የምእመናን ድርሻ በቤተ ክርስቲያን

በዓል በሚውልባቸው ዕለታት መደበኛ ሥራዎችን አቁመን ለበዓሉ የሚገቡና መንፈሳዊ በሆኑ ክንውኖች ልናሳልፋቸው የሚጠበቅብን ሲሆን በሥርዓቱ መሠረት ልናከብር ይገባናል።

‹‹ልጅነቴ!››

ውድ የእግዚአብሔር ልጆች! እንዴት አላችሁልን! የጌታችን የመድኃኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስ የጥምቀቱን በዓል እንዴት አሳለፋችሁ? ደስ በሚል ሁኔታ አሳልፋችሁታል ብለን እናስባለን፡፡ ልጆች! ዛሬ ልንነግራችሁ የፈለግነው ስለ ‹‹ልጅነት›› ነው፡፡ ልጅነቴ! ብለን ስንናገር ወይም ደግሞ ስናስብ ብዙ ሊታወሱን የሚችሉ ነገሮች አሉ፤

ቃና ዘገሊላ

በቃና ዘገሊላ ወይም በገሊላዋ ቃና ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የፈጸመውን ተአምር በማሰብ ቅድስት ቤተ ክርስቲያናችን በዓል ታከብራለች፡፡ ይህም በጥምቀት በዓል ማግስት በጥር ፲፪ ነው፡፡

‹‹ክርስቶስን የምታስመስለን የከበረች ጥምቀት›› ቅዳሴ አትናቴዎስ

በአዳምና በሔዋን በደል ምክንያት ልጅነታችንን በማጣታችን፣ ሰውን ወደ ቀደመ ክብሩ ሊመልሰው እግዚአብሔር ወልድ ከሰማያት ወርዶ፣ ከንጽሕት ቅድስት ድንግል ማርያም ተወልዶ፣ ድኅነትን ሊፈጽም ከጀመረባቸው አንዱ እና ዋነኛው የክርስትናችን መግቢያ በር ጥምቀት ነው፡፡

በዓለ አጋእዝተ ዓለም ሥላሴ

አጋእዝተ ዓለም ሥላሴ በኃጢአት የተገነባውን የሰናዖር ግንብ ያፈረሱበት አንድነታቸውንና ሦስትነታቸውን በግልጽ ያሳዩበት ጥር ሰባት ቀን የከበረ በዓል እንደመሆኑ በቤተ ክርስቲያናችን በድምቀት ይከበራል፡፡

ግዝረተ ክርስቶስ

በቤተ ክርስቲያናችን አስተምህሮ ከጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ከርስቶስ ዘጠኙ ንዑሳን በዓላት አንዱና የመጀመሪው ሲሆን ይህም ግዝረተ ክርስቶስ ይባላል። በቅዱስ ሉቃስ ወንጌል እንደተጻፈው “ሊገርዙት ስምንት ቀን በሞላ ጊዜ፥ በማኅፀን ሳይረገዝ በመልአኩ እንደ ተባለ፥ ስሙ ኢየሱስ ተብሎ ተጠራ። እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያምም ወደ ግዘረት ቤት ወሰደችው፤ ገራዡ ምላጩን ይዞ ቀረበ፤ ነገር ግን ምላጩ እጁ ላይ ሳላ ውኃ ሆኖ ፈሰሰ። ጌታችንም በተአምራት የተገረዘ ሆኖ ተገኘ፡፡” (ሉቃ.፩፥፳፩)

በዓለ ልደቱ ለአቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ

አባታችን አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ሀገራቸው ንሂሳ ግብጽ ነው፡፡መላው ሕይወታቸውንም በምድረ በዳ የኖሩ አባት ናቸው፤ በዝቋላ ተራራ ባለው ባሕር ውስጥ ፻ (መቶ) ዓመት ተዘቅዝቀው ለኢትዮጵያውያን ምሕረትን በመለመን ለብዙዎች ድኅነት የሆኑ ታላቁ አባታችን አቡነ ገብረ መንፈስ የተወለዱት ታኅሣሥ ፳፱ ቀን ቢሆንም በጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ልደት በዓል ምክንያት ሊቃውንተ ቤተ ክርስቲያን በሠሩልን ሥርዓት መሠረት ጥር ፭ በድምቀት እናከብራለን፡፡

ቁጣና መዘዙ

ቁጣ የሚጫር የእሳት ክብሪት ማለት ነው፡፡ እሳት አንድ ጊዜ በክብሪት ከተጫረች በኋላ ሰደድ እሳት ትሆናለች፡፡ በቁጣ ሁሉም የኃጢአት ዓይነቶች ከመዛግብቶቻቸው ወጥተው ይቀጣጠላሉ፡፡ አንድን ሰው ድንገት አንድ ቁጡ ሰው ተነሥቶ ክፉ ቢናገረውና በይቅር ባይነት መንፈስ ቢያልፈው እንኳን ያ ቁጡ ሰው ቀኑን ሙሉ በቁጣ ላይ ሠልጥኖ ይውላል።

ወልድ ተወለደልን!

ኧረ ይህች ቀን ምንኛ ድንቅ ናት!

በዓይን የማይታየው የተገለጠባት

የማይዳሰሰው በአካል የተገኘባት

አንድ አምላክ ፈጣሪ የተወለደባት

እርሱ ነው ተስፋችን የዓለም መድኃኒት

የሆነው ቤዛ ለሁሉ ፍጥረት!

ወልድ ተወለደልን መድኃኒዓለም

በከብቶች በረት በቤተ ልሔም!

‹‹ወደ ቤተ ልሔም እንሂድ!›› (ሉቃ.፪፥፲፭)

ውድ የእግዚአብሔር ልጆች! እንዴት አላችሁልን! ትምህርት እንዴት ነው? አሁንማ ፈተና ደርሷል አይደል ልጆች? ስለዚህ ጨዋታ ሳያታልላችሁ በትኩረት በማጥናት፣ ያልተረዳችሁትን በመጠየቅ፣ የግማሽ ዓመት ፈተናውን በጥሩ ውጠየት ለማለፍ ማቀድ አለባችሁ!

ታዲያ በቀደሙት ትምህርታችን ስለ ጾመ ነቢያትና ስለ ነቢያት አባቶቻችን ስንማማር ነበር፤ አሁን ደግሞ የጌታችን መድኃኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስ የልደት በዓል እናከብራለን፤