ሁለቱ የዘመነ አስተርዮ ክብረ በዓላት በዳግማዊት ኢየሩሳሌም
ጥር 11/2004ዓ.ም
ዲ/ን ጌታየ መኮንን
የ2004 ዓ.ም የጌታችን የመድኀኒታችን የኢየሱስ ከርስቶስ የልደት (የገና) እና የጥምቀት በዓላት አከባበር እንደወትሮው ሥርዓተ ቤተ ክርስቲያንን የጠበቀና ያማረ ነበር፡፡

ካህናቱ ከታኅሣሥ 27 ቀን ጀምሮ በመድኀኒዓለም ቤተ ክርስቲያን አገልግሎት መስጠት የጀመሩ ሲሆን፤ የአማኑኤል በዓል ዋዜማ ጠዋት ደወል ተደውሎ በጣም በደመቀ ሁኔታ ዋዜማው ተቆሞ ውሏል፡፡ 7 ሰዓት ሲሆን ቅዳሴ ተገባ እስከ 9 ሰዓት ቅዳሴ ተጠናቀቀ፡፡ ማታ 2 ሰዓት ማሕሌት ተደውሎ እስከ ለሊቱ 10 ሰዓት የቀጠለ ሲሆን ከ10 ሰዓት እስከ 12 ሰዓት የቅዳሴው ሥርዓት ተከናውኗል፡፡ ጠዋት 3 ሰዓት የልደት በዓል ዋዜማ ተደውሎ እስከ 10 ሰዓት እንደቦታው ትውፊትና ሥርዓት መሠረት የቦታው ቀለም እየተባለ የዋዜማው ቅኔ ለባለ ተራዎቹ እየተሰጠ ተከናውኗል፡፡ ማታ 2 ሰዓት የበዓሉ ደወል ተደውሎ ከተለያዩ የሀገራችን ክፍሎች የመጡ ምእመናን፣ የውጭ ሀገር ዜጎች፣ የቤተ ማርያምን የውስጥና የውጭ ቦታ ማሜ ጋራ የተባለውን ቦታ ከበው በእልልታ በጭብጨባ ጧፍ እያበሩ ማኅሌቱ በመዘምራኑ፣ በካህናቱ፣ በዲያቆናቱ በድምቀት ቃለ እግዚአብሔሩ እየተዘመረና እየተወረበ አድሯል፡፡
ከቦታው ቀለሞች «ክርስቶስ መጽአ ውስተ ዓለም»
«ኮከብ ርኢነ ወመጽአነ ንሰግድ ሎቱ ለዘፈለጠ ብርሃነ»
ሥርዓተ ቅዳሴው እንዳለቀ የአስራ አንዱም አብያተ ክርስቲያናት ካህናትና ዲያቆናት ልብሰ ተክህኖ ለብሰው መስቀል፣ ጥላ፣ ስዕላት ይዘው ወደ ማሜ ጋራ ይወጣሉ መዘምራኑ ከሁለት ተከፍለው ከላይና ከታች ሆነው ምሳሌውም የመላእክትና የኖሎት በአንድነት እግዚአብሔርን ያመሠገኑበት ሲሆን «ቤዛ ኩሉ ዓለም ዮም ተወልደ» እያሉ እየተቀባበሉ በዓሉን በደማቅ ሁኔታ አክብረውታል፡፡ ልክ 3 ሰዓት ሲሆን ቤዛ ኩሉ አልቆ ትምሀርትና ቃለ ምዕዳን በሀገረ ስብከቱ ሊቀ ጳጳስ ብጹዕ አቡነ ቄርሎስ ተደርጎ ልክ 4 ሰዓት የበዓሉ ፍጻሜ ሆኗል፡፡
በዘንድሮው ክብረ በዓል ምንም እንኳን የሀገር ውስጥ ምዕመናን ቁጥር አነስተኛ ቢሆንም፣ ከውጭ የመጡት ቱሪስቶች ቁጥር ግን ከቀድሞው የበለጠ እንደነብር ታውቋል፡፡
የጥምቀት በዓልም እንደ ልደት በዓል በቅዱስ ላሊበላ ለየት ባለ መልኩ የሚከበር በዓል ነው፡፡ ገና በዋዜማው ጠዋት 3 ሰዓት ዋዜማ ተደውሎ እስከ 7 ሰዓት ድረስ ዋዜማ ከተቆመ በኋላ ከ7 ሰዓት እስከ 9 ሰዓት ድረስ ሥርዓተ ቅዳሴው ተከናውኗል፡፡
ልክ 10 ሰዓት ታቦታቱ ከአስራ አንዱም አብያተ ከርስቲያናት ተነስተው በቦታው ሥርዓት መሰረት ወደ 750 የሚጠጉ ካህናትና ዲያቆናት ልብሰ ተክህኖ ለብሰው መምህራኑና መዘምራኑ ጥንግ ድርብ፣ ካባ፣ ሸማ ለብሰው ጠምጥመው መቋሚያና ፀናጽል ይዘው በተራ፤ ምዕመናኑ በእልልታና በሆታ ወደ ጥምቀት ባሕሩ ተጉዘዋል፡፡

ጥምቀት ባሕር እንደደረሱ ውዳሴ ማርያም፣ መልክዓ ማርያም፣ መልክዓ ኢየሱስና፣ መልክዓ ላሊበላ ተደግሞ ስለ ጥምቀት ትምህርት ተሰጥቶ ለውጭ ሀገር ዜጎችም በእንግሊዝኛ ቋንቋ ገለጻ ተደርጎ በጸሎት ከታረገ በኋላ ታቦታቱ ወደ መንበረ ክብራቸው ገብተዋል፡፡
በአጠቃላይ የጥምቀት በዓል በቅዱስ ላሊበላ ከጥንት ጀምሮ ባማረና በደመቀ ሁኔታ የሚከበር ሲሆን የውጭ ሀገር ዜጎችም በተለያዩ ጊዜያት ከዓመት ወደ ዓመት ቁጥራቸው እየጨመረ መጥቷል፡፡ በከተማው ያሉ ሆቴሎች ሁሉም ተይዘው በርካታ ቱሪስቶች ድንኳን ተከራይተው በጥምቀተ ባሕሩ ዙሪያ ማረፋቸው ታውቋል፡፡
በዚህ ዓመትም ወደ 6 የሚጠጉ የውጭ ዜጎች በጥምቀት የእግዚአብሔርን ልጅነት እንዳገኙ የቅዱስ ላሊበላ ደብር ዋና ጸሐፊ ሊቀ ሥዩማን መንግሥቴ ወርቁ ገልጸውልናል፡፡
ምሽት 2፡00 ሰዓት የበዓሉ ደወል ተደውሎ አገልግሎት የሚጀመር ሲሆን 10 ሰዓት ሲሆን ቅዳሴ ይገባል፡፡ ልክ 12፤00 ሰዓት ወደ ባሕረ ጥምቀቱ ይኬድና ጸሎቱ ይቀጥላል፡፡ 3፡00 ሰዓት ፍጻሜ ይሆናል፡፡ 5፤00 ሰዓት ሲሆን ታቦታቱ ይነሱና ወደ አብያተ ክርስቲያናቱ ይሄዳሉ፡፡ 9፡30 አካባቢም የበዓሉ ፍጻሜ ይሆናል፡፡
በዚህ ሁሉ ሂደት ልክ እንደ ቤዛ ኩሉ በዓል መዘምራኑ የክብር ልብሳቸውን ለብሰው በዝማሜ በወረብ በእልልታ በሆታ በትውፊቱና በሥርዓቱ መሠረት ይከናወናል፡፡
በዕለቱ ታቦታቱ ሲነሱ « ሀዲጎ ተሥዐ ወተስዐተ ነገደ» የሚለው ቃለ እግዚአብሔር ተወርቦ ይጀመርና «ወወጽአ በሰላም ቆመ ማእከለ ባሕር ገብዐ » በሚለው ወረብ ይደመደምና ታቦቱ በተለምዶ ማርያም ጥንጫ በሚባለው ቦታ በደብሩ አለቃ ምዕዳንና ፀሎት ከተደረገ በኋላ ታቦታቱ ወደ አብያተክርስቲያናቱ ይገባሉ፡፡
ካህናቱ እንደ መላእክት ያለ ድካም በዝማሬ በዝማሜ በወረብ በአንድ ድምጽ ይዘምራሉ፡፡ የወጭ አገር ዜጎችና የሀገር ውስጥ ምእመናን ካሜራቸውን በመያዝ ቪዲዮና በፎቶ ይቀርጻሉ ያነሳሉ፡፡ እንደዚሁ ሁሉ የቃና ዘገሊላ የቅዱስ ሚካኤልና የቅዱስ ላሊበላ ታቦታት እንደቦታው ሥርዐት እንደ ጥምቀቱ ምሉዕ ካህናት አጅበውት ቃለ እግዚአብሔሩ እየደረሰ ይመለሳሉ፡፡
በከተራ የሚወርዱት 12 ታቦታት ሲሆኑ አስሩ የጥምቀት ዕለት ሲመለሱ ሁለቱ የቃና ዘገሊላ ዕለት ይመለሳሉ፡፡ አካሄዳቸውም እንደቦታው ሥርዓት ሲሆን ይህም ከጥንት የተገኘ ለመሆኑ ገድለ ላሊበላ ላይ ተገልጾ ተቀምጦአል፡፡
ሥርዓቱ አባቶቻችን ጠበቀው በማቆየታቸው ዛሬም በዚሁ ሥርዓት ይቀጥላል፡፡ ለምሳሌ የታቦታቱ ቅደም ተከተል ይሄውም በየተራ በሰልፍ የሚሄዱበት መንገድ፣ የመዘምራን ዝማሜ፣ ጥንግ ድርብ ሻሽና ካባ ለባሽ ሆነው በሁለት ተከፍለው በተራ ይዘማሉ፡፡ ወረቡ በተራ በሊቃውንቱ እየተቃኘ ሌሎች እየተቀበሉ ይደርሳል፡፡
ቱሪስቶች ከዓመት ወደ ዓመት ፍሰታቸው እየጨመረ መጥቷል፡፡ ይህም ዝማሜው፣ አልባሳቱ፣ የበዓሉ ድምቀት ፣ የቦታው ሥርዓት ለየት ያለ እንዲሁም በእግዚአብሔር ድንቅ ጥበብ በቅዱስ ላሊበላ የታነጸው ህንጻ ከሊቃውንቱ፣ ሊቃውንቱ ከህንጻው ጋር አብረው የሚታዩና የማይጠገቡ በመሆናቸው እንደሆነ ሊቀ ሥዩማን ገልጸውልናል፡፡
ከሌሎች ቦታ ለየት የሚያደርገው በዓሉ የተለየ ቃለ እግዚአብሔርም አለ፡፡ ይህም በአባቶች ከቦታው ጋር እንዲስማማ ሆኖ በመደረሱ ነው፡፡
ለምሳሌ፡- «ዘከለሎ ብርሃን ዘከለለሎ»
«ወወጽአ በሠላም ቆመ ማዕከለ ባህር ገባዐ»
«አይኑ ዘርግብ ልብሱ ዘመብረቅ»የሚሉት ይጠቀሳሉ፡፡
በአጠቃላይ በዓሉ አመት እስኪደርስ የሚናፈቅ የሚወደድ ባላለፈ ባላለቀ ጥምቀት ለምን አንድ ጊዜ ብቻ ሆነ የሚያሰኝ ነው፡፡ ሁሉም ህብረተሰብ ወደ ቦታው ሄዶ አይቶ በረከት ቢቀበል በጣም ጥሩ ነው፡፡
ወስብሐት ለእግዚአብሔር





ደብረ ሃይማኖት መካነ ኢየሱስ የሃይማኖት አባቶችን ለሀገሪቱ ከማበርከቱም በላይ በኢትዮጵያ ካቶሊኮች ገብተዉ ከወጡበት የጥንቱ ጊዜ በኋላ መልኩን ቀይሮ የቤተ ክርስቲያን ሊቃዉንትን ሲያበጣብጥ የቆየዉ የቅባትና የጸጋ ሰርጎ ገብ ፈጽሞ ካልረገጣቸዉ የሰሜን ኢትዮጵያ የትርጓሜ ትምህርት ቤቶች አንዱ መሆኑ በሊቃዉንቱ በተደጋጋሚ ተመስክሮለታል፡፡የደብሩ አስተዳዳሪና የድጓ መምህር መልአከ ሃይማኖት ሲሳይ አሰፋ በታሪክ የሚታወሱትን ሊቃዉንት ሲያወሱ የታች ቤት ትርጓሜ መሥራች የሚባሉት መምህር ኤስድሮስ የዚህ ቦታ መምህር እንደ ነበሩና ጣና ገብተዉ መጻሕፍትን መርምረዉ የታች ቤቱን ትርጓሜ ጎንደር ልደታ ላይ ከማስተማራቸዉ በፊት መካነ ኢየሱስ ላይ ተምረዉ ከዚያም ወንበሩን ተረክበዉ ማስተማራቸዉንና በኋላም መጥተዉ በቦታዉ ጥቂት ጊዜያትን ከቆዩ በኋላ እዚያዉ አርፈዉ መቀበራቸዉን አስረድተዋል፡፡ የቦታዉን ታላቅነት አስመልክቶ በሊቃዉንቱ ዘንድ ብዙ የሚነገርለት መሆኑን ያወሱት መልአከ ታቦር ተሾመ ዘሪሁንም በታላቁ ሊቅ የኔታ ገብረ ጊዮርጊስ ከተቀኙት መወድስ ዉስጥ ፤
ነበር፡፡ በዚህም ከአምላኩ ዘንድ ዋጋ አግኝቶበታል፡፡ አንድ ወቅት ያዕቆብ ለላባ “ሃያ ዓመት ሙሉ ከአንተ ጋር ነበርሁ በጎችህና ፍየሎችህ አልጨነገፉም የመንጎችህንም ጠቦቶች አልበላሁም አውሬ የሰበረውን አላመጣሁልህም ነበር፤ እኔ ስለ እርሱ እከፍልህ ነበርሁ፤ በቀንም በሌሊትም የተሰረቀውን ከእጄ ትሻው ነበር፡፡ የቀን ሀሩር የሌሊት ቁር ይበላኝ ነበር ፤ እንቅልፍ ከዐይኔ ጠፋ”(ዘፍ.፴፩፥፴፰-፴፱)ብሎት ነበር፡፡ እናንተ እረኞች ይህን እረኛ ለመንጎቹ ምን ያህል እንዲጠነቀቅ አስተዋላችሁን? በሌሊት እንኳ እነርሱን ለመጠበቅ በትጋት ያለእንቅልፍ የሚተጋ እነርሱንም ለመመገብ በቀን የሚደክም እውነተኛ እረኛ ነበር፡፡
አገልግሎት በአርሲ ሀገረ ስብከት ከኅዳር 29/2004 ዓ.ም እስከ ታኅሣሥ 10/2004 ዓ.ም ለ11 ተከታታይ ቀናት በተለየዩ ወረዳዎች አካሔደ፡፡ 27 አባላት የተሳተፉበት ሐዋርያዊ አገልግሎት በተመረጡ 6 ወረዳዎች ውስጥ በሚገኙ ቤተ ክርስቲያናት እንዲሁም በአሰላ ከተማ በተሳካ ሁኔታ የተከናወነ ሲሆን ቅድስት ቤተ ክርስቲያን ያፈራቻቸው የማኅበረ ቅዱሳን ሰባኪያነ ወንጌል አማካይነት በአውደ ምሕረት ላይ ለምእመናን ሰፋ ያለ የወንጌል ትምህርት ተሰጥቷል፡፡ በማኅበሩ መዝሙር ክፍል አባላት አማካይነት ከአባቶች እግር ስር ቁጭ ብለው የተማሩትን የቤተ ክርስቲያኗን ሥርዓትና ትውፊት የጠበቀ ያሬዳዊ ዝማሬ አቅርበዋል፡፡
የኑፋቄ ትምህርት ይጠበቁ ዘንድ የቤተ ክርስቲያን ዶግማና ቀኖና መሠረት ያደረገ ትምህርት በቀጣይነት እንዲሰጥ፤ እንዳይቋረጥባቸው ተማጽነዋል፡፡ “በሕፃንነቴ ቤተ ክርስቲያን ውስጥ እሰማቸው የነበሩ መዝሙራትን እንዳስታውስ አደረገኝ፡፡ እባካችሁ እኛንም ልጆቻችንም ከዳንኪራ ባልተናነሰ በስመ መዝሙር ከሚቀርቡና ሥርዓተ ቤተ ክርስቲያን ካልጠበቁ ጩኸቶች ታደጉን፡፡” ሲሉ በምሬት ገልጸዋል፡፡ በከፍተኛ ውዥንብር ውስጥ ይከታቸው የነበረው የያሬዳዊ ዜማ አቀራረብ የማኅበረ ቅዱሳን የመዝሙር ክፍል ያቀረበውን ከተመለከቱ በኋላ ትክክለኛውን የቅድስት ቤተ ክርስቲያን ሥርዓትና ትውፊት የጠበቁትን ለመለየት እንደረዳቸውና ማኅበረ ቅዱሳን እየሰጠ ባለው አገልግሎት መደሰታቸውን ገልጸዋል፡፡ “የማኅበረ ቅዱሳን ዘማርያን በሚዘምሩበት ወቅት በተለይ ሴቶች እኅቶቻችን ሲዘመሩ የሙሴ እኅት ማርያም እስራኤላውያን ባህረ ኤርትራን በተሻገሩበት ወቅት ከበሮ ይዛ እግዚአብሔርን ያመሰገኘችበት ዝማሬ አስታወሰኝ፡፡ ሰናይ እገሪሆሙ ለእለ ይእዜኑ ሰናየ ዜና /ኢሳ.52 እንዲል የምሥራች የሚናገሩ ሰዎች እግሮች አመጣጥ መልካም ነው፡፡ መልካም ዜና የሚናገሩ ናቸውና፡፡”በማለት በአገልግሎቱ በመደሰት አስተያየታቸውን ሰጥተዋል፡፡በተጨማሪም ከየማዕከላቱ የማኅበረ ቅዱሳን አባላት ጋር ሰፋ ያለ ውይይት ተደርጓል፡፡


በመሰባሰብ የፈጸመው የቅዳሴ ሥርዓታችን አስቀድሞም በቅዱሳን መላእክት ዓለም የነበረና በምድር ባለች መቅደሱም በምእመናን መሰባሰብ የሚፈጸም ነው፡፡ “እኔ በመካከላቸው እሆናለሁ” ብሎ ደስ የሚያሰኝ ዘላለማዊ ቃል ኪዳን የገባልን ጌታችን፣ “ሁለት ወይም ሦስት በስሜ በሚሰበሰቡበት” በማለት መሰባሰባችን ጸጋና ረድኤቱን እንድናገኝ ምክንያት መሆኑን ነግሮናል /ማቴ.18፥20/ በዚህ ርዕስም የጌታን ቃል በታላቅ ትጋት በፈጸመች ሰማያዊ ሥርዓቷን ከቅዱሳን መላእክት ዓለም ያገኘች፣ የምስጋና ሥርዓቷም በትውፊት ደርሶ ለቤተ ክርስቲየን መሠረት በሆነው በጠንታዊት /በሐዋርያት ዘመን/ ቤተ ክርስቲያን ለምእመናን መሰባሰብ ይሰጥ የነበረውን ትኩረትና ምስጢራዊ እይታ እንመለከታለን፡፡
