አስተርእዮ
ጌታችን የአዳምና የሔዋንን የዕዳ ደብዳቤ ለመሻር በዮርዳኖስ ወንዝ በተጠመቀ ጊዜ የአንድነት እና ሦስትነት ምሥጢር ተገልጿል፡፡ ይህ ምሥጢር ከጥንተ ዓለም ጀምሮ በግልጽ ሳይታወቅ፣ ሳይገለጥ ተሰውሮ ይኖር ነበር፡፡
This author has not written his bio yet.
But we are proud to say that Mahibere Kidusan contributed 1445 entries already.
ጌታችን የአዳምና የሔዋንን የዕዳ ደብዳቤ ለመሻር በዮርዳኖስ ወንዝ በተጠመቀ ጊዜ የአንድነት እና ሦስትነት ምሥጢር ተገልጿል፡፡ ይህ ምሥጢር ከጥንተ ዓለም ጀምሮ በግልጽ ሳይታወቅ፣ ሳይገለጥ ተሰውሮ ይኖር ነበር፡፡
እግዚአብሔር ወልድ በለበሰው ሥጋ በዮርዳኖስ ወንዝ ሲጠመቅ፤ እግዚአብሔር አብ ‹‹የምወደው ልጄ ይህ ነው›› ብሎ አባትነቱን ሲመሰከር፤ እግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስም በርግብ አምሳል ከሰማይ ወርዶ በራሱ ላይ ሲያርፍ ፍጡራን በዓይናቸው አዩ፡፡
በማኅበረ ቅዱሳን የኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ አገልግሎት ክፍል የተሠራው ‹‹ተዋሕዶ›› የተሰኘው የስልክ አፕሊኬሽን አንድሮይድ (Android) የተባለውን የቴክኖሎጂ ውጤት ለሚጠቀሙ ዘመናዊ ስልኮች እና የኪስ ኮምፒውተሮች አመቺ በኾነ መልኩ እንደገና ተሻሽሎ ቀረበ፡፡ ይህ አፕሊኬሽን በ፳፻፮ ዓ.ም ለመጀመሪያ ጊዜ ተዘጋጅቶ የነበረ ሲኾን፣ ክፍሉ ከተጠቃሚዎቹ የደረሱትን አስተያየቶች በማካተት ልዩ ልዩ ማሻሻያዎችን አድርጎ ለሁለተኛ ጊዜ እንዲቀርብ አድርጓል፡፡ አፕሊኬሽኑ በውስጡም የጸሎት መጻሕፍትን፣ ወቅታዊ […]
ድንገት በደረሰው በዚህ የእሳት ቃጠሎ ሁለት መቶ ሃያ አምስት የደቀ መዛሙርት መኖሪያ ጎጆዎች፣ ልዩ ልዩ መጻሕፍት፣ ምግብ እና አልባሳት በአጠቃላይ ከሰባት መቶ ስልሳ ሦስት ሺሕ አምስት መቶ ብር በላይ የሚገመት ንብረት መውደሙን የፍኖተ ሰላም ማእከል የላከልን ዘገባ ያመላክታል፡፡
ሁለቱም እየተነጋገሩ ሲሔዱ የእሳት ሠረገላ፣ የእሳት ፈረስ በመካከላቸው ገባና ለያያቸው፡፡ ኤልያስም በዐውሎ ነፋስ፣ በንውጽውጽታ፣ በእሳት ሠረገላ ዐረገ፡፡ ኤልሳዕም የኤልያስን ወደ ሰማይ መወሰድ አይቶ ጮኸ፤ ‹‹የእስራኤል ኀይላቸው፣ ጽንዓታቸው አባ፣ አባት ሆይ›› አለ፡፡
‹‹ባለሙያ ገራዥ ሆይ! ደሜ ሳይፈስ ልትገርዘኝ ትችላለህን? በዕለተ ዓርብ በመስቀል ስሰቀል ካልኾነ በስተቀር ደሜ አይፈስምና፡፡ ጐኔን በጦር ሲወጉኝ ያን ጊዜ ውኀና ደም ይፈሳል፡፡ ይኸውም ለአዳምና ለሚያምኑ ልጆቹ መድኀኒት ይኾናል፤››
ሥጋችንን ተዋሕዶ ለድኅነት የተገለጠልንን መድኃኒታችንን እያሰብን ድኅነታችንን ገንዘብ በምናደርግበት በታላቁ በዓላችን ወቅት ዘመን በወለዳቸው ኃጢአቶች ድኅነታችንን እንዳናጣ ከመጠንቀቅ ጋርም በዓሉን የበረከት በዓል ልናደርገው እንደሚገባን አንርሳ፡፡
ከመርሐ ግብሩ ተሳታፊዎች መካከል አንዳንዶቹ በሐዊረ ሕይወቱ በመሳተፋቸው በርካታ መንፈሳዊ ቁም ነገር ማግኘታቸውን፣ በትምህርቱ ነፍሳቸው መርካቷንና አእምሯቸውም መደሰቱን ጠቅሰው ይህን ዅሉ ምእመን በአንድ ድንኳን ሥር አሰባስቦ፤ ቍርስ እና ምሳ መግቦ ቃለ እግዚአብሔር እንዲማር በማድረጉ ማኅበረ ቅዱሳንን አድንቀዋል፡፡
‹‹እንግዲህማ ሰላምን እንከተላት፤ ዛሬ ክርስቶስ በዳዊት አገር ተወልዷልና፡፡ በደላችንን ይቅር ብሎ የአብ አንድያ ልጁ፣ የአብ ኃይሉ፣ ወደ እኛ መጣ፤ ብርሃንን ይገልጥ ዘንድ፣ እንደ እኛ ሰው ኾነ፡፡ ከብቻዋ ከኃጢአት በቀር ሰው የሚኾነውን ዅሉ ኾነ፤››
‹‹… በዚያ ያለ እናት አባት አለው፤ በዚህም ያለ ምድራዊ አባት እናት አለው። በዚያ ገብርኤል በፍርሃት ይቆማል፣ በዚህም ገብርኤል በሐሴት የምሥራች ይናገራል፤ በዚያ በጽርሐ አርያም የሚደነቅ ከማይታይ አብ የመወለድ ምስጋና፤ በዚህም በቤተ ልሔም የሚደነቅ ከድንግል የመወለድ ምስጋና …››