ዕረፍቱ ለቅዱስ አትናቴዎስ
ቅዱስ አትናቴዎስ የተወለደው ግብጽ ውስጥ እስክንድርያ ነው:: ሐናፊ ከሚባል የእስላም ነገድና ከአረማውያን ወገን በመሆኑ በልጅነቱ ክርስትናን መማር አልቻለም ነበር::አንድ ቀን ግን ክርስቲያን ሕፃናት እርስ በእርሳቸው እየተጫወተ ተመለከተ። ጨዋታቸውም የሥርዓተ ቤተ ክርስቲያን በመሥራት ስለነበር ከመካከላቸው ዲያቆናትንና ኤጲስ ቆጶሳትን ሲመርጡ እንዲያጫውቱት ለመናቸው። ነገር ግን ‹‹አንተ አረማዊ ነህና ከእኛ ጋር አትደመርም›› በማለት ከለከሉት፡፡አትናቴዎስም ‹‹ክርስቲያን እሆናለሁ›› ባላቸው ጊዜ ሕፃናቱ ደስ ተሰኝተው ማዕረጋቸውን ለመለየት ዕጣ ተጣጣሉ::ለአንዱ ቄስ፣ ለአንዱም ዲያቆን መሆን ሲደርሳቸው ለአትናቴዎስ ፓትርያርክ መሆን ስለ ደረሰው ሌሎቹ ሕፃናት ይሰግዱለት ጀመር::…