ቃና ዘገሊላ

ቅድስት ቤተ ክርስቲያናችን በጥር ፲፪ ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በቃና ዘገሊላ በተደረገ ሠርግ ቤት ያደረገውን ተአምር በማሰብ በዓልን ታደርጋለች፡፡ ጌታችን ከጥምቀቱ በኋላ በዶኪማስ ሠርግ ቤተ ከእናቱ ቅድስት ድንግል ማርያም እንዲሁም ከደቀ መዛሙርቱ ጋር ታጋብዞ በነበረበት ጊዜ ለእንግዶች ወይን ጠጅ አለቀባቸው፡፡

‹‹በዮሐንስ ሊጠመቅ ከገሊላ ወደ ዮርዳኖስ መጣ›› (ማቴ.፫፥፲፫)

ውድ የእግዚአብሔር ልጆች! እንዴት አላችሁ! እንኳን አደረሳችሁ! የጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ልደት በዓል እንዴት አለፈ? ልጆች! አሁን ያላችሁበት ወቅት የዓመቱ አጋማሽ የፈተና ወቅት ነው! ፈተናውን በደንብ አድርጋችሁ መሥራት አለባችሁ! መቼም በርተታችሁ ስታጠኑና ያልገባችሁን ስትጠይቁ ስለነበር በፈተና የሚቀርቡላችሁን ጥያቄዎች በትክክል እንደምትመልሱ አንጠራጠርም! ምክንያቱም የምትጠየቁት የተማራችሁትን ስለሆነ በአንዳች ነገር እንዳትዘናጉ!

ታዲያ ልጆች! ፈተናውን የምትሠሩት ጥሩ ማርክ ለማምጣት ብቻ ሳይሆን ለእውቀትም መሆን አለበት፡፡ ዕውቀት ማለት በተግባር መተርም መሆኑን እንዳትዘነጉ! መልካም! ልጆች ዛሬ ስለ ጌታችንን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ጥምቀት እንማራለን፡፡

“ኑ፥ እንውረድ፤ አንዱ የአንዱን ነገር እንዳይሰማው ቋንቋቸውን በዚያ እንደባልቀው” (ዘፍ.፲፩፥፯)

አጋእዝተ ዓለም ሥላሴ በኃጢያት የተገነባውን የሰናኦር ግንብ ያፈረሱበትና አንድነታቸውንና ሦስትነታቸውን በግልጽ ያሳዩበት ቀን ጥር ሰባት የከበረ በዓል ነው፤

በዓለ ግዝረት

በከበረች በጥር ስድስት ቀን የክብር ባለቤት ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ወደ ቤተ ግዝረት በመግባት የኦሪትን ሕግ ፈጸመ፤ ልሳነ ዕፍረት ሐዋርያው ጳውሎስ “ጌታ ክርስቶስ በሥጋው ግዝረትን ተቀበለ፤ ለአባቶች የተሰጠውን ቃል ኪዳን ይፈጽም ዘንድ” ብሎ እንደተናገረ።

‹‹የምሥራች እነግራችኋለውና አትፍሩ›› (ሉቃ.፪፥፲)

ውድ የእግዚአብሔር ልጆች እንዴት አላችሁ? እንኳን አደረሳችሁ! የልደት በዓል ዝግጅት እንዴት ነው? ልጆች ትምህርተስ እየበረታችሁ ነውን? አሁን የዓመቱ አጋማሽ የፈተና ወቅት በመሆኑ መምህራን ሲያስተምሩን ከመጻሕፍት ስናነብ የነበሩትን ምን ያህሉን እንደተረዳን የምንመዘንበት ጊዜ ነው! መቼም በርተታችሁ ስታጠኑና ያልገባችሁን ስትጠይቁ ስለ ነበር በፈተና የሚቀርቡላችሁን ጥያቄዎች በትክክል እንደምትመልሱ ተስፋችን እሙን ነውና በርቱ! ያለንበት ጊዜ ደግሞ የበዓላት ወቅት ስለሆነ በዚህ እንዳትዘናጉ፣ ከሁሉ ቅድሚያ ትኩረት ለትምህርት መስጠት አለባችሁ።፡ ነገ አገር ተረካቢዎችና ታሪክን ጠባቂዎች ስለምትሆኑ በርቱና ተማሩ!

ታዲያ ልጆች ዕውቀት ማለት በተግባር መተርጎም መሆኑን እንዳትዘነጉ! አንድ ሰው ተማረ፤ አወቀ ማለት ክፉ ነገር ከማድረግ ተቆጠበ፤ ሰዎችን ረዳ (ደገፈ)፤ ለሰዎች መልካም ነገርን አደረገ፤ ሌላውን ወደደ ማለት ነው፤ መማራችሁ ለዚህ መሆን አለበት፡፡ ቅን፣ ደግ፣ አስተዋይ እንዲሁም ወገኑን የሚወድ ሰዎች ሆናችሁ ለመኖር ሁል ጊዜ መበርታት አለባችሁ:: መልካም ልጆች! ዛሬ ስለ ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ልደት እንማራለን!

“ተክለ አብ፣ ተክለ ወልድ፣ ተክለ መንፈስ ቅዱስ”

የካህን ልጅ ካህን፣ ምድራዊ የሆነ ሰማያዊ፣ ሰው ሲሆን መልአክ፣  ከሱራፌል ጋር የእግዚአብሔርን ዙፋን ያጠነ፣ ከመላእክት ጋር የተባበረ፣ ግዙፍ ሲሆን የረቀቀ፣ ባሕታዊ ሲሆን መምህር፣ ኢትዮጵያን በወንጌል ያበራ፣ የምድር ጨው፣ ስለአባታችን ተክለ ሃይማኖት ይህን እወቁ!

የፀጋ ዘአብ ዘር ምን ያህል ቡርክት ነች፤ የእግዚእኃረያ ማህፀን ምን ያህል ለምለም ነች!? አንደበቱ ለምስጋና የተፈታ፣ መላእክት የሚደሰቱበት፣ የሃማኖት ተክል፣ በዛፍ ጥላ ከፀሐይ ሙቀት እንድንጠለል የሃይማኖት ጥላ የሆነ፣ የበረከት ፍሬ፣ የበረከት ምንጭ፣ የጽዮን ደስታ፣ ፍስሐ ጽዮንን አስገኝተዋልና።

በዓታ ለማርያም

ታኅሣሥ በባተ በሦስተኛው ቀን የሚታሰበውና የሚከበረው በዓል ‹‹በዓታ ለማርያም›› በመባል ይታወቃል፡፡ ከእናቷ ከቅድስት ሐና እና ከአባቷ ቅዱስ ኢያቄም በስዕለት የተወለደችው እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ወደ ቤተ መቅደስ የገባችበት ዕለት የከበረ እንደመሆኑ ቅድስት ቤተ ክርስቲያናችን በድምቀት ታከብረዋለች፡፡

ወንጌላዊው ቅዱስ ሉቃስ

በሀገረ አንጾኪያ ከአሕዛብ ወገን የተለወደው አይሁዳዊው ሉቃስ ከሰባ ሁለቱ አርድእት የተቆጠረ ባለ መድኃኒትና ወንጌልን የጻፈ ቅዱስ ሐዋርያ ነው፡፡ ሊቃውንተ ቤተ ክርስቲያን በወንጌል ትርጓሜያቸው ስሙ ‹ዓቃቤ ሥራይ› ወይም ‹ባለ መድኃኒት› የሚል ትርጉም በውስጡ የያዘ መሆኑን ያስረዳሉ፡፡ በላቲን ቋንቋ ‹ሉካስ› ማለት ‹ብርሃናማ፣ ብርሃን የያዘ› ማለት ነው፡፡ መጽሐፈ ስንክሳር ደግሞ ብልህና ጥበበኛ በማለት ይገልጸዋል፡፡

ቅዱስ ዮሐንስ ሐጺር

በዐሥራ ስምንት ዓመት ዕድሜው የመነኮሰ፣ ትዕግሥቱ እጅግ የበዛ እንዲሁም የመታዘዝ ጸጋ የተሰጠው ቅዱስ አባታችን ዮሐንስ ሐጺር የዕረፍት መታሰቢያ ጥቅምት ሃያ ቀን ነው፡፡ ሊቃውንተ ቤተ ክርስቲያን እንደሚገልጹትም ይህ ጻድቅ ከቅዱሳን አባቶች መካከል በቁመት እንደ እርሱ አጭር ስላልነበረ ‹‹ቅዱስ ዮሐንስ ሐጺር፤ አጭሩ አባ ዮሐንስ›› ተብሏል፡፡ የእርሱን ቁመትና የቅድስና ሕይወቱን ሲያነጻጽሩም ‹‹ቁመቱ እጅግ ያጠረ ጽድቁ ግን ከሰማይ የደረሰ ቅዱስ ዮሐንስን ሰላም ሰላም እንለዋለን›› በማለት ተናግረዋል፡፡

ሊቀ ዲያቆናትና ቀዳሜ ሰማዕት ቅዱስ እስጢፋኖስ

ውድ የእግዚአብሔር ልጆች እንዴት አላችሁልን? ትምህርት እንዴት ነው? መቼም በክረምቱ የዕረፍት ጊዜያችሁ ትምህርት እስኪከፈት በጣም ጓጉታችሁ እንደነበር እናስባለን! ይኸው ተከፈተላችሁ! እንግዲህ በርትታችሁ ከአሁኑ መማር፣ ማጥናት፣ የቤት ሥራን መሥራት፣ ያልገባችሁን መጠየቅ ይገባችኋል፡፡ ገና ነው እያላችሁ እንዳትዘናጉ ጥናቱን አሁኑኑ ጀምሩ! የጨዋታም ሆነ ቴሌቪዥን የምታዩበት ጊዜ ከትምህርታችሁ ጋር በማይጋጭ መልኩ መሆን አለበት፡፡ ከሁሉም ትምህርታችሁን አስቀድሙ! ውድ እግዚአብሔር ልጆች! ለዛሬ ያዘጋጀንላችሁ የሊቀ ዲያቆናትና የቀዳሜ ሰማዕት ቅዱስ እስጢፋኖስን ታሪክ ነው፡፡