‹‹እግዚአብሔር ብርሃን ነው፤ ጨለማም በእርሱ ዘንድ ጥቂትስ እንኳ የለም›› (፩ዮሐ. ፩፥፭)
ፀሐይ በቀን፣ ጨረቃም በጨለማ ለምድር ብርሃን እንደሆኑ ሁሉ አምላካችን እግዚአብሔር በአማኞቹ ልብ ያበራል፤ ቅዱስ ዮሐንስ በመልእክቱ ‹‹እግዚአብሔር ብርሃን ነው፤ ጨለማም በእርሱ ዘንድ ጥቂትስ እንኳ የለም›› ሲል እንደተናረው በእርሱ ዘንድ ጨለማ የለም፤ ሁሌም ብርሃን ነው፡፡ ‹‹ከእንግዲህም ወዲህ ሌሊት አይኖርም፤ የመብራት ብርሃን፥ ወይም የፀሐይ ብርሃን አያስፈልጋቸውም፤ እግዚአብሔር ያበራላቸዋልና፤ ለዘለዓለምም እስከ ዘለዓለም ይነግሣሉ›› እንደተባለው ያ ብርሃን ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ነው፡፡ (ራእ. ፳፪፥፭)