ከሃያ አምስት በላይ የግብጽ ምእመናን በቦምብ ፍንዳታ ሕይወታቸው ዐለፈ
በፍንዳታው ሕይወታቸው ያለፈ ምእመናን ሥርዓተ ቀብርም በብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ታዎድሮስ ካልዕ መሪነት ብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳት እና ብዙ ሺሕ የግብጽ ምእመናን በተገኙበት ታኅሣሥ ፫ ቀን ፳፻፱ ዓ.ም በግብጽ ቅድስት ማርያም እና ቅዱስ አትናቴዎስ ቤተ ክርስቲያን ተፈጽሟል፡፡
This author has not written his bio yet.
But we are proud to say that Mahibere Kidusan contributed 1445 entries already.
በፍንዳታው ሕይወታቸው ያለፈ ምእመናን ሥርዓተ ቀብርም በብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ታዎድሮስ ካልዕ መሪነት ብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳት እና ብዙ ሺሕ የግብጽ ምእመናን በተገኙበት ታኅሣሥ ፫ ቀን ፳፻፱ ዓ.ም በግብጽ ቅድስት ማርያም እና ቅዱስ አትናቴዎስ ቤተ ክርስቲያን ተፈጽሟል፡፡
ትምህርቶቹ የተለያዩ ናቸው ስንል የሚነገረው ምሥጢርና ይዘት በወቅታዊ በዓላት ላይ የሚያተኵር መኾኑን ለመግለጽ ነው እንጂ በየትኛውም ጊዜ በቤተ ክርስቲያናችን የሚቀርበው ትምህርት አንዱ የእግዚአብሔር ቃል ብቻ ነው፡፡
የአራቱ እሑዶቹ ስያሜ ከዐቢይ ጾም ሰንበታት ጋር ተመሳሳይ በመኾኑ መደናገራቸውን አንዳንድ ምእመናን ገልጸውልናል፡፡ እውነት ነው፤ የሰንበታቱ ስያሜ ከዐቢይ ጾም ሰንበታት ጋር ተመሳሳይ ይኹን እንጂ የሚዘመሩ መዝሙራት፣ በቅዳሴ ጊዜ የሚነበቡ ምንባባትና የሚቀርቡ ትምህርቶች ግን ይለያያሉ፡፡
ሜልኮል እስከ ዕለተ ሞቷ መካን ኾና እንደ ቀረች የእመቤታችንን ክብር የሚያቃልሉ መናፍቃንም የመንፈስ ቅዱስ ፍሬን ከማፍራት የመከኑ ናቸው /ገላ. ፭፥፳፪/፡፡
ወደ ታቦተ ጸዮን በመመልከታቸው ቤትሳምሳውያን ከተቀሠፉ አማናዊት ጽዮን በኾነችው በእመቤታችን ላይ እባብ ምላሳቸውን የሚያውለበልቡ መናፍቃንማ ዕድል ፈንታቸው ጽዋ ተርታቸው እንዴት የከፋ ይኾን!
‹‹ካህናተ ሰማይ ቅዉማን በዐውዱ አክሊላቲሆሙ ያወርዱ ቅድመ መንበሩ እንዘ ይሰግዱ ይርዕዱ ወኢይዝብጦሙ ሶበ ይበርቅ ነዱ፤ ካህናተ ሰማይ (ሱራፌል) በመንበሩ ዙሪያ ቆመው በፊቱ ሲሰግዱ የመለኮት እሳት ሲበርቅ እንዳይመታቸው ይንቀጠቀጣሉ፤›› /መጽሐፈ ሰዓታት/፡፡
ታቦተ ጽዮን ዳጎንን እንደ ቀጠቀጠችው ዅሉ ጌታችንና መድኀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስም ዲያብሎስንና ሠራዊቱን ቀጥቅጧቸዋል፡፡ ታቦተ ጸዮን የወርቅ ካሣ ተሰጥቷት ከምድረ ፍልስጥኤም እንደ ወጣች ጌታችንና መድኀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስም በወርቀ ደሙ ካሣነት የሲዖልን ነፍሳት ከሲዖል አውጥቷል፡፡
በሐዋርያት እግር የተተኩ አባቶች ሊቃነ ጳጳሳትን እያቃለሉ ‹‹በቅዱስ ሲኖዶስ አንመራም፡፡ ቤተ ክርስቲያን አርጅታለች፤ እናድሳት፤›› በማለት በክርስቶስ ደም የተመሠረተች የቅድስት ቤተ ክርስቲያንን ዶግማና ቀኖና የሚጥሱ ራሳቸውን ‹‹ተሐድሶ›› እያሉ የሚጠሩ ምናምንቴዎች እጣ ፈንታቸው እንደ አፍኒንና ፊንሐስ ነው፡፡
ስቡ ሳይቃጠል፣ መሥዋዕቱም ሳያርግ ለሆዳቸው ያደሩ አፍኒንና ፊንሐስ ሥጋ በመብላታቸው ምክንያት ‹‹ምናምንቴዎች›› እንደ ተባሉ፣ ዛሬም እግዚአብሔርን የሚፈሩ፣ የቤተ ክርስቲያንን ዕድገትና ልማት የሚናፍቁ ደጋግ ክርስቲያኖች የሚያስገቡትን ዐሥራት፣ በኵራት፣ ቀዳምያት በመዝረፍ ቤተ ክርስቲያንን የሚበድሉ ብዙ ምናምንቴዎች አይታጡም፡፡
‹‹የቃል ኪዳኗ ታቦት የቅድስት ድንግል ማርያም ምሳሌና ጥላ ካልኾነች የማን ምሳሌና ጥላ ልትኾን ትችላለች? ይህቺ ታቦት በውስጧ የሕጉን ጽላት እንደ ያዘች እንደዚሁ ቅድስት ድንግል ማርያምም የሕጉ ባለቤት የኾነውን ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስን በማኅፀኗ ተሸክማዋለች፡፡››