ዐቢይ ጾም

‹ዐቢይ›› የተባለው የዓለማት ፈጣሪ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ለአርአያነት ጾሞ የመሠረተው ጾም ስለሆነ ነው፡፡ በኦርቶዶክሳዊት ቤተ ክርስቲያን ካሉት ሰባት የአዋጅ አጽዋማት ረጅሙ (፶፭ ቀን ያለው) ስለሆነ ደግሞ ‹‹ሁዳዴ›› ይባላል፡፡ ኢትዮጵያዊው የዜማና የቅዱሳት መጻሕፍት ሊቅ ቅዱስ ያሬድ በዐቢይ ጾም ውስጥ የሚገኙትን ስምንት ሣምንታት ለትምህርት፣ ለአዘክሮና ለምስጋና በሚመች መልኩ ልዩ ስያሜዎች ሰጥቷቸዋል፡፡ ስለሆነም በእያንዳንዱ ሳምንት (ሰንበት) የሚነበቡ፣ የሚተረጎሙ፣ የሚዘከሩ፣ የሚዘመሩ ልዩ ልዩ መጽሐፍ ቅዱሣዊ ኩነቶችና አስተምህሮዎች አሉ፡፡

‹‹ከዚያ ወዲያ ኢየሱስ ከዲያብሎስ ይፈተን ዘንድ መንፈስ ወደ ምድረ በዳ ወሰደው›› (ማቴ.፬፥፩)

በወንጌል ቅዱስ ማቴዎስ ስለ ጌታችን መድኃኒታችንን ኢየሱስ ክርስቶስ ዐቢይ ጾም ሲጽፍ  ‹‹ከዚያ ወዲያ›› በማለት ከጀምረ በኋላ እርሱ ለሰዎች ድኅነት ሲል ለዐርባ ቀንና ሌሊት ያለ መብልና መጠጥ በጾም በምድረ በዳ እንደቆየ ይገልጽልናል፡፡

የነነዌ ጾም

ነነዌ የሜሶፖታምያ ከተሞች ከሆኑት መካከል አንዷ ናት፡፡ ከሞሱል ከተማ በተቃራኒ ከባግዳድ ሰሜን ምዕራብ ፫፻፶ ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ እንደ ነበረች በታረክ ይነገራል፡፡ በ፵፻ (ዐራት ሺህ) ቅድመ ልደተ ክርስቶስ በናምሩድ በኩል ከተቆረቆረችም በኋላ በ፲፻፬፻ (አንድ ሺህ ዐራት መቶ) ቅድመ ልደተ ክርስቶስ የአሦራውያን ዋና ከተማ ሆናለች፡፡ (ዘፍ.፲፥፲፩፣፪ኛነገ.፲፱፥፴፮)

በከተማዋም ታዋቂ የነበረ አስታሮት የተባለ የጣዖት ቤተ ነበረ፡፡ በዚህች ከተማ የሚኖሩት ሰዎች የሚሠሩት ክፋትና ኃጢአት እጅግ ከመብዛቱ የተነሣ ጽዋው ሞልቶ መጥፊያቸው ስለ ደረሰ ለፍጥረቱ ርኅራኄ ያለው እግዚአብሔር ግን ንስሓ ይገቡ ዘንድ ነቢዩ ዮናስን ልኮላቸዋል፡፡ ይህ ነቢይ ከአሕዛብ ወደ አሕዛብ ወደ ንስሓ ይጠራቸው ዘንድ ነበር የተላከ ነው፡፡

ጾመ ገሀድ

የከበሩ አባቶቻችን ሐዋርያት የጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የልደትና የጥምቀት በዓል በረቡዕ ወይም በዓርብ ቀን ቢሆን በበዓለ ኃምሳ የሚበላውን የጥሉላት መብል በጥዋት በመብላት ምእመናን ሁሉ በዓሉን እንዲአከብሩ አዝዘዋል፤ ይህም ጾመ ገሀድ ነው፡፡ እነዚህ ሁለቱ የእግዚአብሔር ታላላቅ በዓላቶቹ ናቸውና።

ዘመነ ስብከት

ዘመነ ስብከት ከጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የልደት በዓል በፊት ከታኅሣሥ ፯ ጀምሮ እስከ ፳፱ ያለው ወቅት ነው፡፡ ሳምንታቱም ስብከት፣ ብርሃንና ኖላዊ ይባላሉ፡፡ በዚህም ወቅት ስለ ጌታችን ኢየሱስ  መወለድ ነቢያት የተናገሩት ትንቢት ይሰበክበታል፡፡

ጾመ ነቢያት

ከሰባቱ የአዋጅ አጽዋማት መካከል አንዱ የሆነውን ጾመ ነቢያት በየዓመቱ ከኅዳር ፲፭ ጀምሮ እስከ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የልደት በዓል ድረስ በአምላካችን ቅዱስ ፈቃዱ እንጾማለን!

ወርኃ ጽጌ

በቅድስት ቤተ ክርስቲያናችን አስተምህሮ መሠረት ከመስከረም ፳፮ እስከ ኅዳር ፮ ያለው ወቅት ወርኃ ጽጌ (የጽጌ/የአበባ ወር) ይባላል፡፡ በወርኃ ጽጌ አበባዎች ያብባሉ፤ ፍሬም ያፈራሉ፤   በዚህም ወቅት እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም፣ እንዲጠብቃት ከታዘዘው አረጋዊው ዮሴፍ ጋር ስትኖር መልኳ አንዳንድ ጊዜ እንደ ጽጌረዳ አበባ ቀይ ሁና፣ በሌላ ጊዜ ደግሞ እንደ ሮማን አበባ ነጭ ሁና ስትታየው፣  ቀይ የነበረው መልኳ ተለውጦ እንደ ሮማን አበባ ጸዓዳ ነጭ፣ ነጭ የነበረው እንደ ጽጌረዳ ቀይ ሲለወጥ በመደንገጥ እርሷ መሆኗን ለማረጋገጥ ‹‹ማርያም›› ብሎ እየጠራ ያረጋግጥ ነበር፡፡ ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ ስለዚህ ምሥጢር ሲያስረዳ ‹‹መልኳ እንደ ጽጌረዳና እንደ ሮማን አበባ ይለዋወጥበት ስለነበር በአንድ ዓይነት መልክ አላወቃትም›› ብሏል፡፡ በዚህም ሊቃውንተ ቤተ ክርስቲያን እመቤታችንን በአበባ፣ ጌታችንን ደግሞ በፍሬ እየመሰሉ ለማመስገንና ለማወደስ በሚያስችል ምሥጢር የስደቱ ጊዜ በወርኃ ጽጌ እንዲዘከር አድርገዋል፡፡ እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ለዘለዓለሙ የማይደርቀውን የሕይወት ፍሬ ኢየሱስ ክርስቶስን ያስገኘችልን ንጽሕት የማትጠወልግ አበባ ናትና፡፡

ወርኃ ጳጉሜን

የሰው ልጅ እግዚአብሔር አምላኩ ባደለው ሥጦታ ‹ጊዜ› በሕይወት ዘመኑ በበጎ ምግባር እንዲኖርና በጸሎት በጾም እንዲተጋ በዓመታት፣ በወራት እና በቀናት ምልልስ በሚያገኘው ዕድል ዘወትር ፈጣሪውን ደስ የሚያሰኝ ሥራ ሊሠራ እንዲገባ የጊዜ ጭማሪ ተደረገለት፡፡ ይህችም የጭማሮ ጊዜ እስከ ዕድሜው(ዘመኑ) መጨረሻ ከኃጢአት በሙሉ ይነጻ እንዲሁም ጸጋ በረከትን ያገኝ ዘንድ የቀናት ምርቃት ሆነችለት፤ ‹የጳጉሜን ወር› (ወርኃ ጳጉሜን) ተብላም ተሰየመች፡፡ …

‹‹ከሚያልፈው ዓለም ወደማያልፈው ዓለም ተሻገረች››(ቅዱስ ያሬድ)

ቅድስት ድንግል ማርያም በምድር ላይ ለ፷፬  ዓመት በሕይወተ ሥጋ ከኖረች በኋላ ቅዱስ ያሬድ እንደተናገረው በጥር ፳፩ ቀን ከሚያልፈው ዓለም ወደ ማያልፈው ዓለም ተሻግራለች፡፡ «ፈለሰት እምዘይበሊ ኀበ ኢይበሊ፤ ከሚያልፈው ዓለም ወደማያልፈው ዓለም፣ (ከምድር ሕይወት ወደ ሰማያዊ ሕይወት) ተሻገረች» እንዲል፤  (ዚቅ ዘቅዱስ ያሬድ ነሐሴ ፲፮)…
ከዚህም በኋላ ቅዱሳን መላእክት ክቡር ሥጋዋን በገነት በዕፀ ሕይወት ሥር አኖራት፤ ከጥር ፳፩ እስከ ነሐሴ ዐሥራ ስድስት ቀን ለሁለት መቶ አምስት ቀናት ቆይታለች፡፡ …

የሐዋርያት ጾም

ሐዋርያት ወንጌለ መንግሥት እንዲስፋፋና በሕዝብም ሆነ በአሕዛብ ዘንድ አገልግሎታቸው የሠመረ እንዲሆን መንፈስ ቅዱስን በተቀበሉ በበዓለ ሃምሳ ማግሥት  ጾም ጀመሩ፡፡ ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ለሐዋርያቱ በሰጣቸው ሥልጣን ድውያንን መፈወስና አጋንንትን ማውጣት እንዲሁም የተለያዩ ገቢረ ተአምራትን ይፈጽሙ ዘንድ ጸሎትና ጾም ያስፈልጋቸው ነበርና፡፡ በማቴዎስ ወንጌል እንደተጻፈው ጌታችን ጋኔን ያለበትን ልጅ ካዳነው በኋላ ሐዋርያቱ ስለምን እነርሱ ጋኔን ከሰው ማውጣት እንዳልቻሉ በጠየቁት ጊዜ እንዲህ ሲል መልሶላቸዋል፤ ‹‹…ይህ ዓይነቱ ግን ያለጾምና ጸሎት አይወጣም፡፡›› (ማቴ.፲፯፥፳፩)