የ፳፻፱ ዓ.ም በዓለ ልደትን በማስመልከት ቅዱስ ፓትርያርኩ የሰጡት ቃለ ምዕዳን
እኛን ለማዳን በለበሰው ሥጋ በቤተ ልሔም ተወልዶ በመካላችን የተገኘው፣ በመለኮታዊ ባህርዩ የማይወሰነው አካላዊ ቃል እግዚአብሔር ወልድ ጌታችን አምላካችንና መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ እንኳን ለሁለት ሺሕ ዘጠኝ ዓመተ ምሕረት በዓለ ልደቱ በሰላም አደረሳችሁ!!
This author has not written his bio yet.
But we are proud to say that Mahibere Kidusan contributed 1445 entries already.
እኛን ለማዳን በለበሰው ሥጋ በቤተ ልሔም ተወልዶ በመካላችን የተገኘው፣ በመለኮታዊ ባህርዩ የማይወሰነው አካላዊ ቃል እግዚአብሔር ወልድ ጌታችን አምላካችንና መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ እንኳን ለሁለት ሺሕ ዘጠኝ ዓመተ ምሕረት በዓለ ልደቱ በሰላም አደረሳችሁ!!
የቃጠሎው መንሥኤ እስካሁን በግልጽ እንዳልታወቀና በቃጠሎውም ከጽላቶቹ በስተቀር ሕንጻ ቤተ ክርስቲያኑ ሙሉ በሙሉ እንደ ወደመ የደብሩ አስተዳዳሪ መልአከ ሕይወት ሐዋዝ ተስፋ ለማኅበረ ቅዱሳን ሚድያ ክፍል አስታውቀዋል፡፡ እንደ አስተዳዳሪው ገለጻ ከአምስት መቶ ሺሕ ሰማንያ ብር በላይ የሚገመቱ ንዋያተ ቅድሳት በቃጠሎው ወድመዋል፡፡
‹‹ምእመናን በመንፈሳዊ ሕይወታቸው ብቻ ሳይኾን በማኅበራዊ ኑሯቸውም ከሌሎች ጋር ተስማምተው በፍቅር፣ በቅንነት፣ በሰላምና በአንድነት እንዲኖሩ የማስቻል ከማንም በላይ ከአምላክ ዘንድ የተሰጣት መንጋዋን ከጥፋት የመጠበቅ ከፍተኛ ሓላፊነት እንዳለባት ቤተ ክርስቲያናችን ተገንዝባ የአሠራር ችግሮችን በመቅረፍ ከመቼውም ጊዜ በበለጠ ትኩረት ሰጥታ መሥራት ይገባታል››
አቡነ ተክለ ሃይማኖት በእግዚአብሔር ድንቅ ጥበብ፣ በሊቀ መላእክት ቅዱስ ሚካኤል ብሥራት፤ በኢትዮጵያ ምድር በሰሜን ሸዋ ሀገረ ስብከት ልዩ ስሙ ኢቲሳ በሚባል ቦታ ከአባታቸው ከካህኑ ጸጋ ዘአብና ከእናታቸው ከቅድስት እግዚእ ኀረያ መጋቢት ፳፬ ቀን ተፀንሰው ታኅሣሥ ፳፬ ቀን ፲፪፻፲፪ ዓ.ም ተወለዱ፡፡
ስለዚህ የሠለስቱ ደቂቅ ድኅነትን በተመለከተ በድርሳነ ሚካኤል ላይ ሚካኤል፤ በድርሳነ ገብርኤል ላይ ገብርኤል፤ በድርሳነ ሩፋኤል ላይ ደግሞ ሩፋኤል አዳናቸው ተብሎ መገለጹ ከላይ በወንጌል እንዳየነው ትውፊቱን ለያይቶ መዘገብ እንጂ ተቃራኒ ነገር አይደለም፡፡
በዚህ በሠለስቱ ደቂቅ ድኅነት ውስጥ የታየው መገለጠጥ ዋነኛው ምሥጢርና መልእክትም የእግዚአብሔርን ሰው መኾንና አዳኝነት፤ እንደዚሁም እንደ ሠለስቱ ደቂቅ እሳትና ስለት፣ ሰይፍና ጐራዴ፤ እስራትና ግርፋት የሚቀበሉ ሰማዕታትን ዅሉ የሚያድናቸው እርሱ መኾኑን መግለጽ ነው፡፡
የማያመሰኳ እንስሳ የዋጠውን መልሶ እንደማያደቀው መልሶ መላልሶ እንደማያኝከው ዅሉ መናፍቃንም አንድ ጥቅስን በኾነ መንገድ ጐርሰው ከዋጡት በኋላ ምሥጢር አያመላልሱም፤ ደጋግመውም አያኝኩትም፡፡ ማለትም የሚመላለሱ ምሥጢራትን አያገኙም፤ አይመረምሩም፡፡
‹‹አጥምቃችሁን መመለስ ብቻ ሳይኾን ለወደ ፊትም አስተማሪ፣ መካሪ ካህን አጥተን ወደ ሌላ ቤተ እምነት እንዳንወሰድ እየመጣችሁ በመምከር፣ በማስተማርና በማበረታታት በሃይማኖታችን እንድንጸና ድጋፍ አድርጉልን፤››
‹‹ፈኑ ብርሃነከ ወጽድቀከ እማንቱ ይምርሐኒ ወይሰዳኒ ደብረ መቅደስከ ወውስተ አብያቲከ እግዚኦ፤ ብርሃንህን እና ጽድቅህን ላክ፤ እነርሱ መርተው ወደ ቅድስናህ ተራራና ወደ ማደሪያህ ይውሰዱኝ፤›› (መዝ. ፵፪፥፫)
እጅ ቢወድቁ ተመርጕዘው ይነሡበታል፡፡ እጅ የወደቀውን ንብረት ከአካል ሳይለይ ለማንሣት፣ የራቀውን ለማቅረብ፣ የቀረበውን ለማራቅ ይችላል፡፡ እግዚአብሔር ወልድም ከባሕርይ አባቱ ከአብ፣ ከባሕርይ ሕይወቱ ከመንፈስ ቅዱስ ሳይለይ ከእግዚአብሔር ርቆ የነበረውን አዳምን ወደ እርሱ አቅርቦታል፤ ከወደቀበት አንሥቶታል፡፡