በማኅበረ ቅዱሳን አዘጋጅነት ሁለት ጥናታዊ ጽሑፎች ቀረቡ
ግንቦት ፱ ቀን ፳፻፰ ዓ.ም
ዲያቆን ኤፍሬም የኔሰው
በጸሎተ ሃይማኖት *ዘዕሩይ ምስለ አብ በመለኮቱ* የሚለው ንባብ *በመለኮቱ ከአብ ጋር አንድ የሆነ* ተብሎ መስተካከል አለበት ተብሏል፡፡
የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን በዕቃ ቤትና በቅዱሳት መካናት አማካኝነት የቅርስ ቤተ መዛግብት እንደሆነች ተገልጿል፡፡
ወጣቱ ትውልድ የቤተ ክርስቲያንን አስተምህሮ የመጠበቅና የማስጠበቅ ኃላፊነት እንዳለበት ተነግሯል፡፡

በመተከል ሀገረ ስብከት በግልገል በለስ ማእከል ሥር በሚገኙ 3 ወረዳዎች 8620 አዳዲስ አማንያንን ሚያዝያ 15 እና 16 ቀን 2008 ዓ.ም መጠመቃቸውን የማኅበረ ቅዱሳን ትምህርትና ሐዋርያዊ አገልግሎት ዋና ክፍል የስብከተ ወንጌል ማስፋፊያ መርሐ ግብር ገለጸ፡፡
በማኅበረ ቅዱሳን የአዳማ ማእከል ለ4ኛ ጊዜ ያዘጋጀውን የሐዊረ ሕይወት መርሐ ግብር በመቂ ግራዋ ጃዌ አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ቤተ ክርስቲያን መጋቢት 11 ቀን 2008 ዓ.ም አካሔደ፡፡
ማኅበረ ቅዱሳን መጋቢት 11 ቀን 2008 ዓ.ም በምዕራብ ሸዋ ሀገረ ስብከት በደንዲ ወረዳ በሚገኘው ኤጀርሳ ለፎ ደብረ ገነት ቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተ ክርስቲያን የሚያካሒደው 10ኛው የሐዊረ ሕይወት መርሐ ግብር ከዚህ በፊት ከተካሔዱት በተሻለ ቅድመ ዝግጅት በማድረግ ላይ እንደሚገኝ ገለጸ፡፡
ብፁዕ አቡነ ናትናኤል በምሥራቅ ትግራይ ክለተ አውላሎ አውራጃ አውዳ ቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተ ክርስቲያን አጥቢያ ከአቶ ገብረ ሕይወት ፀዓዱ እና ከወይዘሮ ወለተ ክርስቶስ ግብረቱ ግንቦት 12 ቀን በ1923 ዓ.ም ተወለዱ፡፡ ወላጆቻቸው ልጆችን እየወለዱ ይሞቱባቸው ስለነበር በጭንቀት ውስጥ ሳሉ ነው ብፁዕነታቸው የተወለዱት፡፡
ማኅበረ ቅዱሳን