ልደተ አቡነ ተክለ ሃይማኖት

እንኳን ከጻድቁ አባታችን ለአቡነ ተክለ ሃይማኖት ልደት በዓል በሰላም አደረሰን!

የልደቱም ነገር እንዲህ ነው!….

በዓለ ቅዱስ ገብርኤል

ውድ የእግዚአብሔር ልጆች! እንዴት አላችሁልን? ሳምንቱ እንዴት አለፈ? በሰንበት ቤተ ክርስቲያን ሄዳችሁ መንፈሳዊ ትምህርት እየተማራችሁ እንደሆነ ተስፋችን እሙን ነው፤መልካም! ለዛሬ ልንነግራችሁ የተዘጋጀነው ቅዱስ ገብርኤል ከእሳት ስላዳናቸው ሦስቱ ሕፃናትና እና ይህን በዓል አስመልክቶ ክብረ በዓል ከሚከበርባቸው ቅዱሳን መካናት መካከል አንዱ ስለ ሆነው ስለ ቁልቢ ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ታሪክ ነው!

ብርሃንህን ላክልን!

ድቅድቁ ጨለማ ተጋርዶ ከፊቴ
ሰላም ቢያሳጣኝ ካለሁበት ቤቴ
ነፍሴን ካስጨነቃት ጥንቱ ጠላቴ
በእስራቱ ኖርኩኝ ጸንቶ ፍርሃቴ
ከልጅነት ጸጋ ለይቶኝ ከአባቴ

ነገረ ማርያም በነገረ ድኅነት

ነገረ ማርያም በነገረ ድኅነት ውስጥ ከፍተኛ ድርሻ ያለው ትምህርት ሲሆን አካላዊ ቃል እግዚአብሔር ወልድ ከባሕርይ አባቱ ከአብ ከባሕርይ ሕይወቱ ከመንፈስ ቅዱስ ሳይለይ ከምልአትነቱ ሳይጎድል ሰው ሆኖ በተገለጠ ጊዜ እመቤታችን ቅድስት ደንግል ማርያም በሰው ልጅ መዳን ላይ ያላትን ድርሻ (ምክንያትነት) የሚዳስስ ትምህርት ነው፡፡

በጸሎትህ ጠብቅ!

ከቅዱሳን አበው የሆነ ውልደትህ
የጸሎታቸው መልስ ለእናት ለአባትህ
ክብርህ እጅግ በዛ ተወደደ ሥራህ

ፍጥረት ያስደሰተ የውልደትህ ዜና
ገና ሕፃን ሳለህ የጀመርክ ምሥጋና፡፡
ጽድቅን ተጎናጽፈህ ወንጌል ተጫምተሃል
በጉብዝናህ ወራት መስቀሉን ሽተሃል፡፡

እንደ ጠዋት ጤዛ በምትረግፈው ዓለም
ልብህ ሳይሸነፍ ለምቾት ሳትደክም
ከትዳርህ ይልቅ ምንኩስናን መርጠህ
ከጫጉላ ቤት ወጥተህ በረኃ ተገኘህ፡፡

ፍቅር ግን እርሱ ነው!

ፍቅር ግን ምንድነው? ብዬ ስጠይቀው
ሁሉም ሊያብራራልኝ ሊገልጸው አቃተው!
ፍቅር ግን እርሱ ነው
ኢየሱስ ክርስቶስ አምላክ ወሰብእ የሆነው
ራሱን በመስቀል ለእኛ ሲል የሰዋው!

‹‹ለብ ያልህ አትሁን!››

የሁላችንም ሕይወት ትኩስ፣ ለብ ያለና በራድ ተብለው በሚገለጹ ሦስት ሁነቶች ውስጥ የሚገኝ ነው። ቅዱስ ዮሐንስ እነዚህን ሦስቱን የገለጸው ‹‹በራድ ወይም ትኩስ እንዳይደለህ ሥራህን አውቃለሁ፤ በራድ ወይም ትኩስ ብትሆንስ፣ መልካም ነበር፤ እንዲሁ ለብ ስላልህ፥ በራድም ወይም ትኩስ ስላልሆንህ ከአፌ ልተፋህ ነው›› በማለት ነበር፡፡ (ራእ.፫፥፲፭-፲፮)

‹‹ሁሉም ነገር ከንቱ ነው›› (መክ.፩፥፪)

ከፀሐይ በታች ሁሉም እንደ ጥላ የሚያልፍ መሆኑን ጠቢቡ ሰሎሞን በመጽሐፈ መክብብ መጀመርያ ላይ ሲገልጽ ‹‹ሁሉም ነገር ከንቱ ነው›› ብሎ ተናገረ። ጠቢቡ ይህን ያለው በሕይወት ካየው እና ከተረዳው ነው። እርሱም በዚህ ምድር ላይ በዕውቀት፣ በጥበብ፣ በሀብትም ሆነ በሥልጣን የሚተካከለው እንዳልነበረ በመጽሐፈ ነገሥት ተጽፏል፡፡

በዓለ ደብረ ቁስቋም

በከበረች በኅዳር ስድስት ቀን የምናስበው የእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ከተወደደ ልጇ ከመድኃኒዓለም፣ ከአረጋዊው ዮሴፍ እና ሰሎሜ ጋር ከስደት መመለስ እንዲሁም በቁስቋም ተራራ መገኘት ታላቅ በዓል ነው፡፡

የጸሎት ጊዜያት

ውድ የእግዚአብሔር ልጆች! እንዴት አላችሁ? ትምህርት እንዴት ነው!እንግዲህ ልብ በሉ!በመንፈሳዊውም ሆነ በዘመናዊውም ትምህርት ተምራችሁ ማደግ አለባችሁ፤ባለፈው ከሥርዓተ ቤተ ክርስቲያን አንዱ ከሆኑት ስለ ጸሎት ጥቂት ብለናችሁ ነበር!ለዛሬ ደግሞ እንደ እግዚአብሔር ቅዱስ ፈቃድ ስለ ጸሎት ጊዜያት እንማማራለን!