የኒቂያ ጉባኤ

በቢታንያ አውራጃ፤  ጥቁር ባሕር ወደብ አካባቢ የምትገኘው ኒቂያ በባሕርም ሆነ በየብስ ለሚጓዙ ሰዎች እጅግ ተስማሚ ከተማ እንደነበረች ቅዱሳት መጽሐፍት ይጠቅሳሉ፡፡ የእስክንድርያ ንጉሠ ነገሥታት መናገሻቸውን ወደ ቁስጥንኒያ እስከዛወሩበት ዘመነ መንግሥት ድረስ ከኒቂያ በ፴፪ …

የ፳፻፲፫ መስቀል ደመራ በዓል በመስቀል አደባባይ

የ፳፻፲፫ መስቀል ደመራ በዓል የኮሮና በሽታ ወረርሽኝን ለመከላከል የሃይማኖት አባቶችን ጨምሮ አምስት ሺህ ተሳታፊዎች ብቻ  በተገኙበት በአዲስ አበባ መስቀል አደባባይ ተከብሯል፡፡  

መስቀል ብርሃን ለኵሉ ዓለም

ለ፭፼፭፻ ዘመናት የሰው ዘር በኃጢአት ሰንሰለት ታስሮና በጨለማ ተውጦ በነበረበት ዓመተ ፍዳ እግዚአብሔር ወልድ ለዓለም ድኅነት የተሰዋበት ግማደ መስቀሉን ‹‹መስቀል ብርሃን ለኵሉ ዓለም፤ መስቀል የዓለም ብርሃን ነው›› እያልን እንዘክረዋለን፡፡

ዕረፍቱ ለሊቀ ነቢያት ሙሴ

እስራኤላውን በግብፅ ባርነት በተገዙበት ዘመን ፈርዖን እስራኤላውያን ወንድ ልጅ ሲወልዱ እንዲገደል በአዋጅ አስነገረ፡፡ የሙሴም እናት ልጇ በፈርዖን ትእዛዝ መሠረት እንዳይገደልባት ስለ ፈርዖን ትእዛዝ ፍራቻ ልጇን በቅርጫት አድርጋ ወንዝ ውስጥ ጣለችው፡፡ …

ርእሰ ዐውደ ዓመት

እነሆ ለ፳፻፲፫ ዓ.ም. ዘመነ ማቴዎስ ዐውደ ዓመት እንደርስ ዘንድ የአምላካችን እግዚአብሔር ፈቃዱ ሆነ፤ ቅድስት ቤተ ክርስቲያንም በሥርዓቱ መሠረት የበዓላቱና የአጽዋማቱ መደብ የሚታወቅበትና የዘመናቱ ሂደት ተቀምሮ የሚታወጅበት ዕለት መስከረም አንድ ቀን ርእሰ ዐውደ ዓመትን ታከብራለች፡፡

በዓለ ቅዱስ ሩፋኤል

በወርኀ ጳጉሜን ከሚታሰቡ እና ከሚከበሩ በዓላት መካከል በየዓመቱ ጳጕሜን ፫ ቀን የሊቀ መላእክት የቅዱስ ሩፋኤል ዓመታዊ ክብረ በዓል በመላው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ አብያተ ክርስቲያናት በልዩ ልዩ መንፈሳዊ ሥነ ሥርዓት ይከበራል፡፡

ልደቱ ለአቡነ ዘርዐ ብሩክ

በትንቢት ‹‹ከአንዲት ሴት ልጅ በጸሎቱ ዓለምን የሚያድን፣ በአማላጅነቱ ነፍሳትን የሚዋጅ ልጅ ይወለዳል›› ተብሎ ከተነገረ ከብዙ ዘመን በኋላ እግዚአብሔርን የምታመልክ ስሟ ማርያም ሞገሳ የምትባል ሴት ልጅ ተወለደች:: ያችንም ሴት ልጅ እናትና አባቷ ለአቅመ ሔዋን እስክትደርስ ድረስ እግዚአብሔርን በመፍራትና በዕውቀት አሳደጓት:: ዕድሜዋም ለትዳር ሲደርስ እናትና አባቷ እግዚአብሔርን ለሚፈራ ስሙ ደመ ክርስቶስ ለሚባል ሰው ዳሯት::

የአቡነ ተክለሃይማኖት በዓለ ዕረፍት

በነሐሴ ፳፬ በዓለ ዕረፍቱን የምናከብረው የጻድቁ አባታችን አቡነ ተክለ ሃይማኖት ታሪክ እንዲህ ነው፤

የእመቤታችን በዓለ ዕርገት

እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ያረገችበት ዕለት ነሐሴ ዐሥራ ስድስት ቀን በቤተ ክርስቲያናችን ይከበራልና እኛም ስለዕርገቷ እንዲህ እንዘክራለን፤…

በዓለ ደብረ ታቦር

ጌታችን መድኀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በደብረ ታቦር ብርሃነ መለኮቱን፣ ክብረ መንግሥቱን መግለጡን በማሰብ በየዓመቱ ነሐሴ ፲፫ ቀን በዓሉ በድምቀት ይከበራል፡፡ ይህ በዓል በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ምእመናን ዘንድ ‹ቡሄ› በመባል ይታወቃል፡፡ ቡሄ ማለት ‹ገላጣ› ማለት ነው፡፡ በአገራችን ክረምቱ፣ ጭጋጉ፣ ደመናው ተወግዶ የብርሃን ወገግታ የሚታይበት በዚሁ በዓል አካባቢ ስለ ሆነ በዓሉ ‹ቡሄ› ተብሎ ይጠራል፡፡ በዓለ ደብረ ታቦር ጌታችን ምሥጢረ መለኮቱን የገለጠበት፤ ብርሃን የታየበትና ድምፀ መለኮቱ የተሰማበ  ዕለት ስለ ሆነ ‹የብርሃን› ወይም ‹የቡሄ› በዓል ይባላል፡፡