“መራሔ ፍኖት” መንፈሳዊ ጉዞ ለግቢ ጉባኤያት ተዘጋጀ
መጋቢት 25 ቀን 2005 ዓ.ም.
በእንዳለ ደምስስ
በማኅበረ ቅዱሳን አዲስ አበባ ማእከል አስተባባሪነት በ60 ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ሥር ለሚገኙ 5000 /አምስት ሺህ/ ግቢ ጉባኤያት ተማሪዎች “መራሔ ፍኖት” /መንገድ መሪ/ የተሰኘ መንፈሳዊ ጉዞ ወደ ሱሉልታ ደብረ ምሕረት ቅድስት ሥላሴ ቤተ ክርስቲያን በዕለተ ሆሣዕና ሚያዚያ 20 ቀን 2005 ዓ.ም. መዘጋጀቱን የአዲስ አበባ ማእከል ዋና ጸሐፊ አቶ ካሳሁን ኃይሌ ገለጹ፡፡