅላላ ሚሊ ጉባኤ የቀድሞና የአሁን አባላት፡፡
-
በአስመራጭ ኮሚቴው የተመረጡ ከካይሮ 72 አስመራጮች ከእነርሱም መካከል 24ቱ ከአሌክሳንድርያ የሆኑ፡፡
-
ከእያንዳንዱ ሀገረ ስብከት የተመረጡ 12 ድምጽ ሰጪዎች ሜትሮፓሊቲኑ ወይም ጳጳሱ በሚመራው ኮሚቴ የተመረጡ፡፡
-
ወይም የአህጉረ ስብከት ጳጳሳት 5 መራጮች የተካተቱበት አካል፡፡
-
ዕለታዊ ጋዜጣ አዟሪዎችና ዋና አዘጋጆችም እነርሱም የጋዘጠኞች ማኅበር አባላት የሆኑ፡፡
የመጀመሪያወቹ አምስቱ ድምጽ ሰጪዎች /መራጮች/ ዝርዝር ዐቃቤ መንበሩ በሚልከው ዝርዝር ውስጥ የተካተቱ መሆን ይኖርባቸዋል፡፡
በ6ኛው ተራ ቁጥር የተቀመጡ ድምጽ ሰጪዎች ዝርዝር በአስመራጭ ኮሚቴው ይላካል፡፡
በ7ኛ ተራ ቁጥር የተላኩ ድምጽ ሰጪዎች በሜትሮ ፓሊታን አማካኝነት ይላካሉ፡፡
በ8ኛው ምድብ ላይ ያሉ ድምጽ ሰጪዎች በጋዜጠኞች ጉባኤ አማካኝነት ይላካል፡፡
የፓትርያክነት ምርጫ ቅስቀሳው ከተጀመረ በሁለት ወር ጊዜ ውስጥ የመራጮች ዝርዝር ያለምንም ክፍያ ይከናወናል፡፡
አንቀጽ 10
-
የመጨረሻውን የመራጮችን ዝርዝር እንደተጠቃለለ በአረብኛ ቋንቋ በሚታተሙ ሦስት ጋዜጦች ካይሮ ውስጥ ይገለጣል፡፡
-
ስማቸው በስህተት በመጨረሻው ዝርዝር ውስጥ ያልተካተተ መራጮች ዝርዝሩ እንዲስተካከል ማመልከት ይችላሉ፡፡ ጉዳዩም ዐቃቤ መንበሩ በሚመራው ኮሚቴ ይታያል፡፡ ከምርጫ አስፈጻሚ መካከል የተመረጡ ሁለት አባላት አብረው ይሆናሉ፡፡ ከሁለቱ አንዱ ካህን ይሆናል፡፡ ይህ ኮሚቴ የሚሰጠው ውሳኔ የመጨረሻው ይሆናል፡፡ ነገር ግን በስድስተኛውና በሰባተኛው ተራ ቁጥር በአንቀጽ 9 የገለጥነውን መራጭ ኮሚቴው አለመቀበሉ አስፈላጊ መስሎ ከታየው የምርጫ አስፈጻሚ ኮሚቴው ተቀባይነት ያላገኙ መራጮችን ተክተው የሚመዘገቡ ሌሎች መራጮችን መውሰድ መብት አለው፡፡
አንቀጽ 11
-
ስማቸው በምርጫው ጠረንጴዛ ላይ የተካተተ መራጮች ስማቸው ሓላፊነታቸው ሥራቸው ዕድሜአቸው ወደ ምርጫ የገቡበት ጊዜ የምርጫ ቁጥራቸውን የሚያሳይ መታወቂያ ይሰጣቸዋል፡፡ ይህንን መታወቂያ የመስጠቱ ሓላፊነት የምዝገባ ኮሚቴው ሰብሳቢ ወይም የአጥቢያ ሜትሮፓሊን ወይም ጳጳስ ይሆናል ይህም መራጩ በሚኖርበት አካባቢ ነው፡፡
-
መራጮች መታወቂያቸውን ለመውሰዳቸው መፈረም ይኖርባቸዋል፡፡ መታወቂያውን የሰጠው ወገን ፊርማውን ያስቀምጣል፡፡ ከምርጫው አስቀድሞ ባሉት 15 ቀናት የሚከናወን ይሆናል፡፡
2. የምርጫ ሂደት
አንቀጽ 12
-
አስመራጭ ኮሚቴው ዐቃቤ መንበሩን ሰብሳቢ ሦስት ካህናት በቅዱስ ሲኖዶስ የተመረጡ ሦስት አካላት በሰያሚ ኮሚቴው /nomination committee/ የተመረጡ ከምርጫው ከሦስት ቀን አስቀድሞ ይሠየማሉ፡፡ የቃለ ጉባኤውን ሥራ ሰብሳቢው ደስ ያለውን ሰው በመሰየም ያስይዛል፡፡
-
በኮሚቴው ሰብሳቢ ጥያቄ የምርጫ ሂደቱን የሀገር ውስጥ ጉዳይ ሚኒስትር እንዲከታተለው ይደረጋል፡፡ ሰብሳቢው ከአቅም በላይ በሆነ ችግር ለመገኘት ባይቻለው ከሜትሮ ፓሊታን መካከል የሰብሳቢውን ሥራ ተክቶ ይሠራል፡፡ ከኮሚቴው አባላት የጎደለ ቢኖር ከአጠቃላይ ምርጫ ጉባኤው መካከል የሚተካ ሰውን ሰብሳቢው ይመርጣል፡፡
አንቀጽ 13
-
ምርጫው በሚካሄድበት ቀን አስቀድመን የገለጥነው ኮሚቴ በፓትርያርኩ ቤት መገኘት ይኖርበታል፡፡ ምርጫው ከ 3፡00 ሰዓት እስከ ቀኑ 11፡00 ሰዓት ድረስ ይከናወናል በቀኑ በ11ኛው ሰዓት ድምጽ መስጠት ያልቻለ መራጭ ቢኖር ኮሚቴው ዝርዝራቸውን ተናግሮ ሁሉንም ድምጽ ይሁንታ እስከሚያገኝ ሥራውን ይቀጥላል፡፡
አንቀጽ 14
-
ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን ከሚመጡ ድምጽ ሰጪዎች በስተቀር /እነርሱ በራሳቸው ወይም ሕጋዊ በሆኑ ወኪሎቻቸው አማካኝነት የሚፈጽሙት ሆኖ ስም ዝርዝርራቸው በምርጫ ጠረጴዛው ላይ ከሰፈረ ውጪ በሕጉ ላይ እንደተቀመጠው
- ሜትሮፓሊቲንና ጳጳሳት፡፡
- የንጉሡ ተወካይ፡፡
- በመላው ግብጽ የታወቁ 24 ሰዎች ይህም በንጉሡ በፕሬዝዳንቱ የሚሰየሙ ይካተታሉ፡፡
አንቀጽ 15
-
በምርጫ ጠረጴዛው ላይ አስቀድሞ የስም ዝርዝርራቸው ባለ መራጮች ቁጥር ልክ ካርዶች ይዘጋጃሉ፤ ካርዶቹ በሊቀ መንበሩ /በምርጫ ኮሚቴ ስብሰባው ማኅተም መታተም ይኖርባቸዋል፤ ለእያንዳንዱ መራጭም ይሰጣል፤ ወደ ምርጫው አደባባይ ሲመጡ ይዘው ይቀርባሉ፡፡ ካርዱ የመራጩ ስም የምርጫ ቁጥር ይኖረዋል፡፡ ድምጽ ሰጪው ካርዱን ለመውሰዱ ለዚህ ዓላማ በተዘጋጀው መዝገብ ላይ በፊርማው ያረጋግጣል፡፡
-
ድምጽ ለመስጠት ከተመዘገቡት ውስጥ ካርድ ያልወሰዱ ካሉ፣ ካርዱ የሌሉ ሰዎች ካርድ በሚቀመጥበት ኤንቨሎፕ ውስጥ ይቀመጣል፡፡ ለምርጫ ኮሚቴው ሊቀመንበርም ይሰጣል፡፡ ኤንቨሎፑን ካሸገ በኋላ ቀዶ ማኅተም ያደርግበታል፡፡
-
በአስመራጭ ኮሚቴው የተመረጡ 6 ድምጽ ሰጪዎች ያሉበት ኮሚቴ ከምርጫው 3 ቀን አስቀድሞ ካርዶቹን ያስረክባል ምርጫውንም ይቆጣጠራል፡፡
አንቀጽ 16
-
ድምጽ ሰጪዎች በአስመራጭ ኮሚቴ ፊት ሲቀርቡ ለጸሐፊው የምርጫ ካርዶቸውን መስጠት ይኖርባቸዋል፡፡ ጸሐፊው ካርዱን አትሞ ለዚህ ዓላማ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ይከታል፡፡ መራጮች የምርጫ ወረቀት ይጧቸዋል የመረጡትን ሰው ስም ይይዛል፡፡
-
የዕጣ መጣሉ ሁኔታ በተወሰነ አግባብ ውስጥ የሚካሄድ ነው፡፡ ድምጽ የሚሰጠው ሰው ለድምጽ መስጫ በተከለለ ምስጢራዊ ቦታ ሊመርጥ ያሰበውን ዕጩ ያስቀምጣል፡፡ ድምጽ ሰጪዎች በምርጫ ወረቀቱ ላይ ምልክት ባያስቀምጡ ማንነታቸውን የሚገልጽ ነገር ባይኖረው ወረቀቱ ዋጋ አይኖረውም፡፡
አንቀጽ 17
-
የምርጫ ሂደቱ ከተጠቃለለ በኋላ ኮሚቴው የመራጭ ሰዎችን ካርድ ይቆጥራል፡፡ የኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን ተወካዮች ቁጥር ከመራጮች ካርድ እና ከቀሪዎች ካርድ ጋር ተደምሮ የተመዝጋቢዎችን አጠቃላይ ቁጥር መስጠቱ ይመሳከራል ይህም የኢትዩጵያ ተወካዮች ቁጥር ጨምሮ ነው፡፡
-
ጸሐፊው ይህንን ሁኔታ በቃለ ጉባኤው ላይ ካሰፈረ በኋላ ኮሚቴው ድምጹን ይለያል ከምርጫው ጋር በተያያዘ ጉዳዮች ላይ ውሳኔውን ያሳልፋል፡፡ እያንዳንዱ መራጭ በሰጠው ድምጽ ላይ ያሰፈረውን አስተያየት ተአማኒነት ይመረመራል፡፡
-
ኮሚቴው የሚሰጠው ይሁንታ አስተያየት ምስጢራዊ ነው፡፡ ውሳኔውንም የሚተላለፈው በሚቆጠረው ድምጽ ይሆናል፡፡ የተሰጠው ድምጽ እኩል ሲሆን ዐቃቤ መንበሩ የሚሰጠው ውሳኔ ተፈጻሚ ይሆናል፡፡
-
የድምጽ ቆጠራው ከተጠናቀቀ በኋላ ሊቀ መንበሩ የመጨረሻዎቹን ሦስት እጩዎች ስም ዝርዝር ያሳውቃል፡፡ እነርሱም የብልጫውን ድምጽ ያገኙ ናቸው፡፡ የኮሚቴው ጸሐፊ ሁለት ኮፒ ቃለ ጉባኤውን ያረቅቃል ዐቃቤ መንበሩ ይፈርምበታል፡፡ የሀገር ውስጥ ጉዳይ ሚኒስትር ተወካዮችም ይፈርማሉ፡፡
-
ምርጫው በተካሄደበት እሑድ ምዝገባው ይካሄዳል፡፡ ይሄውም ከላይ ለተገለጸው ሚኒስትር መ/ቤት 1 ኮፒ ቃለ ጉባኤ ይላካል/ቀሪው ካይሮ በሚገኘው የመንበረ ፓትርያርክ ጽ/ቤት ይቀመጣል፡፡ የምርጫ ሂደት ወረቀቶች በኤንቨሎፕ ቀይ ማኅተም ታትሞባቸው በፓትርያርኩ ጽ/ቤት ይቀመጣሉ፡፡
አንቀጽ 18
-
በቤተ ክርስቲያኒቱ ሕግና ሥርዓት መሠረት ዐቃቤ መንበር ዕጣው የሚጣልበትን ሁኔታ ያመቻቻል፡፡ በዕጣ መጣሉ ሂደት ያሸነፈውን ዕጩ ስም ዐቃቤ መንበሩ ፈርሞበት ሁለት ኮፒ ቃለ ጉባኤ ይጻፋል፡፡ በምርጫ ኮሚቴው ስምና ፊርማ ይጸድቃል፡፡ የቅዱስ ሲኖዶስ አባላትም ፊርማቸውን ያስቀምጣሉ፡፡ የዕጩ ጥቆማ አስተባባሪ ኮሚቴም እንዲሁ ፊርማቸውን ያስቀምጣሉ፡፡ አንዲ ኮፒ ለሀገር ውስጥ ጉዳዮች ሚኒስትር ይላካል፡፡
-
በቤተ ክርስቲያኒቱ ሥርዓት መሠረት የተሾመው ፓትርያርክ በመላ ሀገሪቱ ይገለጣል፡፡
ምዕራፍ 4
ጠቅላላ ደንብና ከጊዜ ጋር የተያያዙ ደንቦች
አንቀጽ 19
አስፈላጊ ሆኖ ሲያገኘው የዕጩ አፈላላጊ ኮሚቴው /nomination committee/ በዚህ ሕግ ውስጥ የተቀመጠውን ጊዜ የማሳጠር ሥልጣኑ አለው፡፡ ይህም በጋራ በሚደረግ ውሳኔ ነው፡፡




ጻድቃንን ማሰብ ሥራቸውን መዘከር ክርስቲያናዊ ሕይወታችንን ያጐለምሳል፡፡ የበረከታቸው ተሳታፊ በማድረግ በነፍስ በሥጋ የሚታደገንን የሚረባን፤ የሚጠቅመን ይሆናል፡፡ ስለጻድቁ አባታችን ስለ ቅዱስ ተክለ ሃይማኖትም የምናስበው ከዚህ የተለየ አይደለም፡፡ በመንፈሳዊ አርአያነታቸው፣ በጸሎታቸውና በትምህርታቸው ከከበቡን የነፍስ ጠላቶች፤ ከርኲሳን መናፍስትና ከጨለማው ልጆች፣ ከክፉ ሰዎች ሽንገላና ተንኰል ለመሰወርና ለመጠበቅ ከእግዚአብሔር የተቀበሉት ሥልጣን ምን ጊዜም ይሠራል፡፡ በጻድቃን መኖር ሀገር ከጥፋት ትድናለች፡፡ የጻድቃንን ስም ጠርቶ እግዚአብሔርን በመለመን በረከትና ረድኤት ይገኛል፡፡ ስለጻድቃን ብሎ እግዚአብሔርም ምሕረቱን ያድላል፡፡ ስለዚህ ነው ቤተ ክርስቲያናችን ጻድቃንን እንድናስባቸው፣ በስማቸውም ለድሆችና ለጦም አዳሮች እንድንመጸውት መታሰቢያቸውን እንድናደርግ የምትመክረን፤ የምታስተምረን፡ ጻድቁ ተክለ ሃይማኖትንም የምናስባቸው ከዚሁ የቤተ ክርስቲያን አስተምህሮ በመነሣት ነው፡፡ ማቴ.10፥41-42 ጻድቃንን በሕይወተ ሥጋ ሳሉም ቢሆን፤ ከሞቱም በኋላ በአጸደ ነፍስ በጸሎታቸው ለሚታመኑ፣ በቃል ኪዳናቸው ለሚማጸኑ፣ የድኅነተ ሥጋ፣ የድኅነት ነፍስ ምክንያት ናቸው፡፡
በጊዜው ከነበሩት አበምኔት ከአባ ዮሐኒ ቆብና አስኬማ ተቀብለው በገድል በትሩፋት መንፈሳዊ ተጋድሎአቸውን ቀጠሉ፡፡ ከደብረ ዳሞ ገዳም ወደሌላ ለመሄድ ሲነሡ፤ ክቡር አባታችን ተክለሃይማኖት አበምኔቱና መነኰሳቱ ሲሸኟቸው ሳለ፤ አርባ ክንድ ርዝመት ባለው ገመድ ገደሉን ለመውረድ እንደጀመሩ፤ ገመዱ ከካስማው ሥራ በመቆረጡ እንዳይወድቁ በተሰጣቸው ስድስት የብርሃን ክንፎች እየበረሩ፤ ክንፎቻቸውን እያማቱ ሦስት ምዕራፍ ሄደው ዐርፈዋል፡፡ ከዚያም ወደ ገዳመ ዋሊ ገብተዋል፡፡ በዚህም ጊዜ ነቢዩ ኢሳይያስ የተናገረው ትንቢት “ለደካማ ኀይልን ይሰጣል፤ ጉልበት ለሌለው ብርታትን ይጨምራል፡፡ ብላቴኖች ይደክማሉ፤ ይታክቱማል፡፡ ጐበዛዝትም ፈጽመው ይወድቃሉ፡፡ እግዚአብሔርን በመተማመን የሚጠብቁ ግን ኀይላቸውን ያድሳሉ፤ እንደ ንስርም በክንፍ ይወጣሉ፤ ይሮጣሉ፤ አይታክቱም፡፡ “ኢሳይያስ 40፥29-31 ያለው ቃል በጻድቁ በቅዱስ ተክለ ሃይማኖት ሕይወት ሊተረጐም ችሏል፡፡ ከ1266-1267 ዓ.ም. አንድ ዓመት ሙሉ ገዳማተ ትግራይን በመጐብኘት ኢየሩሳሌምንና ግብፅ ያሉ ቅዱሳት መካናትን ሲጎበኙ ቆይተዋል፡፡ ከዚህ በኋላ አንድ ወር ሙሉ “ዳዳ” በተባለ ስፍራ ይመለክ የነበረውን 75 ክንድ ዘንዶ በጸሎት ኀይል በተአምራት ገድለውታል፡፡ አርባዓቱ እንስሳ /በኪሩቤልና በሱራፌል/ ስም ቤተ ክርስቲያን አንፀው፤ ታቦተ ሕግ /ጽላተ ሕግ/ አስገብተዋል፡፡ ከሴቶችና ከልጆች ሌላ፤ ሦስት ሺህ በጣዖት የሚያመልኩ ወንዶችን መልሰው፤ አጥምቀው አቊርበዋል፡፡ በዚህም ተግባራቸው መድኀኒታችን “እነሆ እባቡንና ጊንጡን ትረግጡ ዘንድ በጠላትም ኀይል ሁሉ ላይ ሥልጣን ሰጥቻችኋለሁ፥ የሚጎዳችሁም ምንም የለም” ሉቃስ 10፥19 ያለው ቃል ተፈጽሞላቸዋል፡፡ ክቡር ዳዊት በመዝሙር 90፥13-14 “በተኲላና በእባብ ላይ ትጫማለህ፤ አንበሳውና ዘንዶውን ትረግጣለህ፡፡ በእኔ ተማምኗልና አስጥለዋለሁ፤ ስሜንም ዐውቋልና እጋርደዋለሁ፡፡” የተባለው ትንቢት ተፈጽሞላቸዋል፡፡ ከ1267-1289 ዓ.ም. በደብረ ሊባኖስ ካለችው ገዳመ አስቦ ዋሻ በመግባት፤ ስምንት ጦሮችን /ሁለቱን በፊት፣ ሁለቱን በኋላ ሁለቱን በቀኝ፣ ሁለቱን በግራ አስተክለው እጆቻቸውን በትእምርተ መስቀል በመዘርጋት የክርስቶስን ሕማምና ሞት፣ ነገረ መስቀልን በማሰብ በተመስጦ ሌትና ቀን ያለማቋረጥ በጾምና በጸሎት በአርምሞ ተወስነው ሲጋደሉ፤ ከቊመት ብዛት የተነሣ ጥር 4 ቀን 1289 ዓ.ም. አንዲቱ የእግራቸው አገዳ ተሰብራለች፡፡ ደቀ መዛሙርቱም የመንፈሳዊ አባታቸውን ስባረ ዐፅም አክብረው በሥርዓት አኑረውታል፡፡ እግራቸው እስኪሰበር የቆዩባቸው ዓመታት በቊጥር ሃያ ሁለት ናቸው፡፡ በመዓልትና በሌሊት በትጋትና በቊመት በተጋድሎ ብዛት፤ አንዲት የአገዳ እግራቸው ስትሰበር፤ ዕድሜያቸው 92 ዓመት ሆኗቸው ነበር፡፡
የያዘችውን ሰበን ሰጥታ ሰደደችው፡፡ ከዚህ በኋላ ሄዶ፤ “የእመቤታችን ነገር እንደምን ሆነ?” አላቸው “ሥጋዋን አግኝተን ቀበርናት” አሉት፡፡ እርሱም “ሞት በጥር በነሐሴ መቃብር ተዉ ይህ ነገር አይመስለኝም” አላቸው፡፡ ቅዱስ ጴጥሮስ “አንተ እንጂ ልማድህ ነው፡፡ አንተ ብቻ ተጠራጥረህ አትቀርም፤ አንተ እየተጠራጠርህ ሰውን ሁሉ ስታጠራጥር ትኖራለህ” አለው፡፡ እርሱም የያዘውን ያውቃልና ጸጥ ብሎ ይሰማቸዋል፡፡ ከዚህ በኋላ ቅዱስ ጴጥሮስ ተቆጥቶ ሂዶ መቃብሩን ቢከፍተው የእመቤታችን ሥጋዋን አጥቷል፡፡ በዚህም ምክንያት ደንግጦ ቆመ፡፡ ይህን ጊዜ ቅዱስ ቶማስ “አታምኑኝም ብዬ ነው እንጂ እመቤታችንስ ተነሣች ዐረገች” አላቸው፡፡ የያዘውንም ሰበን እያሳያቸው፡- “ቅዱስ ሥጋዋን የገነዛችሁበት ጨርቅ /ሰበን/ ይህ አይደለምን” ብሎ ሰበኑን ሰጣቸው፡፡ ይህንንም ለበረከት ተካፍለውታል፡፡ ከዚህ በኋላ በዓመቱ “ቶማስ ትንሣኤሽን ዕርገትሽን አይቶ እኛ ሳናይ በማለት ጾም ጀመሩ፡፡ በ16ኛው ቀን እመቤታችንን መንበር ቅዱስ ጴጥሮስን ንፍቅ ቄስ፣ እስጢፋኖስን ሠራዒ ዲያቆን አድርጎ ራሱ ቀድሶ አቁርቦአቸዋል፡፡
ቦታ ተሰይሟል፡፡
የቤተ ክርስቲያናችን የሥርዓትና የሕግ መጽሐፍ የሆነው ፍትሐ ነገሥት በ15ኛው አንቀጹ መግቢያ ላይ “ጾምስ በሕግ ውስጥ በታወቀው ጊዜ የሰው ከምግብ መከልከል ነው፡፡ በደሉን ለማስተሥረይ ዋጋውን ለማብዛት እርሱን ወዶ ሕጉን ለሠራለት እየተታዘዘ የፈቲዉን ኀይል ያደክምበት ዘንድ ለነባቢትም ነፍስ ትታዘዝ ዘንድ፤” በማለት የጾምን ምንነትና ጥቅም አጠር አድርጎ ያብራራል፡፡