ተራዳኢው መልአክ ቅዱስ ገብርኤል
ሐምሌ 18 ቀን 2007 ዓ.ም.
አንድ አምላክ በሆነ በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም ሐምሌ ዐሥራ ዘጠኝ በዚችም ቀን ሕፃኑ ቅዱስ ቂርቆስና እናቱ ኢየሉጣ በሰማዕትነት መከራ ተቀበሉ፡፡
This author has not written his bio yet.
But we are proud to say that Mahibere Kidusan contributed 1445 entries already.
ሐምሌ 18 ቀን 2007 ዓ.ም.
አንድ አምላክ በሆነ በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም ሐምሌ ዐሥራ ዘጠኝ በዚችም ቀን ሕፃኑ ቅዱስ ቂርቆስና እናቱ ኢየሉጣ በሰማዕትነት መከራ ተቀበሉ፡፡
ሰኔ 25 ቀን 2007 ዓ.ም.
በእንዳለ ደምስስ
በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የሰዋስወ ብርሃን ቅዱስ ጳውሎስ መንፈሳዊ ኮሌጅ በብሉያት እና በሐዲሳት ትርጓሜ፤ እንዲሁም በቀንና በማታ በነገረ መለኮት ትምህርት በዲፕሎማ ያሰለጠናቸውን 218 ደቀመዛሙርት ሰኔ 25 ቀን 2007 ዓ.ም በጠቅላይ ቤተ ክህነት ስብከተ ወንጌል አደራሽ አስመረቀ፡፡
ሰኔ 23 ቀን 2007 ዓ.ም.
ፍትሐት ማለት ከዚህ ዓለም በሞት ለሚለዩ ሰዎች በሕይወተ ሥጋ ሳሉ ከሠሩትና ከፈጸሙት በደል እንዲነጹ ከማእሠረ ኃጢአት እንዲፈቱ ወደ እግዚአብሔር የሚቀብ ጸሎት ነው፡፡ ቤተ ክርስቲያን ለሙታን ጸሎተ ፍትሐት እንዲደረግ ታዝዛለች፡፡
ጸሎተ ፍትሐት ለበደሉት ሥርየት ኃጢአትን፣ ይቅርታን ዕረፍተ ነፍስን ያሰጣል፡፡ ለደጋጎች ደግሞ ክብርን፣ ተድላን፣ ዕረፍትን ያስገኛል፡፡
ሰኔ 17 ቀን 2007 ዓ.ም.
በእንዳለ ደምስስ
ጉባኤ ፊደል የተሰኘና በፊደል ላይ ያተኮረ ፊደል፤ ጥንቱ እድገቱና ተግዳሮቱ በሚል በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ የሥነ ሰብእ፣ ቋንቋዎች ጥናት፣ ጋዜጠኝነትና ተግባቦት ኮሌጅ አዘጋጅነት በርካታ ጥናታዊ ጽሑፎች በዘርፉ ምሁራን ሰኔ 16 ቀን 2007 ዓ.ም በእሸቱ ጮሌ ሕንፃ መሰብሰቢያ አዳራሽ ቀርበዋል፡፡
ሰኔ 12ቀን 2007 ዓ.ም.
አንድ አምላክ በሆነ በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም ሰኔ ዐሥራ ሁለት በዚች ዕለት የከበረ የመላእክት አለቃ የመልአኩ የሚካኤል የመታሰቢያውን በዓል ያከብራሉ፡፡
(ክፍል 2)
ሰኔ 8 ቀን 2007 ዓ.ም.
በቀሲስ ይግዛው መኰንን
4. ሰማያዊውን ሕይወት ናፋቂዎች ስለሆኑ
ክቡር ዳዊት âበቤትህ የሚኖሩ ሁሉ የተመሰገኑ ናቸው፤ ለዓለምና ለዘለዓለምም ያመሰግኑሃል፡፡ አቤቱ እርዳታው ከአንተ ዘንድ የሆነለት በልቡም የላይኛውን መንገድ የሚያስብ ሰው ምስጉን ነው፡፡â በማለት ሰማያዊውን መናፈቅ እንደሚያስመሰግን በመንፈስ ቅዱስ ተቃኝቶ ተናገረ፡፡ መዝ. 83፥4
ግንቦት 27ቀን 2007ዓ.ም በማኅበረ ቅዱሳን የአዲስ አበባ ማእክል ሥራ አስፈጻሚ ጉባኤ አባላት ከአባለቱ ጋር ግንቦት 29ቀን 2007ዓ.ም ከቀኑ 10፡30 ጀምሮ የምክክር ጉባኤ ያደርጋል፡፡ ስለዚህ የአዲስ አበባ ማእከል አባላት በምክክር ጉባኤው እንድትገኙ ጥሪያችንን እናስተላልፋለን፡፡ የአዲስ አበባ ማእከል፡፡
ግንቦት 25ቀን 2007 ዓ.ም
ዲ/ን ዘአማኑኤል አንተነህ ከጎንደር ማእከል
ከግንቦት 22-23 ቀን 2007 ዓ.ም በመካነ ነገሥት ግምጃ ቤት ማርያም ቤተ ክርስቲያንና በደብረ ጽጌ መጥምቀ መለኮት ቅዱስ ዮሐንት ቤተክርስቲያን 3ኛው መደበኛ ጠቅላላ ጉባኤ ሲካሄድ በጉባኤው ተገኝተው የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የሰሜን ጎንደር ሀገረ ስብከት የሰንበት ት/ቤት ምክትል ኃላፊ መልአከ በረሃ ገብረ ሥላሴ አድማሱ ናቸው፡፡ በአንድነት መደበኛ ጠቅላላ ጉባኤው በአፈጻጸማቸው ከ1-3 ለወጡት ለደብረ ምሕረት አቡን ቤት ቅዳሴ ለገብርኤል ሰንበት ት/ቤት፤ ለልደታ ለማርያም ሰንበት ት/ቤትና ለወልደነጎድጓድ ቅዱስ ዮሐንስ ሰንበት ት/ቤት በቅደም ተከተል ተሸልመዋል፡፡ ልምዳቸውንም አካፍለዋል፡፡ በሰንበት ት/ቤቶች በአገልግሎት ዘመን ቆይታ ያላቸው ወንድሞች የሕይወት ልምዳቸውንና ምክራቸውን ለጉባኤው ተሳታፊዎች አካፍለዋል፡፡
ግንቦት 25 ቀን 2007 ዓ.ም.
ጅማ ማእከል
በማኅበረ ቅዱሳን የጅማ ማእከል ያዘጋጀው ሁለተኛው የሐዊረ ሕይወት መርሐ ግብር ግንቦት 22 ቀን 2007 ዓ.ም. በኮሳ ቅድስት ማርያም ቤተ ክርስቲያን ተካሄደ፡፡
ግንቦት 23ቀን 2007ዓ.ም
ዲ/ን ሚክያስ አስረስ
ይህች ዓለም ከእውነትን የራቀች መኖሪያዋን ሐሰት ያደረገች መሆኗ ይታወቃል፡፡ ሰው ማንነቱን አጥቶ በበደል ምክንያት በሐሰት ሰጥሞ ኖሯል፡፡ ሰው በፈቃዱ ጥመት ምክንያት ከሚፈጽማቸው በደሎች ትልቁ በደል ውሸት ነው፡፡ ውሸት ተሸንፎ ይወድቃል፤ ከሕይወት ይርቃል፡፡ የኀጣውእ ሁሉ ራስ ሐሰት ናት፡፡ ለዚህ ነው ክፋትን ከራሱ አንቅቶ የበደለ ዲያብሎስ አቡሃ ለሐሰት፤ የሐሰት አባት(ዮሐ.8፡44) የተባለው፡፡