“ክፉውን በመልካም አሸንፍ እንጂ በክፉ አታሸነፍ” (ሮሜ ፲፪፥፳፩)

ክፉና በጎ የሰው ልጆች ባሕርያት ናቸው፡፡ ይሁን እንጂ እግዚአብሔር ዓለምን ሲፈጥር ለመልካም ነበረ፡፡ (ዘፍ.፩፥፲፪) ምንም እንኳን የፍጥረት አክሊል የሆነው ሰው ነጻ ፈቃዱን ተጠቅሞ ከብርሃን ጨለማን፣ ከሕይወት ሞትን፣ ከመታዘዝ አለመታዘዝን ቢመርጥም እግዚአብሔር አምላክ የፈጠረው ስሙን እንዲቀድስ ክብሩን እንዲወርስ ነበረ፡፡ ለዚህም ክፉና ደጉን መለየት ይችል ዘንድ አስቀድሞ የሚያስተውል አእምሮ ሰጥቶት ነበር፡፡ በኅሊናው መመራት ተስኖት የሰው ልጅ ከወደቀ በኋላ ዳግመኛ የተጻፈ ሕግ ሰጥቶታል፡፡ ሰዎች ራሳቸው ላይ የክፉ ብድራት እንዳይደርስባቸው አስበው በባልንጀራቸው ላይ ክፉ እንዳያደርጉ ክፉ ላደረጉ የክፉ ብድራት እንዲከፈላቸው ሙሴ ሕግን ጻፈላቸው፡፡

“ወደ ምሥራቅ ተመልከቱ” (ሥርዓተ ቅዳሴ)

ምሥራቅ የቃሉ ፍቺ “የፀሐይ መውጫ” ማለት ነው፡፡ (አለቃ ኪዳነ ወልድ መጽሐፈ ሰዋሰው ወግሥ ወመዝገበ ቃላት ሐዲስ ገጽ ፮፻፹) በሥርዓተ ቅዳሴ ላይ ዲያቆኑ “ወደ ምሥራቅ ተመልከቱ” በማለት በዜማ ለምእመናኑ ያውጃል፤ በእርግጥ በቅዳሴ ጊዜ በመካከል የሚያነቃቁና የአለንበትን ቦታ እንድናስተውል የሚያደርጉ ሌሎች ዐዋጆች አሉ፡፡ ከእነዚህም መካከል “እለ ትነብሩ ተንሥኡ፤ የተቀመጣችሁ ተነሡ” የሚለው ነው፡፡ በቅዳሴ ጊዜ ከታመመ ከአረጋዊ በቀር ማን ማንም አይቀመጥም፡፡ ሰው እያስቀደሰ እየጸለየ ልቡናው ሌላ ቦታ ይሆንበታል፤ ይባዝናል፤ ያለበትን ትቶ በሌላ ዓለም ይባዝናል፡፡ አንዳንዴ ጸሎት እየጸለይን ሐሳባችን ሊበታተን ይችላል፡፡ ከየት ጀምረን የት እንዳቆምንም ይጠፋብናል፤ መጀመራችን እንጂ እንዴት እንደጨረስነውም ሳናውቀው ጨርሰን እናገኘዋለን፤ ዲያቆኑ በቅዳሴ ጊዜ “የተቀመጣችሁ ተነሡ” ማለቱ “የቆማችሁ በማን ፊት እንደሆነ አስታውሉ” ሲል ነው፡፡

እንዲሁም “ወደ ምሥራቅ ተመልከቱ” ሲባል ምን ማለት ነው? ዲያቆኑስ ምን እንድናደርግ ነው ያዘዘን? የሚለውን በመቀጠል እናያልን።

በዓይኖችህ ታየዋለህ

በሰማርያ ረኃብ በጸናበት ዘመን የሚቀመስም ጠፋ፤ ከረኃቡ ጽናት የተነሣ እናት ልጇን እስከ መብላት ደረሰች። በእዚያም ሀገር ኤልሳዕ የሚባል የእግዚአብሔር ሰው ነበረ። እንዲህም አለ፤ ነገ በዚህች ከተማ በአንድ ሰቅል አንድ መሥፈርያ መልካም ዱቄት በአንድ ሰቅል ሁለት መስፈርያ ገብስ ይሸመታል። ያኔ ንጉሡ በእግዚአብሔር ላይ ተገዳደረ፤ እንዴት ይቻላልም አለ። የእግዚአብሔር ሰው ኤልሳ እንዲህ አለው፤ “ታየዋለህ እንጅ አትቀምሰውም” ልብን የሚከፍል ንግግር! በረኃብ የቆየች ሀገር ደስ በምትሰኝበት ሰዓት የማይጨበጥ ሕልም ሲሆን ምንኛ ያሳዝናል?  የሶርያ ንጉሥ ሲመኘው የኖረውን ነገር በዓይኑ አየው ግን አልቀመሰውም።  (፪ኛነገ.፯፥፪)

ሥርዓተ አምልኮ

በጸሎትና በስግደት እንዲሁም በምጽዋት የታገዘ ጾም በእግዚአብሔር ፊት የተወደደ በመሆኑ ድኅነትን ማሰጠት ብቻም ሳይሆን በረከትን ያስገኛል፡፡ በዚህም የተነሣ ሥራችን፣ ትዳራችን እንዲሁም አገልግሎታችን ይባረክልናል፡፡

ስብከተ ወንጌል

ቅዱስ ዳዊት “ኢትዝክር ለነ አበሳነ ዘትካት ፍጡነ ይርከበነ ሣህልከ እግዚኦ እስመ ተመንደብነ ፈድፋደ፤ የቀደመውን በደላችንን አታስብብን፥ ምሕረትህ በቶሎ ታግኘን፥ እጅግ ተቸግረናልና”  እንዳለ  የቀደመ በደላችንን ሳያስብብን ጭንቀታችንን ችግራችንን ይቅር ብሎ ወደ እዚህ ምድር መጥቶ የምሥራች፣ ብርሃን፣ መንገድ፣ መስታወት፣ የሕይወት ዛፍ የሆነችውን ወንጌልን ሰበከን፤ አስተማረን። (መዝ.፸፰፥፰) ሐዋርያትንም “ሑሩ ውሰተ ኩሉ ዓለም ወስብኩ ወንጌለ ለኩሉ ፍጥረት፤ ወደ ዓለም ሁሉ ሂዱ፤ ወንጌልንም ለፍጥረት ሁሉ ስበኩ” በማለት በይሁዳ፣ በኢየሩሳሌም፣ በሰማርያና እስከ ዓለም ዳርቻ እንዲያስተምሩ ላካቸው። (ማር.፲፮፥፲፭)

“በምንም አትጨነቁ” (ፊል.፬፥፮)

በሕይወታችን ለሚገጥመን ማንኛውም ችግር ከእግዚአብሔር ዘንድ መፍትሔ ይኖረዋል፡፡ በእርሱ አምነንና ታምነን እስከኖርን ድረስ ከመከራና ከሥቃይ ያወጣናል፡፡ ሰዎች በተለያዩ ጊዜያት በሕይወታቸው ውስጥ ችግር ሊገጥማቸው ይችላል፡፡ የሚረዳቸው ቤተሰብም ሆነ ዘመድ ከሌላቸው ደግሞ ችግራቸውን ስለሚያባብሰው ወደከፋ መከራ ውስጥ ሲገቡ ሰምተንም ሆነ ተመልክተን ይሆናል፡፡ ነገር ግን አምላካችን እግዚአብሔር ሰውን የሚፈትነው ለበጎ እንደሆነ በማወቅና በመረዳት የነገን ተስፋ አድርጎ መኖር ይኖርብናል እንጂ ተስፋ መቁርጥ ወይም ማማረር አይገባም፡፡ በተቻለው መጠን ለኑሯችን ተሯሩጠን የዕለት ጉርሻችን መሙላት እንዲሁም ወደ ተሻለ ሕይወት መትጋት ይገባል፡፡

“ለፀሐይም ቀንን አስገዛው፤ ጨረቃንና ከዋክብትንም ሌሊትን አስገዛቸው” (መዝ.፻፴፭፥፰‐፲)

‹‹የፀሐይን፣ የጨረቃን፣ የከዋክብትን ሥራቸውን ዕወቅ፤ ከሁሉ የሚደንቅ ክበባቸውን ከሁሉ የሚበልጥ ብርሃናቸውን ሁሉ ዕወቅ፤ በየወገናቸው የሚያበሩ የሚመላለሱ የእነዚህን የምሳሌያቸውን ሥራ ዕወቅ፤ ሁሉ ጊዜ እርስ በእርሳቸው እንደምንም እንደሚቀራረቡ ዳግመኛም እንደምንም እንደሚራራቁ ዕወቅ…›› (ሃይማኖተ አበው ዘቅዱስ ባስልዮስ ምዕራፍ ፴፭፥፲፯)

የዕለተ ሠሉስ ፍጥረታት

ዕለተ ማክሰኞ የፍጥረት ሦስተኛ የምስጋና ሁለተኛ ቀን ነች፤ በባሕረ ሐሳብ ቀመር ደግሞ ዕለተ ቀመር ትባላለች፤ በፀሐይ አቆጣጠር ሰባተኛ ቀን ትባላለች፡፡ ዛሬ ግን የምናነሣው በዕለተ ፍጥረት ስለተከናወነባት ክንዋኔ ነው፡፡

የነፋስ ነገር

እግዚአብሔር ያለ ምክንያት የፈጠረው ፍጥረት የለምና ነፋስንም በምክንያት ፈጥሮታል፡፡ ልበ አምላክ ክቡር ዳዊት በመዝሙሩ “ሰማያት የእግዚአብሔርን ክብር ይናገራሉ፤ የሰማይም ጠፈር የእጁን ሥራ ያወራል፡፡ ቀን ለቀን ነገርን ታወጣለች፤ ሌሊትም ለሌሊት እውቀትን ትናገራለች” በማለት እንደዘመረው ሥነ ፍጥረት አእምሮ ላለው የሰው ልጅ የእግዚአብሔርን ባሕርያዊ መገለጫዎች ሥራና ፈቃዳት ያስተምራሉ፡፡ (መዝ.፲፰፥፩) ሰውንም ሲፈጥረው ከዐራቱ ባሕርያተ ሥጋ አምስተኛ ባሕርየ ነፍስን አድርጎ በመልኩና በምሳሌው እንደፈጠረው የታወቀ ነው፡፡ (ዘፍ. ፩፥፳፮) እነዚህ አራቱ ባሕርያተ ሥጋ የሚባሉትም ነፋስ፣ እሳት፣ መሬትና ውኃ ናቸው፡፡ በሥነ ፍጥረት ትምህርት እግዚአብሔር ሰውን ከእነዚህ ዐራት ባሕርያት የፈጠረበት ምክንያት በምልዓትና በስፋት ይተነተናል፡፡ በዚህ አጠር ያለ ጽሑፋችንም ከነፋስ ምን እንማራለን? የሚለውን እናነሣለን፡፡

“እግዚአብሔር ኃያል ነኝ ሲል እሳትን ፈጠረ“ (መጽሐፈ ሥነ ፍጥረት)

ታላቁ የቤተ ክርስቲያናችን አባት ሊቀ መዘምራን ዕቁበ ጊዮርጊስ ሲናገሩ “እግዚአብሔር ኃያል ነኝ ሲል እሳትን ፈጠረ“ ይላሉ፡፡