ቅድስት ድንግል ማርያም እና ታቦተ ጽዮን – የመጀመሪያ ክፍል
ታቦተ ጽዮን የእመቤታችን የቅድስት ድንግል ማርያም ምሳሌ ስትኾን፣ በውስጧ የያዘችው የሕጉ ጽላትም የጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ምሳሌ ነው፡፡ ታቦቷ ከማይነቅዝ እንጨት መሠራቷ የእመቤታችንን ንጽሕና የሚያመለክት ሲኾን፣ በውጪም በውስጥም በጥሩ ወርቅ መለበጧ ደግሞ ቅድስናዋንና በሁለት ወገን ድንግል መኾኗን የሚያስረዳ ነው፡፡