በአዲስ ዓመት አዲስ ሕይወት
ዘመን አዲስ የሚባለው እኛ ሰዎች (ክርስቲያኖች) ሕይወታችንን በጽድቅ ስናድስ ነው፡፡ ያለ መልካም ሥራ የሚመጣ ዓመት፤ ከክፉ ግብር ጋር የምንቀበለው ዘመን አዲስ ሊባልም፣ ሊኾንም አይችልም፡፡ የሰው ልጅ መንፈሳዊ ሕይወት በመልካም ሥራ ሲዳብር ግን መጭው ዘመን ብቻ ሳይኾን ያለፈውም አዲስ ነው፡፡
This author has not written his bio yet.
But we are proud to say that Mahibere Kidusan contributed 1445 entries already.
ዘመን አዲስ የሚባለው እኛ ሰዎች (ክርስቲያኖች) ሕይወታችንን በጽድቅ ስናድስ ነው፡፡ ያለ መልካም ሥራ የሚመጣ ዓመት፤ ከክፉ ግብር ጋር የምንቀበለው ዘመን አዲስ ሊባልም፣ ሊኾንም አይችልም፡፡ የሰው ልጅ መንፈሳዊ ሕይወት በመልካም ሥራ ሲዳብር ግን መጭው ዘመን ብቻ ሳይኾን ያለፈውም አዲስ ነው፡፡
እንግዲህ ጳጕሜን የምትባለው አስገራሚዋና ትንሿ ወራችን እንዲህ በስሌት የተሞላች፣ በሦስት ዓመታት አምስት ቀን ኾና ቆይታ በአራት ዓመቱ አንድ ጊዜ ስድስት፣ በየስድስት መቶ ዓመት ደግሞ ሰባት ቀን የምትኾን ወር ናት፡፡ እንደዚሁም ታላላቆቹ ወሮች ምንም ሳይፈጥሩ የልደትን ቀን የምትወስን፣ የዓመቱን ሠግር የምታመጣ፣ ታሪከኛ ወር ናት፡፡
በአጠቃላይ ይህ ወቅት ‹‹ቡሄ ካለፈ የለም ክረምት፤ ዶሮ ከጮኸ የለም ሌሊት›› እንደሚባለው ክረምቱ እየቀለለ፤ ዝናሙ እያባራ፤ ማዕበሉ እየቀነሰ፤ ሰማዩ እየጠራ የሚሔድበት የንጋት፣ የወጋገን፣ የብርሃን ጊዜ ነው፡፡
ያለማቋረጥ ፈጣሪያቸውን ልዑል እግዚአብሔርን ከሚያመሰግኑ ቅዱሳን መላእክት መካከል አንዱ መልአከ ጥዒና ወሰላም /የሰላምና የጤና መልአክ/ የሚባለው ቅዱስ ሩፋኤል ነው፡፡ ‹‹ሩፋኤል›› የሚለው የስሙ ትርጓሜ ደስ የሚያሰኝ፣ ቸር፣ መሐሪ፣ ቅን የዋህ ማለት ነው፡፡
ከጉባኤው አዳዲስ ክሥተቶች ውስጥ በጠቅላላ ጉባኤው ማጠቃለያ ነሐሴ ፳፱ ቀን ፳፻፰ ዓ.ም በዕለተ እሑድ ምሽት የብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳትና የሰባክያነ ወንጌል ምክርና የአደራ ቃል ያለበት የ፳ ደቂቃ ዘጋቢ ፊልም የጉባኤውን ተሳታፊዎች አስለቅሷል፡፡
በዛሬው ዕለትም የማኅበሩ ቀጣይ ስልታዊ ዕቅድ በተሳታፊዎች የቡድን ውይይት ተደርጎበታል፡፡ በመቀጠልም በሚቀጥሉት አራት ዓመታት ማኅበሩን የሚመሩ የሥራ አመራር አባላት በምልዓተ ጉባኤው በተሰየመው አስመራጭ ኰሚቴ አቅራቢነት በብፁዕ አቡነ ሉቃስ ቡራኬ በጸሎትና በዕጣ ተመርጠዋል፡፡
በሥልጠናውም የሥራ አመራር ጥበብ፤ የውሳኔ አሰጣጥና የግጭት አፈታት ዘዴ፤ ሕግጋተ ቤተ ክርስቲያንና ቃለ ዓዋዲ ከሥራ አመራር አንጻር፤ እንደዚሁም የፋይናንስ አስተዳደርና ሒሳብ አያያዝ የሚሉ አርእስት የተካተቱ ሲኾን በተጨማሪም የተሐድሶ መናፍቃን እንቅስቃሴን የተመለከተ የግንዛቤ ማስጨበጫ ገለጻ ለሠልጣኞቹ ተደርጎላቸዋል፡፡
ከጐብኚዎቹ መካከልም ጥቂት የማይባሉ ምእመናን በዐውደ ርእዩ መዘጋጀት የተሰማቸውን ደስታ በዕንባ ሲገልጹ የታዩ ሲኾን በአስተያየቶቻቸውም ማኅበሩ በየአገሩ እንደዚህ ዓይነት አስተማሪነት ያላቸውን መርሐ ግብራት ደጋግሞ እንዲያቀርብ አሳስበው ለዚህም የሚያስፈልገውን ኹሉ ድጋፍ ለማድረግ ፈቃደኛ መኾናቸውን ገልጸዋል፡፡
ሚዲያ ክፍላችን ያነጋገራቸው አንዳድ ምሩቃን በሥልጠናው ጠቃሚ ዕውቀት እንደቀሰሙበትና በርካታ ቁም ነገሮችን እንዳገኙበት ገልጸው ለወደፊቱም ‹‹የየማእከላቱ ክትትልና ድጋፍ እንዳይለየን›› ሲሉ አስተያየት ሰጥተዋል፡፡
በጉባኤው ከቀረቡት ጥናቶች መካከልም ‹‹በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የአብነት ትምህርት ቤት ተማሪዎች የአስኳላ ትምህርት መማር አስፈላጊነት››፤ ‹‹የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን መንፈሳዊ ፍርድ ቤቶች የማቋቋም ሒደት›› እና ‹‹የግእዝ ቋንቋ ለኢትዮጵያ ቋንቋዎች ዕድገት ያበረከተው አስተዋጽዖ› የሚሉት ርእሰ ጉዳዮች ይገኙባቸዋል፡፡